Read Online in Amharic
Table of Content
መግቢያ እና ይዘቶች
መሰረታዊ መረጃ
የኩላሊት መድከም
ሌሎች ዋና ዋና የኩላሊት ህመሞች
የኩላሊት ህመም ወቅት አመጋገብ

20. የፕሮስቴት እጢ ህመም

ፕሮስቴት የሚባለው አካል በወንዶች ውስጥ ብቻ ነው የሚገኘው። የፕሮስቴት መጠን መጨመር በአዛውንት ወንድ ውስጥ (ብዙውን ጊዜ ዕድሜው 60 ዓመት በላይ) በመሽናት ላይ ችግር ያስከትላል። በሕይወት የመቆየት ዕድሜ እየመጨመሩ በፕሮስቴት እጢ ህመም የመያዝ እድል እንዲሁ ጨምሯል።

ፕሮስቴት ምንድን ነው? ተግባሩ ምንድነው?

ፕሮስቴት የወንዶች የመራቢያ ሥርዓት አካል የሆነ ትንሽ አካል ነው።

ፕሮስቴት የወንዶች የመራቢያ ሥርዓት ውስጥ የሚጠቃለል ትንሽ አካል ነው። ፕሮስቴት የሚገኘው ከሽንት ፊኛ በታች እና በፊንጢጣ ፊት ለፊት ነው። ፕሮስቴት የሁለተኛው የሽንት ቱቦን (ማለትም ከሽንት ፊኛ ሽንት የሚወስደውን ቱቦ) ይከበባል። በሌላ አገላለጽ የዚህ ሽንት ቧንቧው የመጀመሪያ ክፍል (3 . ያህል ርዝመት ያለው) በፕሮስቴት ውስጥ ያልፋል።

ፕሮስቴት የወንድ የዘር ፍሬ አካል ነው። በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ የወንዱ ዘርን የሚመግብ እና የሚሸከም ፈሳሽ ያመነጫል

ፕሮስቴት እጢ ምንድነው?

ቤናይን ማለት የፕሮስቴት ችግሩ በካንሰር ምክንያት የማይዝ እና ሃይፕርፕሌዣ ማለት ደግሞ መስፋት ወይም ማደግ ማለት ነው። ካንሰር- ነክ ያልሆነ የፕሮስቴት መስፋፋት ሲሆን በሁሉም ወንዶች ላይ ዕድሜያቸው እየጨመረ ሲሄድ የሚመጣ ትግር ነው ማለት ይቻላል። ወንዶች እያረጁ ሲሄዱ ፕሮስቴት ቀስ እያለ ያድጋል። የተስፋፋው ፕሮስቴት የሽንት ቧንቧውን ይጨምቃል ፣ የሽንት ፍሳሽን ያግዳል እና በመሽናት ላይ ችግር ያስከትላል። የሽንት ቱቦው በመጥበቡ ምክንያት የሽንት ፍሰት እየቀነሰ እና ሀይል እያጣ ይሄዳል።

የፕሮስቴት እጢ ምልክቶች

የፕሮስቴት እጢ ምልክቶች ብዙውን ጊዜ የሚጀምሩት 50 ዓመት እድሜ በኋላ ነው። በ 60 ዎቹ ዕድሜ ውስጥ ከሚገኙት ወንዶች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት እና በ 70 ዎቹ እና በ 80 ዎቹ ዕድሜ ውስጥ ካሉ ወንዶች እስከ 90% የሚሆኑት መካከል የፕሮስቴት እጢ ምልክቶች አላቸው። አብዛኛዎቹ የፕሮስቴት እጢ ምልክቶች ቀስ በቀስ የሚጀምሩ እና ባለፉት ዓመታት እየተባባሱ ይሄዳሉ። አብዛኛዎቹ የፕሮስቴት እጢ ምልክቶች ቀስ በቀስ የሚጀምሩ እና በዓመታት እየተባባሱ ይሄዳሉ። የፕሮስቴት እጢ የተለመዱ ምልክቶች:-

  • በተደጋጋሚ መሽናት በተለይም በምሽት። ይህ ብዙውን ጊዜ የመጀመሪያ ምልክት ነው
  • ቀስ ያለ ወይም ደካማ የሽንት ፍሰት
  • ፊኛው ሙሉ ሆኖ ቢሰማውም እንኳ የሽንት መፍሰሱን ለመጀመር ችግር ወይም መወጠር
  • ቶሎ ለመሽናት መፈለግ አጥብቆ የሚረብሽ ምልክት ነው
  • ለመሽናት መቸገር
  • የተቆራረጠ የሽንት ፍሰት
  • በሽንት መጨረሻ ላይ ማንጠባጠብ። የሽንት ጠብታዎች ከሽንት በኋላ እንኳን የውስጥ አልባሳት እንዲርሱ ምክንያት ይሆናሉ።
  • የፊኛ ባዶ አለመሆን ወይም ጨርሶ የመሽናት ስሜት አለመሰማት

