Read Online in Amharic
Table of Content
መግቢያ እና ይዘቶች
መሰረታዊ መረጃ
የኩላሊት መድከም
ሌሎች ዋና ዋና የኩላሊት ህመሞች
የኩላሊት ህመም ወቅት አመጋገብ

11. ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም ምልክቶች እና ምርመራ

በዚህ ስር የሰደደ ህመም የኩላሊት ስራ የሚዳከመው በዝግታ ሲሆን ከወራት እስከ ዓመታት ይወስዳል። በህመሙ የመጀመሪያ ደረጃዎች ላይ ያሉ አብዛኞቹ ህመምተኞች በአንጻራዊ ሁኔታ ሲታይ የህመም ምልክት የማያሳዩ ሲሆን ይኸውም የሚሆነው ሰውነታቸው የማካካሻ ስራ ስለሚሰራ እና የሚፈጠረውን የሜታቦሊክ መዛባት በጊዜ ሂደት ስለሚለማመደው ነው።ነገር ግን የኩላሊት ስራ በጣም በሚዳከምበት ጊዜ በሠውነት ውስጥ ከሚጠራቀሙ መርዞች እና ፈሳሾች የተነሳ ምልክቶች መታየት ይጀምራሉ።

ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም ምልክቶች

ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ምልክቶች ምንድን ናቸው?

ምልክቶቹ በኩላሊቱ የጉዳት መጠን የሚለያዩ ሲሆን ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም በኩላሊቱ የመስራት ወይም የማጣራት አቅም ልክ በአምስት ደረጃዎች ይከፈላል። የኩላሊት ማጣራት አቅም በደም ክሬያትኒን መጠን የሚለካ ሲሆን ከ90./ደቂቃ በላይ ይሆናል።

ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም ደረጃዎች

ደረጃ 1 ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም(የኩላሊት የማጣራት አቅም 90-100%)

በደረጃ 1 ስር የሰደደ የኩላሊት በሽታ የኩላሊት የማጣራት አቅም 90./ደቂቃ/1.732 በላይ ቢሆንም ሽንት ውስጥ ያለ የፕሮቲን መጠን ከፍ ማለት ፤በ ራጅ አልትራሳውንድ MRI እና ሲቲ ስካን ላይ የሚታይ የኩላሊት ጉዳት ወይም በቤተሰብ አባል ላይ የፖሊሲስቲክ ኩላሊት ህመም መኖር እና የመሳሰሉ ከተለመደው የወጡ የላብራቶሪ ምርምራ ውጤቶች እና ግኝቶች ሊገኙ ይችላሉ። አብዛኛውን ጊዜ ግን ህመምተኞች ምልክት አያሳዩም።

ደረጃ 2 ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም(የኩላሊት የማጣራት አቅም 60-89%)

ደረጃ 2 ወይም መለስተኛ ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ጊዜ የኩላሊት የማጣራት አቅም 60-89./ደቂቃ/1.732 ሲሆን ህመምተኞች በአብዛኛው ምልክት አይኖራቸውም ሆኖም ግን አንዳንዶች ላይ በተለይ ማታ ጊዜ ሽንት ቶሎ ቶሎ የመሽናት፤የደም ግፊት መጨመር ፣በሽንት ምርመራ ላይ ከተለመደው ውጪ ግኝቶች ወይም በትንሹ የደም ክሬያቲኒን መጨመር ሊታይ ይችላል።

የኩላሊት ማጣራት አቅም ምድቦች

ደረጃ

ገለፃ

የኩላሊት የማጣራት አቅም

ከፍ ያለ ተጋላጭነት ያላቸው

ለስር የሰደደ የኩላሊት በሽታ አጋላጭ ሁኔታዎች ያሏቸው(የስኳር ህመም፣ከፍተኛ የደም ግፊት፣የቤተሰብ ታሪክ፣ከፍ ያለ ዕድሜ እና የመሳሰሉት)

90 በላይ

1

የኩላሊት ጉዳት(በሽንት ውስጥ የሚገኝ የፕሮቲን መጠን መጨመር)እና ኖርማል የኩላሊት የማጣራት አቅም መጠን

90 በላይ

2

የኩላሊት ጉዳት እና በመለስተኛ ደረጃ የቀነሰ የኩላሊት የማጣራት አቅም መጠን

60-89

3

3

በመለስተኛ ወይም መካከለኛ ደረጃየቀነሰ የኩላሊት የማጣራት አቅም መጠን

45-49

3

በመካከለኛ ወይም ከፍተኛ ደረጃ የቀነሰ የኩላሊት የማጣራት አቅም መጠን

30-44

4

በከፍተኛ ደረጃ የቀነሰ የኩላሊት የማጣራት አቅም መጠን

15-29

5

የኩላሊት ድክመት

15 በታች

 

