Read Online in Amharic
Table of Content
መግቢያ እና ይዘቶች
መሰረታዊ መረጃ
የኩላሊት መድከም
ሌሎች ዋና ዋና የኩላሊት ህመሞች
የኩላሊት ህመም ወቅት አመጋገብ

24. በልጆች ላይ የሚከሰት በማታ ሽንት አለመቆጣጠር ችግር

በእንቅልፍ ወቅት አልጋን ማራስ ወይም ያለፈቃድ ሽንትን ባለመቆጣጠር የሚከሰት የአልጋ እርጥበት በልጆች ላይ በጣም የተለመደ ነው። አብዛኛውን ጊዜ ያለ ምንም ህክምና ልጆች ሲያድጉ በራሱ የሚፈታ ችግር ነው። ቢሆንም ግን ለልጆቹ እና ለቤተሰቦቻቸው አሳሳቢ፣ ምቾትን የሚያሳጣ እና እፍረትን ሊያስከትል የሚችል ጉዳይ ነው። ይህ ችግር የሚያጋጥመው በኩላሊት በሽታ በስንፍና ወይም በልጆች ተንኮል ምክንያት አይደለም።

ምን ያህል ልጆች ለአልጋ ማራስ ችግር ይጋለጣሉ? በስንት ዕድሜም ሊያቆማል ይችላሉ?

አልጋን ማራስ በተለይም ከ 6 ዓመት በታች ባሉ ልጆች የተለመደ ክስተት ነው። እድሚያቸው 5 ዓመት በሆኑ ሕፃናት ውስጥ ከ 15 እስከ 20% ያህል የሆኑትን ሊያጠቃ ይችላል። ዕድሜ እየጨመረ ሲሄድ በተመጣጣኝ መጠን የክስተቱ ቁጥር ይቀንሳል። የአልጋ ማራስ ስርጭት በ 10 ዓመት ላይ 5 በመቶ፣ በ 15 ዓመት ላይ እና 2 በመቶ ፤በወጣቶች ላይ ደግሞ 1 በመቶ በታች ነው።

የትኞቹ ልጆች ናቸው በአልጋ ማራስ የመጠቃት ዕድላቸው ሰፊ የሆነው?

 • ወላጆቻቸው በልጅነታቸው ተመሳሳይ ችግር ያጋጠማቸው ልጆች።
 • የዘገየ አዕምሮ እድገት ያላቸው በዚህም ምክንያት የሽንት ከረጢታቸው ሲሞላ የመለየት ችሎታቸው የደከመባቸው ህፃናት።
 • ጥልቅ እንቅልፍ ያላቸው ልጆች።
 • ወንዶች ከሴቶች ይልቅ ብዙ ጊዜ ለዚህ ችግር ይጋለጣሉ።
 • የስነልቦና ጭንቀት ወይም የአካላዊ ጫና መጨመር መንስኤው ሊሆን ይችላል።
 • በጣም ትንሽ ቁጥር ባላቸው ልጆች ውስጥ (2%-3% ባሉ ህፃናት)የተ ወሰኑ የህክምና ችግሮች እንደ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ፣ የስኳር በሽታ ፣ የኩላሊት ሽንፈት ፣ የፒን ትሎች ፣ የሆድ ድርቀት ፣ ትንሽ ፊኛ ፣ በአከር ካሪ አጥንት ውስጥ ወይም በወንድ ልጆች ውስጥ የሽንት ቧንቧ ቫልቮች ጉድለት ና የመሳሰሉት ለዚህ ችግር ሊዳርጉ ይችላሉ።

ለአልጋ ማራስ ችግር መቼ እና የትኞቹ ምርመራዎች መከናወን አለባቸው?

የሚከናወኑት ምርመራዎች በተወሰኑ የጤና ወይም የሰውነት አካል ችግር አለባቸው ተብሎ በሚገመቱ ልጆች ላይ ብቻ ነው። በጣም የተለመዱት ምርመራዎች የሽንት ምርመራ ፣ በደም ውስጥ የሚገኘው የግሉኮስ መጠን፣ የአከርካሪ አልትራሳውንድ ወይም ኤክስሬይ እና የኩላሊት ወይም የፊኛ ሌሎች የምስል ምርመራዎች ናቸው።