የፕሮስቴት እጢ ችግሮች

ከባድ ፕሮስቴት እጢ ካልታከመ በጥቂት ታካሚዎች ውስጥ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ከባድ ችግሮች ያስከትላል። የፕሮስቴት እጢ የተለመዱ ችግሮች:-

አጣዳፊ የሽንት መወጠር:- በጊዜ ሂደት ያልታከመ ከባድ ፕሮስቴት እጢ ድንገተኛ ፣ ሙሉ በሙሉ እና ብዙውን ጊዜ ህመም ያለው የሽንት ፍሰት መቋረጥን ያስከትላል። እንደነዚህ ያሉት ህመምተኞች ከሽንት ፊኛ ውስጥ የተከማቸውን ሽንት ለማፍሰስ ካቴተር የሚባለውን ቱቦ ማስገባት ይፈልጋሉ።

ሥር የሰደደ የሽንት መወጠር:- ረዘም ላለ ጊዜ የሽንት ፍሰት በከፊል መዘጋት ሥር የሰደደ የሽንት መወጠርን ያስከትላል። ሥር የሰደደ የሽንት መወጠር ሥቃይ የለውም እና ከሽንት ፊኛ ባለ በተረፈ የሽንት መጠን ተለይቶ ይታወቃል። በተለመደው ጊዜ ከሽንት በኋላ ፊኛ ውስጥ የሚቀረው የሽንት መጠን ቀሪ ሽንት ይባላል። የፕሮስቴት እጢ መደበኛ ግኝት በከፊል ሙሉ የሆነ የሽንት ፊኛ ወይም አዘውትሮ አነስተኛ መጠን ያለው ሽንት መሽናት ነው።

ፊኛ እና የኩላሊት ጉዳት:- ሥር የሰደደ የሽንት መወጠር የፊኛውን የጡንቻ ግድግዳ መላላትን ያስከትላል። በረጅም ጊዜ ውስጥ ፊኛው ደካማ ይሆናል እናም ከእንግዲህ በትክክል ሽንት ማስወጣት አይችልም።

የቀረው የሽንት ብዙ ከሆነ የፊኛ ውስጥ ግፊት እንዲጨምር ያደርጋል። ከፍ ያለ የፊኛ ግፊት በመጀመርያ የሽንት ቱቦዎች እና ወደ ኩላሊት ሊተላለፍ ይችላል። የሽንት ቱቦዎች እና የኩላሊት መሙላቱ ምክንያት በመጨረሻ ወደ ኩላሊት ሽንፈት መከሰት ሊያመራ ይችላል።

የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን እና የፊኛ ጠጠሮች:- ፊኛውን ሙሉ በሙሉ ባዶ ማድረግ አለመቻል ለሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን እና ለፊኛ ጠጠሮች የመፍጠር አደጋን ይጨምራል።

ያስታውሱ ፕሮስቴት እጢ ለፕሮስቴት ካንሰር የመጋለጥ እድልን አይጨምርም።

የፕሮስቴት እጢ ምርመራ

የህክምና ታሪክ እና ምልክቶቹ ..ኤችን ሲያመለክቱ የፕሮስቴት ካንሰር አለመሆኑን ለማረጋገጥ የሚከተሉት ምርመራዎች ይከናወናሉ።

  • የጣት የፊንጢጣ ምርመራ

በዚህ ምርመራ ውስጥ ማለስለሻ የተቀባ ፣ በጓንት የተሸፈነ ጣት በቀስታ በታካሚው አንጀት ውስጥ ይገባል። የፕሮስቴቱን ትልቀት መገመት የፊንጢጣ የፊተኛው ግድግዳ በኩል በመዳበስ ማወቅ ይቻላል። ይህ ምርመራ ለዶክተሩ የፕሮስቴት መጠን እና ሁኔታውን ግምት ይሰጠዋል።

ፕሮስቴት እጢ ላይ ፕሮስቴት ትልቅ ለስላሳ እና በጠንካራ ይዘት ያለው ነው። ፕሮስቴት ጠንከር ያለ እና መደበኛ ያልሆነ ቅርፅ ካለው ካንሰርን ያለለክታል።

  • የአልትራሳውንድ ምርመራ እና ከሽንት በኋላ ፊኛ ውስጥ የሚቀረው ሽንት ልኬት

አልትራሳውንድ የፕሮስቴት መጠንን መገመት እና የካንሰር ምልክቶችን ፣ የመጀመርያ የሽንት ቱቦ መስፋትን ፣ የኩላሊት እጢ መኖርን እና ሌሎች ችግሮችን ለይቶ ማወቅ ይችላል።

አልትራሳውንድ በተጨማሪም ከመሽናት በኋላ በሽንት ፊኛ ውስጥ የሚቀረው የሽንት መጠን ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ ይጠቅማል። ከመሽናት በኋላ የሚቀረው የሽንት መጠን 50 ሚሊ ሜትር በታች የሆነ በቂ መሽናት ችሎታን ያሳያል። ከመሽናት በኋላ የሚቀረው የሽንት መጠን 100 እስከ 200 ሚሊ ወይም ከዚያ በላይ ከፍ ያለ ሲሆን ተጨማሪ ግምገማ ያስፈልጋል ተብሎ ይታሰባል።

  • የፕሮስቴት ምልክት ውጤት ወይም መረጃ ጠቋሚ (.ኤስ.አይ.)