ብሔራዊ የኩላሊት ፋውንዴሽን የኩላሊት ህመም ውጤቶች ጥራት ተነሳሽነት፡ለ ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም የክሊኒካል ልምድ መመሪያዎች

ደረጃ 3 ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም(የኩላሊት ስራ 30-59%)

ሶስተኛ ደረጃ ወይም መካከለኛ ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ላይ የኩላሊት የማጣራት አቅም መጠን 30-59./ደቂቃ/1.732 ነው። አሁንም ህመምተኛው ምልክቶች ላያሳይ ወይንም መለስተኛ ምልክቶችን ማሳያት ሊጀመር ይችላል። ሽንት ላይ የሚታዩ ያልተለመዱ ምልክቶችም ሊታዩ ሲችሉ በተጨማሪም የደም ክሬያቲኒን መጠን ከፍ ይላል።

ደረጃ 4 ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም (የኩላሊት ስራ 15-29%)

በአራተኛው ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ላይ የኩላሊት የማጣራት አቅም 15-29./ደቂቃ/1.732 ነው። ምልክቶቹ እንደ የኩላሊት ድክመቱን እንዳመጡት ምክንያቶች እና ተያያTh ህመሞች አይነት መለስተኛ እና ግልፅ ያልሆኑ ወይም በጣም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ።

ደረጃ 5 ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም (የኩላሊት ስራ 15% በታች)

አምስተኛው ስር የሰደደ የኩላሊት ህመምበጣም ከባድ ሲሆን የኩላሊት የማጣራት አቅምም 15./ደቂቃ/1.732 በታች ነው። በሌላ ስሙ የመጨረሻ ደረጃ የኩላሊት ህመም በመባል የሚታወቅ ሲሆን ህመምተኞቹ የኩላሊት እጥበት ህክምና ወይም የኩላሊት ንቅለ ተከላ ያስፈልጋቸዋል።ምልክቶቹ ከመካከለኝ እስከ ከፍተኛ ሊላያዩ ሲችሉ ለሕይወት አስጊ ለሆኑ እና ውስብስብ ችግሮች ይዳርጋሉ።

ህክምናው እና የኩላሊት ድክመት ምልክቶቹ እየጨመሩ ስለሚሔዱ አብዛኞቹ ህመምተኞች የኩላሊት እጥበት ህክምና ወይም የኩላሊት ንቅለ ተከላ ያስፈልጋቸዋል።

ዋና ዋና የኩላሊት ህመም ምልክቶች

 • የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ማቅለሽለሽ እና ወደ ላይ ማለት
 • ድካም እና የክብደት መቀነስ
 • የታችኛው የእግር ክፍል ላይ እብጠት መታየት
 • በተለይም ጠዋት ጠዋት ላይ የሚታይ የፊት ዐይን አካባቢ እብጠት መኖር፤
 • በተለይም ከባድ ፣ከቁጥጥር ውጪ እና ወጣቶች ላይ የሚታይ ከሆነ ከፍተኛ የደም ግፊት የማምጣት ዕድል አለው
 • ግርጣት
 • የእንቅልፍ ችግሮች፣የትኩረት ማጣት እና ማዞር
 • የቆዳ ማሳከክ፣የጡንቻ መሸማቀቅ ወይም የእረፍት ማጣት
 • ሽንጥ አካባቢ ህመም መሰማት
 • በተለይም በመኝታ ሰአታት ምሽት ላይ፤ ቶሎ ቶሎ መሽናት
 • አዋቂዎች ላይ የሚታይ አጥንት ህመም እና ስብራት በተጨማሪም ልጆች ላይ የሚታይ የእድገት ዝግመት
 • የግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎት መቀነስ፣ በተለይ ወንዶች ላይ የሚታይ ስንፈተ ወሲብ እና የሴቶች የወር አበባ መዛባት።

በከፍተኛ የደም ግፊት ተጠቂዎች ላይ መቼ ስር የሰደደ የኩላሊት ህመምን እንጠርጥር?