የሚሰጠው ሕክምና

የአልጋ ማራስ ሙሉ በሙሉ ያለፈቃደኝነት የሚሆን ክስተት ሲሆን ሆን ተብሎ የሚደረግ አይደለም። ልጆች የአልጋ ማራስ ልምድ ቀስ በቀስ የሚጠፋ የሚቆም እንደሆነ መረዳት አለባቸው። በተጨማሪ በዚህ ምክንያት ሊቆጡ ወይም ሊቀጡ አይገባም። ለአልጋ ማራስ የመጀመሪያ ሕክምናዎች የሚያካትቱት ለችግሩ ትክክለኛው ግንዛቤ መኖር፣ ተነሳሽነት፣ ፈሳሽ የመውሰድን እና የአሸናን ልምዶች መለወጥ ናቸው። በእነዚህ እርምጃዎች የአልጋ ማራስ ልምድ የማይሻሻል ከሆነ የአልጋ ማራስ ማንቂያዎች ወይም መድኃኒቶች መሞከር ይችላሉ።

1. ትምህርት እና የተነሳሽነት ሕክምና፡-

 • ህፃኑ ስለ ችግሩ በአግባቡ ማወቅ እና መማር አለበት
 • የአልጋ ማርጠብ ሆን ተብሎ ያልተፈጠረ፤ የልጆቹ ስህተት ስላልሆነ ህፃናቱ መወቀስ የለባቸውም።
 • ማንም ሰው በዚህ ምክንያት ልጁቹ ላይ እንዳያፌዘስባቸዉ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል። አለፎ አልፎ ቢከሰትም ፤ህፃናቱም በዚህ አማካኝ ነት የሚደርስባቸውን ጭንቀት መቀነስ ወሳኝ ነው። በተጨማሪም የልጆቹ ቤተሰቦችም በቂ ድጋፍ ሊያደርጉላቸው እና ችግሩ ጊዜያዊ መሆኑን ለል ጆቻቸው ማስረዳት ይኖርባቸዋል።
 • ከዳይፐር ይልቅ የሥልጠና ሱሪዎችን ይጠቀሙ።
 • የለሊት መብራቶችን በአግባቡ በማመቻቸት በመሸ ጊዜ ልጆች ወደ መፀዳጃ ቤት በቀላሉ መድረስ መቻላቸውን ያረጋግጡ።
 • ተጨማሪ ጥንድ የለሊት ልብሶችን፣አንሶላ እና ፎጣ ማዘጋጀት። ይህንንም ማድረግ ልጁች አልጋቸውን አርሰው በለሊት በሚነሱበት ጊዜ የረጠቡ ትን ልብሶችን እና አንሶላዎች በቀላሉ መለወጥ እንድቺሉ ያደርጋቸዋል።
 • ህፃናቱ የሚተኙበት ፍራሾች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ፍራሹን በፕላስቲክ መሸፈን።
 • ከአንሶላቸው ስር አንድ ትልቅ ፎጣ ያስቀምጡ። ይህ ተጨማሪን እርጥበት ለመምጠጥ ይረዳል።
 • የሽንት ሽታ እንዳይኖር በየቀኑ ጠዋት ሰውነትን መታጠብን ያበረታቱ።
 • ልጅዎ አልጋቸውን ባላራሱ ጊዜ ማበረታታት እና መሸለም። አንድ ትንሽ ስጦታ እንኳን አንድ ነው ለልጅ ማበረታቻ።
 • የሆድ ድርቀት ካለ ችላ ሳይባል መታከም ይኖርበታል።

2. ልጆቹ የሚወስዱትን ፈሳሽ መጠን መገደብ፡-

 • ህፃኑ ከሚተኛበት ከሁለት እስከ ሶስት ሰዓታት በፊት የሚጠጣውን ፈሳሽ መጠን መገደብ። ቢሆንም ግን በቀን ውስጥ በቂ ፈሳሽ መውሰድውን ማረጋግጥ ያስፈልጋል።
 • ምሽት ላይ ካፊን ያላቸው እንደ ሻይ እና ቡናን ያሉትን መጠጦች ማስወ ገድ። በተጨማሪም ካርቦሀይድሬት ያላቸውን እንደ ኮካ ያሉ መጠጦች እና ቸኮሌትን ምሽት ላይ መገደብ ይኖርብናል። እነዚህ መጦች የመሽናት እና አልጋን የማራስ ልምድን ሊያባብሱ ይችላሉ።