የዓለም አቀፉ የፕሮስቴት ምልክት ውጤት (አይ..ኤስ.ኤስ) ወይም .. (አሜሪካን ዩሮሎጂካል አሶሴሽን) የምልክት መረጃ ጠቋሚ ለቢ..ኤች ምርመራ ይረዳል። በዚህ የምርመራ ዘዴ ታካሚዎች ስለቢ..ኤች የተለመዱ ምልክቶች መኖር አለመኖራቸውን ይጠየቃሉ። ከዚያ በኋላ መልሶቹ ተቆጥረው በተሰላው የፕሮስቴት ምልክቶች ውጤት መሠረት የሽንት ችግር ክብደት ይፈረድበታል።

  • የላቦራቶሪ ምርመራዎች

የላቦራቶሪ ምርመራዎች ቢ..ኤችን ለመመርመር አይረዱም። ነገር ግን ተጓዳኝ ችግሮችን ለመመርመር ይረዳሉ። ሽንት ለህመም ይመርመራል እንዲሁም ደም ለኩላሊት ተግባር ምርመራ ይደረግለታል።

የፕሮስቴት የተለፍየ አንቲጂን(.ኤስ.):- ለፕሮስቴት ካንሰር የሚደረግ የደም ምርመራ ነው።

  • ሌሎች ምርመራዎች

የፕሮስቴት እጢ ምርመራን ለማጣራት ወይም ለማግለል የሚደረጉ ሌሎች የተለያዩ ምርመራዎች ዩሮፍሎሜትሪ ዪሮዳይናሚክ ጥናቶች ሲስቶስኮፒ የፕሮስቴት ባዮፕሲ የደም ሥር ፓዬሎግራም ወይም ሲቲ ዩሮግራም እና ሬትሮግሬድ ፓዬሎግራፊ ናቸው።

የፕሮስቴት እጢ ምልክቶች ምልክቶች ያሉት ሰው የፕሮስቴት ካንሰር ሊኖረው ይችላል?

የፕሮስቴት ካንሰር እንዴት ይታወቃል?

አዎ። ብዙ የፕሮስቴት ካንሰር እና የፕሮስቴት እጢ ምልክቶች ተመሳሳይ ናቸው ስለሆነም ምልክቶችን መሠረት በማድረግ በሁለቱ ሁኔታዎች መካከል ያለውን ልዩነት ለመለየት አይቻልም። ግን ያስታውሱ ፕሮስቴት እጢ ከፕሮስቴት ካንሰር ጋር የተዛመደ አይደለም። የፕሮስቴት ካንሰር ምርመራን ሊያረጋግጡ የሚችሉ ሶስት በጣም አስፈላጊ ምርመራዎች የጣት የፊንጢጣ ምርመራ (.አር.) ፣ የፕሮስቴት የተለፍየ አንቲጂን(.ኤስ.) እና የፕሮስቴት ባዮፕሲ ምርመራ ናቸው።

የፕሮስቴት እጢ ሕክምና

የፕሮስቴት እጢ ሕክምና አማራጮችን የሚወስኑ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ነገሮች የሕመም ምልክቶች ክብደት በምልክቶች ምክንያት የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ ምን ያህል ተጽዕኖ እንደሚፈጠር እና ተያያTh የሕክምና ሁኔታዎች መኖራቸው ናቸው። የፕሮስቴት እጢ ሕክምና ግቦች የሽንት መወጠር ምልክቶችን ለመቀነስ የሕይወትን ጥራት ለማሻሻል ቀሪ የሽንት መጠንን ለመቀነስ እና የፕሮስቴት እጢ ተያያTh ትግሮችን ለመከላከል ናቸው።

ሦስት የተለያዩ የፕሮስቴት እጢ ሕክምና አማራጮች አሉ

. ያለምንም ህክምና ተጠንቅቆ መጠበቅ እና የአኗኗር ዘይቤ መለወጥ

. የመድሀኒት ሕክምና

. የቀዶ ጥገና ሕክምና

. ያለምንም ህክምና ተጠንቅቆ መጠበቅ እና የአኗኗር ዘይቤ መለወጥ

ምንም ዓይነት ህክምና ሳይኖር "መጠበቅ እና መመልከት" ቀላል ምልክቶች ወይም የማይረብሹ ምልክቶች ላላቸው ወንዶች ተመራጭ አማራጭ ነው። ነገር ግን ተጠንቅቆ መጠበቅ ማለት የፕሮስቴት እጢ ምልክቶችን ለመቀነስ ዝም ብለን መጠበቅ እና ምንም አለማድረግ ማለት አይደለም። በዚህ ጊዜ ሰውየው የፕሮስቴት እጢ ምልክቶችን ለመቀነስ በአኗኗር ዘይቤ ላይ ለውጥ ማድረግ እና እንዲሁም ምልክቶቹ እየተሻሻሉ ወይም እየተባባሱ ስለመሆናቸው በየጊዜው ዓመታዊ ምርመራዎች ማድረግ አለባቸው።

