Read Online in Amharic
Table of Content
መግቢያ እና ይዘቶች
መሰረታዊ መረጃ
የኩላሊት መድከም
ሌሎች ዋና ዋና የኩላሊት ህመሞች
የኩላሊት ህመም ወቅት አመጋገብ

8. የኩላሊት መድከም ምንድነው?

ኩላሊታችን ሰዉነታችን ተግባሩን በተገቢ መንገድ ማከናወን እንዲችል የሚያበረክተው በርካታ አስተዋጽኦ አለው። ከሰዉነታችን ውስጥ የሚወጣውን ቆሻሻ አጣርቶ በፈሳሽ መልክ ለማስወገድ ያግዘናል። በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘውን የውሀ እና ንጥረነገር ለአብነት የሶድየም፣ፖታሲየም እና የካልሲየም መጠንን ለማስተካከል ይረዳናል። በተጨማሪም ሰውነታችን ውስጥ ከመጠን በላይ ያለውን የአሲድ እና አልካላይን መጠን ለመጠበቅ ያግዘናል። እነዚን ሥራዎች ማከናወን ሲያዳግተው የኩላሊት ድክመት ተብሎ ይጠራል። 

የኩላሊት ድክመትን እንዴት መመርመር ይቻላል?

ሁለቱ ኩላሊቶቻችን ሲደክሙ በደም ውስጥ የሚገኘው የቆሻሻ መጠን ከፍ ይላል። ይህንን ደረጃ ለመለካት በጣም ቀላሉ በላብራቶሪ ውስጥ የሚደረገው ምርመራ የክሬቲንን እና የዩሪያን መጠን ምዘና ነው። የኩላሊትን ጤንነት ወይም ግሎሜሩላር ማጣሪያ መጠን የሴረም ክሬቲንን ደረጃ በመጠቀም ለማወቅ የሚያስችሉን የተዘጋጁ ቀምሮችን በኢንተርኔት ወይም በአንዳንድ አፕሊኬሽኖች ላይ በቀላሉ ማግኘት እንቻላል። በተጨማሪም ትንሽ የክሬቲንን መጠን መጨመር የኩላሊት ተግባር በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን ያሳየናል። 1.6 ሚሊግራም / ዴሲሊትር የክሬቲንን ደረጃ ብቻ 50 በመቶ በላይ የኩላሊት ሥራ መጥፋትን ሊያመለክት ይችላል።

የአንዱ ኩላሊት ድክመት ብቻ ወደ አጠቃላይ የኩላሊት ድክመት ሊዳርግ ይችላል?

ሊዳርግ አይችልም። ከሁለቱ አንዱ ኩላሊት ብቻ ሲደክም ወይም በቀዶ ጥገና ሲወጣ አጠቃላይ የኩላሊት ተግባር ላይነካ ወይም ጉልህ የሆነ ችግር ላያጋጥመው ይችላል። የቀረው ኩላሊት የሁለቱን ኩላሊቶች ሥራ ጫና ሊወስድ ወይም ሊረከብ ይችላል።

የኩላሊት ድክመት በተፈጥሮ አጣዳፊ ወይም ሥር የሰደደ ተብሎ ለሁለት ሊከፈል ይችላል

አጣዳፊ የኩላሊት ድክመት

  • በኩላሊት ላይ ከባድ ጉዳት በጥቂት ቀናት ውስጥ ሲከሰት በአጭር ጊዜ የኩላሊታችን ሥራ የማከናወን አቅም ሊቀንስ ወይም ሊከሸፍ ይችላል።
  • ይህ የተግባር ማሽቆልቆል ቀደም ሲል አጣዳፊ የሆነ የኩላሊት ድክመት (.አር.ኤፍ) ተብሎ ይጠራ የነበረ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ በፊት አጣዳፊ የኩላሊት ጉዳት ተብሎ እንዲጠራ ተወስኗል።
  • ይህ ዓይነት የኩላሊት ችግር አብዛኛውን ጊዜ ጊዜያዊ ነው። የኩላሊት ተግባራት በትክክለኛ የህክምና መንገድ አብዛኛው ህሙማን ውስጥ ወደ መደበኛ ሥራ ሊመለስ ይችላል።

ሥር የሰደደ የኩላሊት ድክመት

  • ከብዙ ወራቶች እስከ ዓመታት ድረስ ቀስ በቀስ እያደገ የሚሄድ እና የማይ ቀለበስ የኩላሊት ክሽፈት (ቀደም ሲል ሥር የሰደደ የኩላሊት መታወክ በመባል ይታወቃል የነበረው) ሥር የሰደደ የኩላሊት ድክመት ይባላል።
  • ይህ የላቀ እና ለሕይወት አስጊ የሆነ የህመም ደረጃ የመጨረሻ ደረጃ የኩ ላሊት ህመም ይባላል።