3. የሰውነትን ፈሳሽ የማስወገጃ ልምድ ምክር፡-

 • ልጆች ከመተኛታቸው በፊት ቢያንስ ሁለት ጊዜ ሽንት እንዲሽኑ ማበረታ ታት ይኖርቦታል። የመጀመሪያ ጊዜ በመደበኛው የመኝታ ሰዓት ሲሆን ሁለ ተኛው ደግሞ ልጁዎ እንቅልፍ ከመተኛታቸው ጥቂት ደቂቃ ቀደም ብሎ ይሆናል።
 • ልጆች መፀዳጃ ቤትን በየተወሰኑ ሰዐታት አካባቢ የመጠቀም ልማድ እን ዲያዳብሩ ማድረግ።
 • በየምሽቱ ልጅዎ ከመተኛታቸው ከሶስት ሰዓታት በኋላ አንቅተው ሽንት እንዲሸኑ ማድረግ እና አስፈላጊ ከሆነም ማንቂያ መጠቀም ይኖርቦታል።
 • ህፃናቱ አልጋቸውን የሚያረጥቡበትን ሰዐት በመገመት የሚነቁበትን ጊዜ መወሰን ይቻላል።

4. የአልጋ ላይ ማንቂያ ደወሎች፡-

 • የአልጋ እርጥበትን የሚያረጋግጡ ደወሎች መጠቀም መቻል ችግሩን ለመ ቆጣጠር የሚረዳ ዘዴ ነው። ይህን የምንጠቀመው ዕድሜያቸው ከ 7 ዓመት በላይ ላሉ ህፃናት ነው።
 • ይህ ማንቂያ ከልጁ የውስጥ ሱሪ ጋር የተያያዘ ነው። ልጆች አልጋ ላይ ሽንት በሚሸኑበት ጊዜ መሣሪያው የመጀመሪያዎቹን የሽንት ጠብታዎች ለይቶ ድምጽ በማሰማት ልጁን ከእንቅልፉ ያስነሳል። ከእንቅልፉ የተነሳው ልጅ ሽንቱን ወደ መጸዳጃ ቤት እስከሚደርስ ድረስ መቆጣጠር ይችላል።
 • ይህ ማንቂያ ልጁ ልክ ሽንቱ በሚመጣበት ሰዐት በጊዜ መንቃትን ልምድ እንዲያዳብር ይረዳል።

5. የፊኛ ስልጠና እንቅስቃሴዎች፡-

 • አልጋ በሽንት አማካኝነት የማርጠብ ችግር ያለባቸው ብዙ ልጆች አነስተኛ ፊኛዎች አሏቸው። በመሆኑም፤ የፊኛ ስልጠና ግብ የፊኛውን አቅም ከፍ ማድረግ ነው።
 • በቀን ውስጥ ልጆች በርከት ያለ መጠን ያለዉ ውሃ እንዲጠጡ ይጠየ ቃሉ። ከዚያም በኋላ ሽንት የማስተላለፍ ፍላጎት ቢኖራቸውም ሽንታቸ ውን ወደ ኋላ እንዲመልሱ ወይም እንዲወጥሩ ይነገራቸዋል።
 • በተግባር ሲታይ አንድ ልጅ ረዘም ላለ ጊዜ ሽንት መያዝ ይችላል። ይህ የፊኛ ጡንቻዎችን ያጠናክራል እንዲሁም የፊኛውን አቅም ይጨምራል

6. የመድሀኒት ሕክምና፡-

መድሃኒቶች የአልጋ ማራስ ችግርን ለማስቆም እንደ የመጨረሻ አማራጭ ያገለግላሉናል። እናም በአጠቃላይ ጥቅም ላይ የሚውሉት ከሰባት ዓመት በላይ ለሆኑ ሕፃናት ብቻ ነው። እነዚህ መድሀኒቶች ውጤታማ ቢሆኑም ግን ለችግሩ ፈውስሊሆኑ አይችሉም። ለአልጋ ማራስ ልምድ ጊዜያዊ ማቆሚያ ሲሆኑ የዘላቂ መፍትሄ ሊሆኑ አይችሉም። ብዙውን ጊዜ መድሀኒቱ ከተቋረጠ ወይም ከቆመ በኋላ ችግሩ በድጋሚ ይመለሳል። ዘላቂ ፈውስ የማግኘት እድል ሰፊ የሚሆነው ከመድኃኒቶች ሳይሆን ከአልጋ ማንቂያ ደውሎች ነው።

. ዴስሞፕረሲን አስቴት:

የዴስሞፕረሲን ክኒኖች በገበያው ውስጥ የሚገኙ እና የሚታዘዙት ሌላ አማራጮች ሳይኖሩ ሲቀር ነው።ይህ መድሃኒት በለሊት የሚመረተውን የሽንት መጠን ለመቀነስ እና ጠቃሚ የሚሆነው ከፍተኛ የሽንት መጠን በሚያመርቱ ልጆች ላይ ብቻ ነው። ልጆች ይህን መድሃኒት መውሰድ ከጀመሩ በኋላ ምሽት ላይ የሚወስዱትን የፈሳሽ መጠን መገደብ የውሃ ስካርን ለመከላከል ይረዳል። ይህ መድሃኒት ብዙውን ጊዜ የሚሰጠው ከመኝታ ሰዓት ቀደም ብሎ ሲሆን ነገር ግን ህፃኑ በሌላ ምክንያት ብዙ ፈሳሽ ወስዶ ከነበረ መድሀኒቱን ከመስጠት መቆጠብ ይኖርበታል። ምንም እንኳን ይህ መድሃኒት በጣም ውጤታማ እና ጥቂት የጎንዮሽ ጉዳቶች ቢኖሩትም ዋጋው ከፍ ያለ በመሆኑ ተጠቃሚው ውስን ነው።

. ኢምፔራሚን:

ኢምፔራሚን የሽንት ከረጢትን ዘና የሚያደርግ መድሀኒት ሲሆን የፊኛ ፊንጢጣን ደግሞ ያጠነክራል። ይህ ደግሞ የፈኛን ሽንት የመያዝ አቅም ይጨምራል። መድሃኒቱ አብዛኛውን ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውለው ለ3-6 ወራት ያህል ነው።

በፍጥነት በሚያሳድረው ተጽዕኖ ምክንያት መድሃኒቱ የሚወሰደው ህፃናቱ ከሚተኙበት አንድ ሰዓት በፊት ነው። ይህ መድሃኒት በጣም ውጤታማ ቢሆንም በሚያስከትለው የጎንዮሽ ጉዳት ምክንያት በውስን መጠን ብቻ ጥቅም ላይ ይውላል። መድሀኒቱ የሚያስከትለው የጎንዮሽ ጉዳቶች እንደ ማቅለሽለሽ ፣ ማስታወክ ፣ ድክመት ፣ ግራ መጋባት ፣ እንቅልፍ ማጣት ፣ ጭንቀት ፣ የልብ ምት መሰማት ፣ የአይን ብThታ ፣ ደረቅ አፍ ፣ ሆድ ድርቀት እና የመሳሰሉት ነው።

. ኦክሳይቡታይኒን:

ኦክሳይቡታይኒን የቀን ቀን አልጋ የማራስ ችግርን ለመከላከል የሚረዳ መድሀኒት ነው። ይህ መድሃኒት የፊኛ መኮራመትን ለመቀነስ እና የፊኛ አቅም

ለመጨመር ያግዛል። መድሀኒቱን መውሰድ የሚያስከትለው የጎንዮሽ ጉዳቶች እንደ አፍ ድርቀት የፊት ገጽታ መለወጥ እና የሆድ ድርቀትን ናቸው።

አንድ ወላጅ ለልጆቹ ሐኪምን ማማከር ያለበት መቼ ነው?

የአልጋ ማራስ ችግር ያለበት የአንድ ልጅ ቤተሰብ ወዲያውኑ ሐኪም ማማከር ያለበት ልጁ:-

 • በቀን ጊዜ አልጋውን የማርጠብ ችግር ካለበት።
 • አልጋውንየማራስ ልምድ ከሰባት ወይም ከስምንት ዓመት በኋላ ከቀጠለ።
 • ቢያንስ ከስድስት ወር ደረቅ ጊዜ በኋላ እንደገና አልጋውን ማርጠብ ከጀመረ።
 • በመጸዳጃ ጊዜ መቀመጫን ማለፍ ወይም እራሱን መቆጣጠርን ሲያቅ ተው።
 • ትኩሳት ህመም ማቃጠል ፣ብዙ ጊዜ መሽናት ያልተለመደ ጥማት የፊት ወይም የእግር እብጠት እና የመሳሰሉት ምልክቶች ሲታዩበት።
 • በመጸዳጃ ጊዜ ደካማ የሽንት ፍሰት የመቅረት ችግር ወይም ሽንትን ለማ ስወገድ ተጨማሪ ሀይል ሚያስፈልግ ከሆነ።