  • በሽንት ልምዶች እና በፈሳሽ ፍጆታዎች ላይ ቀላል ለውጦችን ያድርጉ።
  • በተቻለ መጠን የሽንት ፊኛ ባዶ እንደሆነ እስኪሰማዎ ድረስ ይሽኑ። ሽንት ለረጅም ጊዜ አይያዙ። ፍላጎቱ ከተነሳ ወዲያውኑ ይሽኑ።
  • ሁል ጊዜ ሁለት ጊዜ ይሽኑ። ይህ ማለት ሽንት በተከታታይ ሁለት ጊዜ ለማ ስወገድ መሞከር ማለት ነው። መጀመሪያ ዘና ባለ መንገድ በመደበኛነት መሽናት ፣ ለጥቂት ጊዜ መጠበቅ ፣ እና እንደገና ለመሽናት መሞከርን ያካ ትታል። ሙሉ ለሙሉ ባዶ ለማድረግ አይጣሩ ወይም አይጨነቁ።
  • ምሽት ላይ አልኮል እና ቡና ወይም ሻይ ከመጠጣት ይቆጠቡ። ሁለቱም የፊኛው ጡንቻ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ ፣ እናም ሁለቱም ኩላሊ ቶችን ሽንት እንዲያመነጩ ያነሳሳሉ ፣ ይህም ወደ ማታ-ጊዜ መሽናትን ያስ ከትላል።
  • ከመጠን በላይ ፈሳሽ መውሰድ ያስወግዱ (በቀን 3 ሊትር በታች ፈሳሽ ይውሰዱ)። ብዙ ፈሳሾችን በአንድ ጊዜ ከመውሰድ ይልቅ በቀን ውስጥ ፈሳሽ መውሰድን በተን ያድርጉ።
  • ከመተኛትዎ በፊት ወይም ከመውጣትዎ ጥቂት ሰዓታት በፊት ፈሳሽ መውሰድዎን ይቀንሱ።
  • ማስታገሻ መድኃኒቶችን ወይም የጉንፉን እና የሳይነስ መድኃኒቶችን በሐኪም ቤት ካልታዘዘ በስተቀር አይውሰዱ። እነዚህ መድሃኒቶች ምል ክቶችን ሊያባብሱ ወይም የሽንት መወጠርን ሊያስከትሉ ይችላሉ።
  • የሽንት መጠንን የሚጨምሩ መድኃኒቶችን የሚወሰዱበትን ጊዜ ይቀይሩ። መሸት ባለ ሰዐት አይውሰዱ።
  • በሞቃት አካባቢ ውስጥ ይቆዩ እና አዘውትረው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ። ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እጥረት ምል ክቶችን ሊያባብሱ ይችላሉ።
  • የማትሽንት ፍሰትን ለመከላከል ጠቃሚ ስለሆኑ የዳሌ ማጠናከሪያ እንቅ ስቃሴዎችን ይማሩ እና ያካሂዱ። የዳሌ ማጠናከሪያ እንቅስቃሴዎች ፊኛን የሚደግፉ እና የሆድ ዕቃን ለመዝጋት የሚረዱትን ጡንቻዎች ያጠናክ ራሉ። የሽንት ቁጥጥርንም ይረዳሉ። እንቅስቃሴዎቹ የዳሌ ጡንቻዎችን ደጋግመው ማጠንከር እና መለቀቅን ያጠቃልላሉ።
  • በጊዜ የተወሰነ እና ሙሉ በሙሉ በመሽናት ላይ ያተኮረ የፊኛ ልምድ ይኑርዎ። በመደበኛ ጊዜያት ለመሽናት ይሞክሩ።
  • የሆድ ድርቀት ህክምና ማካሄድ።
  • ጭንቀትን ይቀንሱ። ድንጋጤ እና ውጥረት በተደጋጋሚ ወደ መሽናት ሊያመራ ይችላል።

. የመድሀኒት ሕክምና

ቀላል እና መካከለኛ ምልክቶችን ለመቆጣጠር መድሃኒቶች መውሰድ በጣም የተለመደ እና ተመራጭ የሆነ መንገድ ነው። መድሃኒቶች ከታከሙ ወንዶች ውስጥ ሁለት ሦስተኛ ያህል ለሚሆኑት ዋና ዋና ምልክቶቻቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳሉ። ለተለቀ ፕሮስቴት ሁለት አይነት መድኃኒቶች አሉ።

አልፋ-አጋጆች (ታምሱሎሲን ፣ አልፉዞሲን ፣ ቴራዞሲን እና ዶክሳዞሲን):- በፕሮስቴት ውስጥ እና በአካባቢያቸው ያሉትን ጡንቻዎች የሚያላሉ ፣ የሽንት መወጠርን የሚያስታግሱ እና ሽንት በቀላሉ እንዲፈስ የሚያደርጉ በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶች ናቸው። በጣም የተለመዱት የጎንዮሽ ጉዳቶች ቀላል ራስ ምታት ማዞር እና ድካም ናቸው።