በከፍተኛ የደም ግፊት ተጠቂዎች ላይ ከታች ያሉትን ሁኔታዎች ስናገኝ ስርየሰደደ የኩላሊት ህመም መጠርጠር ይኖርብናል

 • ከፍተኛው የደም ግፊት በተገኘበት ጊዜ ዕድሜ 30 በታች ወይም 50 በላይ ሲሆን
 • ከፍተኛው የደም ግፊት ሲገኝ ከባድ ደረጃ ላይ ከሆነ (200/120 ሚሚ ሜሪኩሪ በላይ)
 • በመደበኛ ሕክምና እንኳን መቆጣጠር የሚያዳግት ከባድ የሆነ ከፍተኛ የደም ግፊት
 • ተያይዘው የሚመጡ የዓይን እይታ ችግሮች
 • ከመጠን ያለፈ ፕሮቲን በሽንት ውስጥ መገኘት
 • ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም የሚያሳዩት ምልክቶች ለምሳሌ የሰውነት እብጠት፣የምግብ ፍላጎት ማጣት እና ድካም የመሳሰሉት ናቸዉ።

ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም ችግሮች

ከባድ ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም የሚያስከትላቸው ውስብስብ ችግሮች ምንድን ናቸው?

ከባድ ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም የሚያስከትላቸው ውስብስብ ችግሮች፡-

 • ሳንባ ላይ በሚጠራቀም ውሃ(ውሃ የቋጠረ ሳንባ) አማካኝነት የሚመጣ ከፍተኛ የመተንፈስ ችግር እና የደረት ህመም
 • ከባድ የሆነ ከፍተኛ የደም ግፊት
 • ከባድ ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ
 • ከባድና ተከታታይ የድካም ስሜት መኖር
 • የማዕከለኛው የነርቭ ሥርዓት ችግሮች፡- ግራ የመጋባትና የብThታ ስሜት መስተዋል ፣ጽኑ የእንቅልፍ ስሜት፣ማንቀጥቀጥ እና ኮማ
 • የልብን የመስራት አቅም የሚያዳክም እና ለሕይወት አስጊ የሆነ ከፍተኛ ደም ውስጥ የሚገኝ የፖታሽየምቨ መጠን መታየት
 • ፔሪካርዳይተስ፣ከረጢት መሳይ ስስ የልብ ሽፋን(ፔሪካርድይም)ቁስለት መኖር።

ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም ምርመራዎች

ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም በመጀመሪያዎቹ ደረጃዎች ጊዜ ምልክት አይኖረውም። ብዙ ጊዜ ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ለመጀመሪያ ጊዜ በምርመራ የሚገኘው ከፍተኛ የደም ግፊት ሲገኝ፣ከፍ ያለ የክሬያቲኒን መጠን በደም ምርመራ ውጤት ውስጥ ሲገኝ ወይም በሽንት ምርመራ ውስጥ አልቡሚን በሚገኝበት ጊዜ ነው። ስለዚህ ለህመሙ ከፍ ያለ ተጋላጭነት ያለው ግለሰብ(የስኳር ሕመም፣ከፍተኛ የደም ግፊት፣ከፍ ያለ የዕድሜ ደረጃ እና በቤተሰብ ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም በጊዜ ምርመራ ማድረግ አለበት።

1. ሄሞግሎቢን

የሄሞግሎቢን መጠን በአብዛኛው አነስተኛ ሲሆን ደም ማነስ የሚመጣው የኩላሊት ኤሪትሮፖይቲንን የማምረት አቅም ስለሚቀነስ ነው።

2. የሽንት ምርመራ

አልቡሚን ወይም ፕሮቲን በሽንት ውስጥ መገኘት የመጀመሪያው ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ምልክት ሲሆን የአልቡሚን በእጅግ አነስተኛ መጠን እንኳን ሽንት ውስጥ መገኘት የመጀመሪያው ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ምልክት ሊሆን ይችላል። የፕሮቲን ሽንት ውስጥ መገኘት ከሰውነት ሙቀት መጨመር ወይም ከከባድ የአካል እንቅስቃሴ የመጣ ሊሆን ስለሚችል የኩላሊት ህመሙን ከመጠርጠር በፊት ሌሎች አምጪ ምክንያቶችን አስቀድሞ በምርመራ ለይቶ ማወቅ የተሻለ ይሆናል።