ፀረ-አንድሮጅንስ ወይም 5-አልፋ-ሪዳክቴስ አጋቾች (ፊናስቴራይድ እና ዱታስቴራይድ):- የፕሮስቴት መጠንን ሊቀንሱ የሚችሉ መድኃኒቶች ናቸው። እነዚህ መድሃኒቶች የሽንት ፍሰትን መጠን ይጨምራሉ እንዲሁም የቢ..ኤች ምልክቶችን ይቀንሳሉ። እነዚህ መድኃኒቶች እንደ አልፋ-አጋጆች በፍጥነት አይሰሩም (ሕክምናው ከጀመረ በስድስት ወራቶች ውስጥ ነው መሻሻል የሚታየው) እና በአጠቃላይ ከባድ የፕሮስቴት መስፋፋት ላላቸው ወንዶች በተሻለ ሁኔታ ይሰራሉ። የፀረ-አንድሮጅንስ በጣም የተለመዱት የጎንዮሽ ጉዳቶች ለወሲብ መነሳሳት አለመቻል እና የወንድ የዘር ፈሳሽ ማስወጣት ችግር ለወሲብ ፍላጎትን ማጣት እና ለወሲብ አቅም ማጣት ናቸው።

የጥምረት ሕክምና:- እነዚህ ሁለት መድሃኒቶች በተለየ መንገድ የሚሰሩ እና በተመሳሳይ ጊዜ የሚሰጡ ተጨማሪዎች ውጤት አላቸው። ስለሆነም የሁለቱም መድኃኒቶች በውህደት መውሰድ አንዳቸውን ለብቻ ከመውሰድ ይልቅ ለፕሮስቴት እጢ ምልክቶችን በተሻለ መንገድ ለመቆጣጠር ይጠቅማል። መድኃኒቶቹን በውህደት መውሰድ ከባድ የሕመም ምልክቶች ፣ ትልቅ ፕሮስቴት እና በከፍተኛ መጠን ለተሰጡ የአልፋ ማገጃ መድኃኒቶች በቂ ያልሆነ ምላሽ ለሰጡ ወንዶች ይመከራል።

የቀዶ ጥገና ሕክምና

የቀዶ ጥገና የሚመከረው በሚከተሉት ሁኔታዎች ነው

  • በህክምና የማይድን፣ ከመካከለኛ እስከ ከባድ ምልክት ላላቸው
  • አጣዳፊ የሽንት መወጠር ላላቸው
  • በተደጋጋሚ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን
  • በሽንት ውስጥ ተደጋጋሚ ደም መገኘት
  • በየፕሮስቴት እጢ ምክንያት የኩላሊት መበላሸት
  • ከየፕሮስቴት እጢ ጋር የፊኛ ድንጋይ ሲታከል
  • ሽንት ከተሸና በኋላ በፊኛ ውስጥ የሚቀረው የሽንት መጠን እየጨመረ ከሄደ

የተላዩዩት በፕሮስተት እጢ ላይ የሚከናወኑት የቀዶ ህክምናዎች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ

1. ትራንስዩሬትራል ሪሴክሽን ኦፍ ፕሮስቴት

ትራንስዩሬትራል ሪሴክሽን ኦፍ ዘ ፕሮስቴት ከመላ የፕሮስቴት ህክምናዎች መካከል በጣም ስኬታማው ሲሆን ብዙውን ጊዜ ከ መድኃኒትም የተሻለ ውጤት ያስገኛል። ቢያንስ ከ 85% ወደ 90% ለሚሆኑት በሽተኞች የሽንት ቧንቧ መዘጋትን የሚያቃልል ሲሆን ብዙውን ጊዜ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ መፍትሄ ነው። ትራንስዩሬትራል ሪሴክሽን ኦፍ ዘ ፕሮስቴት ከ ቀዶ ህክምናዎች ውስጥ ቀለል ያለው ሲሆን ዩሮሎጂስትበሚባሉ ሃኪሞች የሚከናወን ነው። በዚህ ህክምና የሽንት ቧንቧውን የዘጋው የ ፕሮስቴት ክፍል ይወገዳል። ትራንስዩሬትራል ሪሴክሽን ኦፍ ዘ ፕሮስቴት ማንኛውንም የቆዳ መቆረጥ ወይም መገጣጠጥን አይፈልግም ግን ሆስፒታል መተኛትን ይጠይቃል።

ከቀዶ ጥገና በፊት

  • ከሂደቱ በፊት የሰውየው ጤንነት ይረጋገጣል
  • ሲጋራ ማጨስ የደረት እና ቁስለት ኢንፌክሽን የመያዝ አደጋን ስለሚጨ ምር እና ማገገሙን ሊያዘገይ ስለሚችል ታካሚው ማጨስ እንዲያቆም ይጠየቃል
  • ታካሚው ደም-አቅጣኝ መድኃኒቶችን (ዋርፋሪን ፣ አስፕሪን እና ክሎፒዶግ ሬል) እንዲያቆም ይጠየቃል።

በቀዶ ጥገናው ወቅት

  • ትራንስዩሬትራል ሪሴክሽን ኦፍ ፕሮስቴት በአጠቃላይ 60 እስከ 90 ደቂቃዎች ያህል ይወስዳል
  • ትራንስዩሬትራል ሪሴክሽን ኦፍ ዘ ፕሮስቴት የሚካሄደው ብዙውን ጊዜ ህብረ-ሰረሰር በኩል ማደንዘዣ ተሰጦ ነው።
  • ኢንፌክሽንን ለመከላከል አንቲባዮቲኮች ይሰጣሉ።
  • በትራንስዩሬትራል ሪሴክሽን ኦፍ ፕሮስቴት ወቅት ፕሮስቴትን ለማስወ ገድ አንድ መሣሪያ (ሪሴክቶስኮፕ)በብልት በኩል ወደ ሽንት ቧንቧ ውስጥ ይገባል።
  • ሬሴክቶስኮፕ ለዕይታ እንዲያስችል ብርሃን እና ካሜራ ሕብረ ሕዋሳትን ለመቁረጥ እና የደም ሥሮችን ለመዝጋት የሚያስችል የኤሌክትሪክ ዑደት እና ፈሳሽ ወደ ፊኛው የሚወስድ ሰርጥ አለው።
  • በሂደቱ ወቅት የተወገደው የፕሮስቴት ሕብረ ሕዋስ የፕሮስቴት ካንሰር አለመኖሩን ለማረጋገጥ ወደ ሂስቶሎጂ ምርመራ ላቦራቶሪ ይላካል።

ከቀዶ ጥገና በኋላ

  • ከትራንስዩሬትራል ሪሴክሽን ኦፍ ፕሮስቴት በኋላ የሆስፒታል ቆይታ ብዙውን ጊዜ 2 እስከ 3 ቀናት ነው
  • ከቀዶ ጥገናው በኋላ አንድ ትልቅ ሶስት የሉዝ ካታተር በወንድ ብልት ጫፍ (በሽንት ቧንቧው በኩል) ወደ ፊኛው ውስጥ ይገባል።
  • በካቴተሩ በኩል ፈሳሽ በማስገባት ፊኛው ያለማቋረጥ ለ 12-24 ሰዓታት ያህል ያታጠባል። ይህም የሚደረገው ቀዶ ህክምናው ጊዜ የፈሰሰ ደም እናም በተጨማሪ የረጋ ደም ካለ ከፊኛ ለማስወገድ ነው።
  • ሽንት ጉልህ የሆነ የደም መፍሰስ ወይም የደም መርጋት ነፃ በሚሆንበት ጊዜ ካቴተር ይወገዳል።

ከቀዶ ጥገና በኋላ ምክር

ከትራንስዩሬትራል ሪሴክሽን ኦፍ ዘ ፕሮስቴት በኋላ አንዳንድ እርምጃዎችን መውሰድ ቀደም ብሎ ለማገገም ይረዳል።

  • ከፊኛ ሽንትን ቶሎ ቶሎ ለማስወገድ ብዙ ፈሳሾችን ይጠጡ
  • በመጸዳዳት ወቅት ሰገራን ለማስወገድ ብዙ አይጣሩ መጣር የደም መፍሰ ስን ሊያስከትል ይችላል
  • የሆድ ድርቀት ከተከሰተ ለተወሰኑ ቀናት አንጀት የሚያነቃቃ መድሃኒት ይውሰዱ
  • ከሐኪሙ ምክር ውጭ ደም-ማቅጠኛ መድኃኒቶችን አይጀምሩ
  • 4-6 ሳምንታት ከባድ እቃ ማንሳትን እና ከባድ እንቅስቃሴን ያስወግዱ
  • ከቀዶ ጥገናው በኋላ 4-6 ሳምንታት ግብረ ስጋ ግንኙነት አይፈፅሙ
  • አልኮል ቡና እና በርበሬ የበዛባቸውን ምግቦች ያስወግዱ

ከቀዶ ጥገና በኋላ ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮች

  • ወዲያውኑ የሚታዩ የተለመዱ ችግሮች የደም መፍሰስ እና የሽንት ቧንቧ ኢን ፌክሽን ናቸው።
  • ቆይተው ሊታዩ የሚችሉ ችግሮች የሽንት ቧንቧ መጥበብ፣ ሽንትን መቆጣ ጠር አለመቻል እና ወሲባዊ ድክመት ናችው።
  • የወንድ የዘር ፈሳሽ ወደ ፊኛ (ወደ ኋላ መመለስ) የትራንስዩሬትራል ሪሴክ ሽን ኦፍ ዘ ፕሮስቴት የተለመደ ችግር ነው በ 70% ከሚሆኑት በሽተኞች ውስጥ ይከሰታል።
  • ይህ የወሲብ ተግባርን ወይም ደስታን መቀነስ አያስከትልም ነገር ግን መሃ ንነትን ያስከትላል
  • የችግሮችን ተጋላጭነት ከፍ ሊያደርጉ የሚችሉ ምክንያቶች ከመጠን በላይ ውፍረት ፣ ማጨስ ፣ አልኮል አለአግባብ መጠቀም ፣ የተመጣጠነ ምግብ አለመመገብ እና የስኳር በሽታ ናቸው።