3. የደም ክሬያቲንን ዩሪያ ናይትሮጅን እና የኩላሊት የማጣራት አቅም መጠን ግምት

የደም ክሬያቲንን ልኬት ቀላል እና ውድ ያልሆነ የኩላሊት ስራን መለኪያ መንገድ ሲሆን የደም ክሬያቲኒን ልኬት ከጾታ እና ዕድሜ ጋር በመሆን የኩላሊት የማጣራት አቅም መጠንን ለመገመት በሚረዱ በተለያዩ ፎርሙላዎች ውስጥ በመግባት ያገለግላል። መደበኛ የደም ክሬያቲኒን ቁጥጥር በማድረግ ስር የሰደደ የኩላሊት በሽታ ሂደትን እና የሕክምናውን ውጤት መከታተል ይቻላል። በኩላሊት የማጣራት አቅም መጠን ግምት መሠረት ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም በ5 ደረጃዎች ይከፈላል። ክፍፍሉም ተጨማሪ ምርመራዎችን ለማዘዝ እና ተስማሚውን ሕክምና ለማድረግ ይጠቅማል።

4. የኩላሊት አልትራሳውንድ

አልትራሳውንድ ቀላል፣ጥሩ ውጤት ያለው እና ውድ ያልሆነ የኩላሊት መመርመሪያ መንገድ ነው። የተኮማተሩ ኩላሊቶች በአልትራሳውንድ ምርመራ ሲገኙ ስር የሰደደ የኩላሊት ህመምን ያመለክታሉ። ነገር ግን በአዋቂ ፖሊሲስቲክ ኩላሊት ህመም በስኳር ህመም የሚመጣ የኩላሊት ህመም እና አማይሎኢዶሲስ ኖርማል እና ተለቅ ያሉ ኩላሊቶች ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ላይ ሊታዩ ይችላሉ። አልትራሳውንድ በኩላሊት ጠጠር እና በሽንት ቧንቧ መዘጋት የሚመጣን ስር የሰደደ የኩላሊት ሕመም ለይቶ ለማወቅም ይረዳል።

5. ሌሎች ተጨማሪ ምርመራዎች

ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም የኩላሊትን የተለያዩ ስራዎችን ይረብሻል። እነዚህን ስራዎች ለመመርመር የተለያዩ ምርመራዎች ይደረጋሉ፡የኤሌክትሮላይት እና የአሲድ ቤዝ ባላነስ ምርመራዎች ሶዲየም፣ፖታሺየም፣ማግኒThም፣ባይካርቦኔት፣የደም ማነስ ምርመራዎች (ሄማቶክሪት፣ፌሪቲን፣ትራንስፈሪን ሳቹሬሽን ፣ፔሪፈራል ስሚር የአጥንት ህመም ምርመራዎች (ካልሺየም ፣ፎስፈረስ ፣አልካላይን ፎስፋቴዝ እና ፓራታይሮይድ (እንቅርቲት ዕጢ) ሆርሞን)ሌላ አጠቃላይ ምርመራዎች(የደም አልቡሚን መጠን ልኬት፣ኮሌስትሮል ፣ትራይግላይሴሪድስ፣የደም ስኳር ልኬት እና ሄሞግሎቢን 1 ኢሲጂ እና ኤኮካርዲዮግራፊ ናቸው።

መቼ ነው ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ታማሚ ሐኪም ጋር መሔድ ያለበት?

ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ታማሚዎች ከስር የተዘረዘሩት ሲያጋጥማቸው ወዲያውኑ ሐኪም ጋር መሔድ ይኖርባቸዋል-

 • ፈጣን የሆነ የኪሎ መጨመር፣ጉልህ የሆነ የሽንት መጠን መቀነስ፣የከፋ የሠውነት እብጠት፣የትንፋሽ ማጠር ወይም አልጋ ላይ በሚጋደሙበት ጊዜ ለመተንፈስ መቸገር
 • የደረት ሕመም፣በጣም ዝግ ያለ ወይም ፈጣን የልብ ምት፤
 • ትኩሳት፣ከባድ የሆነ ተቅማጥ ፣ከባድ የሆነ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ከ ባድ የሆነ ወደ ላይ ማለት፣ደም የቀላቀለ ተውከት ወይም ምክንያቱ ያልታ ወቀ የክብደት መቀነስ መከሰት፤
 • በጀመረ ቅርብ ጊዜ የሆነዉ ከባድ የጡንቻ መዛል ስሜት መኖር።
 • ግራ መጋባት፣በከባድ እንቅልፍ መሸነፍ እና ማንቀጥቀጥ
 • በቅርቡ የተባበሰ በጥሩ ቁጥጥር ውስጥ የነበረ ከፍተኛ የደም ግፊት
 • የቀላ ሽንት ወይም ከመጠን በላይ የሆነ መድማት