ከሆስፒታል ከወጣ በኋላ የሚከተሉት ችግሮች ከተፈጠሩ ታካሚው ባለበት ሐኪሙን ያነጋግሩ

  1. ሽንት ለመሽናት ከተቸገሩ ወይም ከነጭራሹ ሽንት መሽናት ካልቻሉ
  2. በህመም ማስታገሻ የማያቆም ከባድ ህመም ከተሰማዎት
  3. ካቴተሩን የሚዘጉ ትላልቅ የረጉ ደሞች ካሉ
  4. ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት ወይም ሌሎች የኢንፌክሽን ምልክቶች ከታዩ

2. ትራንዩሬትራል ኢንሲሽን ኦፍ ፕሮስቴት

ትራንዩሬትራል ኢንሲሽን ኦፍ ዘ ፕሮስቴት አነስተኛ ፕሮስቴት ላላቸው ወንዶች ወይም ጤንነታቸው በጣም ደካማ ለሆኑ እና ለ ትራንስዩሬትራል ሪሴክሽን ኦፍ ፕሮስቴት የማይመች ለሆኑ ትራንስዩሬትራል ሪሴክሽን ኦፍ ፕሮስቴት አማራጭ ነው።

የትራንዩሬትራል ኢንሲሽን ኦፍ ዘ ፕሮስቴት አሰራር ከ ትራንስዩሬትራል ሪሴክሽን ኦፍ ዘ ፕሮስቴት ጋር ተመሳሳይ ነው ፣ ነገር ግን ከፕሮስቴት ላይ ቲሹን ከማስወገድ ይልቅ በፕሮስቴት ውስጥ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ጥልቀት ያላቸው ቅደት የተሰሩ ናቸው።

እንዚህ ቅደት የሽንት ቧንቧን ሲፋት ይጨምራሉ፣በተሸማሪም የሽንት ቧንቧ ላይ ያለውን ሻና ይቀንሳሉ እናም የሽንት ፍሰትን ያሻሽላሉ

ትራንዩሬትራል ኢንሲሽን ኦፍ ዘ ፕሮስቴት ከ ትራንስዩሬትራል ሪሴክሽን ኦፍ ዘ ፕሮስቴት ጋር ሲነፃፀር ያነሰ የደም ፍሰት ነው ያለው ፣ ከ ቀዶ ጥገና ጋር የተያያዙ ችግሮችም የለውም፡ በሆስፒታል ብዙ ጊዜ መተኛት አያስፈልገውም፡ እናም ለማገገም የሚፈጀውም ጊዜ አጭር ነው። በተጨማሪም ለሽንት መቆጣጠር ችግር እና ለወንድ ዘር ወደፊኛ የመፍሰስ ችግሮች ተጋላጭነት በአንጻራዊው አነስተኛ ነው።

ነገር ግን፣ ትራንዩሬትራል ኢንሲሽን ኦፍ ዘ ፕሮስቴት የሽንት ቧንቧ መዘጋት በተያያዙ የሚመጡ ችግሮችን የመፍታት ውጤታማነቱ ከ ትራንስዩሬትራል ሪሴክሽን ኦፍ ፕሮስቴት ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ነው። አንዳንድ በሽተኞችም ትራንዩሬትራል ኢንሲሽን ኦፍ ዘ ፕሮስቴት ከተሰራላቸው በኋላ የሚፈለገውን ያህል ውጤት ባለመገኘቱ ምክንያት በድጋሚ ትራንስዩሬትራል ሪሴክሽን ኦፍ ዘ ፕሮስቴት ሊሰራላቸው ልያስፈልግ ይችላል።ትራንዩሬትራል ኢንሲሽን ኦፍ ዘ ፕሮስቴት ትልቅ ፕሮስቴት ላላቸው ህመምተኞች ፍቱህ መፍትሄ አይደለም።

3. ኦፕን ፕሮስታቴክቶሚ

ይህ ሆድ እቃ ተከፍቶ ሙሉ የ ፕሮስቴት ህብረ ህዋስ የሚወገድበት ቀዶ ጥገና ነው። ነገር ግን ከዚህ የተሻሉ እናም ቀለል ያሉ ብዙ የህክምና አማራጮች ስላሉ ይህ ቀዶ ጥገና የሚፈጸመው በጣም አልፎ አልፎ ነው።

ይሄ ቀዶ ጥገና የሚፈጸመው ከመጠን በላይ የ ፕሮስቴት ትልቀት ላላቸው እናም ከዚህ ጋራ ሌላም ችግር ለታከለባቸው በሽተኞች ነው።

አነስተኛ ቀዶ ሕክምና ሕክምናዎች

አነስተኛ ቀዶ ሕክምና ዘዴዎች ብዙ የማይጎዱ ናቸው። በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና ምርምር አነስተኛ ቀዶ ሕክምና ሕክምናዎች አነስተኛ ችግሮች ባሏቸው ቀላል አሰራሮች አማካኝነት ፕሮስቴት እጢን ለማከም ያተኮሩ ናቸው።

እነዚህ የሕክምና ዘዴዎች ከፕሮስቴት ውስጥ ከመጠን በላይ የሆነ ቲሹን ለማስወ ገድ ሙቀትን ሌዘርን ወይም የኤሌክትሪክ ኃይልን ይጠቀማሉ።

እነዚህ ሁሉ ህክምናዎች በወንድ ብልት ውስጥ ባለው የሽንት ቧንቧ በኩል በመውጣት ነው የሚሰሩት።

አነስተኛ ቀዶ ሕክምና ሕክምናዎች ጥቅሞች-አጭር የሆስፒታል ቆይታ ፣ አናሳ ማደንዘዣ አስፈላጊነት ፣ ከመደበኛ የፕሮስቴት ቀዶ ጥገና ይልቅ አነስተኛ አደጋዎች እና ችግሮች እና አጭር የሕመምተኛ የማገገሚያ ጊዜያት ናቸው።

የእነዚህ ዘዴዎች ጉድለታቸው የሚከተሉት ናቸው-ከመደበኛ ትራንስዩሬትራል ሪሴክሽን ኦፍ ዘ ፕሮስቴት ያነሰ ውጤታማነት ፣ ከ 5 ወይም ከ 10 ዓመት በኋላ እንደገና ቀዶ ጥገና የማድረግ ዕድሉ ከፍተኛ መሆን ለሂስቶፓቶሎጂ ምርመራ የፕሮስቴት ቲሹ አለመገኘት (ፕሮስቴት ካንሰር አለመኖሩን ለማረጋገጥ) እና ስለደህንነት እና ውጤታማነታቸው የተሰሩ የረጅም ጊዜ ጥናቶች ቁጥር አነስተኛ መሆናቸው። ከዚህም በተጨማሪ አነስተኛ ቀዶ ሕክምና ሕክምናዎች በአብዛኛዎቹ ታዳጊ ሀገሮች የማይገኙ እና በአሁኑ ጊዜ በጣም ውድ የሆኑ ናቸው።

በፕሮስቴት እጢ ውስጥ ጥቅም ላይ የዋሉ የተለያዩ አነስተኛ ወራሪ ሕክምናዎች ትራንስዩሬትራል ማይክሮዌቭ ተርሞቴራፒ ትራንስዩሬትራል በመርፌ ማስወገጃ፣ በውሃ ላይ የተመሠረተ ቴርሞቴራፒ ፣ የፕሮስቴት ስቴንት እና ትራንስቱረራል ሌዘር ቴራፒ ናቸው።

  1. ትራንስዩሬትራል ማይክሮዌቭ ቴርሞቴራፒ:- በዚህ ሂደት ውስጥ ማይክሮዌቭ ሙቀት የሽንት ፍሰትን የሚያግድ ከመጠን በላይ የፕሮስቴት ሕብረ ሕዋሳትን ለማቃጠል ይጠቅማል።
  2. ትራንስዩሬትራል በመርፌ ማስወገጃ፡- በዚህ አሰራር ውስጥ የሬዲዮ ሞገድ ኃይል የሽንት ፍሰትን የሚያግድ ከመጠን በላይ የፕሮስቴት ህብረ ህዋሳትን ለማርጋት እና ለመግደል ጥቅም ላይ ይውላል።
  3. በውሃ ላይ የተመሠረተ ቴርሞቴራፒ፡- በዚህ ዘዴ ውስጥ የሞቀ ውሃ ትርፍ የፕሮስቴት ህብረ ህዋሳትን ሞት እና መርጋት ያስከትላል።
  4. ትራንስቱረራል ሌዘር ቴራፒ፡- በዚህ ቴክኖሎጅ ውስጥ የሌዘር ኃይል የፕሮስቴት ትርፍ ክፍሎችን በማሞቅ ያጠፋል።
  5. የፕሮስቴት ስቴንት፡- ስቴንቶች ጥቅልሎሽ ቅርፅ ያላቸው ተጣጣፊ ፣ እራሳቸውን የሚያሰፉ የቲታኒየም ሽቦ መሣሪያዎች ናቸው። በዚህ ቴክኒክ በፕሮስቴት መተለቅ በጠበበው የሽንት ቧንቧ ክፍል ውስጥ አንድ ስቴንት ይቀመጣል። ስቴንት የሽንት መተላለፊያውን ክፍት ያደርገዋል እና በሽተኛው በቀላሉ እንዲሸና ያስችለዋል።

የፕሮስቴት እጢ ሕመምተኛ ሐኪም ማማከር ያለበት መቼ ነው?

የፕሮስቴት እጢ ሕመምተኞች በሚከተሉት ጊዜ ሀኪም ማማከር አለባቸው

  • መሽናት ሙሉ በሙሉ አለመቻል
  • በሽንት ጊዜ ህመም ወይም ማቃጠል
  • መጥፎ ሽታ ያለው ሽንት ወይም ትኩሳት እና ማንቀጥቀጥ ሲኖር
  • በሽንት ውስጥ ደም ሲገኝ
  • የልብሶችን መራስ የሚያስከትል ሽንት የመቆጣጠር ችሎታ ማጣት