Read Online in Amharic
Table of Content
መግቢያ እና ይዘቶች
መሰረታዊ መረጃ
የኩላሊት መድከም
ሌሎች ዋና ዋና የኩላሊት ህመሞች
የኩላሊት ህመም ወቅት አመጋገብ

9. አጣዳፊ የኩላሊት መድከም

አጣዳፊ የኩላሊት ጉዳት ምንድን ነው?

በአጣዳፊ የኩላሊት ጉዳት (ቀደም ብሎ አጣዳፊ የኩላሊት ሽንፈት ተብሎ የሚጠራው) ውስጥ የኩላሊት ተግባራት መቀነስ ወይም ማጣት በአጭር ጊዜ ውስጥ ይከሰታል (ከሰዓታት ከቀናት ወይም ከሳምንታት በላይ)

ይህ ጊዜያዊ እና አብዛኛውን ጊዜ የሚመለስ የኩላሊት ችግር ነው።

የአጣዳፊ ኩላሊት ጉዳት መንስኤው ምንድን ነው?

የአጣዳፊ ኩላሊት ጉዳት ብዙ ምክንያቶች አሉ። የተለመዱት መንስኤዎች የሚያካትቱት:

  1. የኩላሊት የደም አቅርቦትን በተቅማጥ ፣ በደም ማጣት ፣ በቃጠሎ ወይም በደም ግፊት መውረድ ምክንያት ሲቀንስ።
  2. ከባድ ኢንፌክሽን ከባድ ህመም ወይም ከከባድ ቀዶ ህክምና በኋላ።
  3. የሽንት መተላለፊያው ቧንቧ በድንገት ሲዘጋ።ለዚህ ችግር መከሰት በጣም የተለመደው መንስኤ የኩላሊት ጠጠር ነው።
  4. ሌሎች ምክንያቶች: ወባ ፣ ሌፕቶስፓይሮሲስ ፣ የእባብ ንክሻ ፣ የተወሰኑ የኩላሊት ህመሞች እርግዝና ውስብስብ ችግሮች የአንዳንድ መድኃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳቶች፣ ለራዲዮ ኮንትራስት የምንጠቀመው መድሀኒት እና የተወሰኑ ከእፅዋት የተሰሩ ቅመሞች ናቸው።

የአጣዳፊ ኩላሊት ጉዳት ምልክቶች

በአጣዳፊ ኩላሊት ጉዳት ውስጥ የኩላሊት ሥራ በድንገት በመቋረጡ ፣ የቆሻሻ ምርቶች በፍጥነት በመከማቸታቸው እና የፈሳሽ ና ኤሌክትሮላይት መጠን መዛባት ምክንያት ታካሚው ጉልህ የሆኑ የሕመም ምልክቶች ይታይበታል። የሕመሙ ምልክቶች ዓይነት እና ክብደታቸው ከህመምተኛ እስከ ህመምተኛ ይለያያሉ። እነዚህም የሚከተሉትን ያካትታሉ:

  1. የኩላሊት ድክመት የሚያስከትሉ ተጓዳኝ ህመሞች ምልክቶች (ተቅማጥ  ደም መፍሰስ፣ ትኩሳት ብርድ ብርድ ማለት)
  2. የሽንት መጠን መቀነስ (የሽንት መጠን በጥቂት ታካሚዎች ውስጥ መደበኛ ሆኖ ሊቆይ ይችላል)
  3. በቁርጭምጭሚት ወይም በእግር እብጠት እና በፈሳሽ መጠን መብዛት ምክንያት ክብደት መጨመር።
  4. የምግብ ፍላጎት ማጣት ማቅለሽለሽ ማስታወክ የጭንቀት መንቀጥቀጥ ድካም ግድየለሽነት እና ግራ መጋባት።
  5. ከባድ እና ለሕይወት አስጊ የሆኑ ምልክቶች እንደ ትንፋሽ ማጣት ፣ የደረት ህመም ፣ ንዝረት ወይም ኮማ ፣ የደም ማስታወክ እና በከፍተኛ የደም ፖታስየም መጠን የተነሳ ያልተለመደ የልብ ምት ናቸው።
  6. የከባድ የኩላሊት ድክመት የመጀመሪያ ደረጃ ላይ አንዳንድ ህመምተኞች ምንም አይነት ምልክት ላያሳዩ ይችላሉ። በሌላ ጉዳይ ምክንያት የደም ምርመራ በሚደረግበት ጊዜ ህመሙ በአጋጣሚ ሊገኝ ይችላል።

የአጣዳፊ ኩላሊት ጉዳት ምርመራዎች

ብዙ የአጣዳፊ ኩላሊት ህሙማን ምልክት ላያሳዩ ወይም ልዩ ያልሆኑ ምልክቶች (ለምሳሌ: ድካም፣ከባድ ያልሆም) ብቻ ሊያሳዩ ይችላሉ። ስለሆነም በማንኛውም ሁኔታ አንድ ሰው ምልክቶችን በሚመለከት ጊዜ ወይም ትንሽ ጥርጣሬ ካለው ሁል ጊዜ አጣዳፊ የኩላሊት ጉዳት በመጠርጠር ምርመራ ማድረግ አለበት።

ምርመራው በደም ምርመራ (በሴረም ክሬቲኒን እና በደም ዩሪያ ውስጥ መነሳት) ፣ በሽንት መጠን መለኪያ ፣ በሽንት ምርመራ እና በአልትራሳውንድ የሚረጋገጥ ነው። አጣዳፊ የኩላሊት ጉዳት ዝርዝር ታሪክ ባላቸው ታካሚዎች ላይ የህመሙን ምክንያቶች ፣ ችግሮች እና መባባስን ለመገምገም የተለያዩ ምርመራዎች ይከናወናሉ።

የአጣዳፊ ኩላሊት ጉዳት ሕክምና

በአብዛኛው ታካሚዎች ውስጥ ትክክለኛ ህክምና አጣዳፊ የኩላሊት ጉዳትን ሊቀለብስ ይችላል።

ሆኖም ለከባድ የኩላሊት ችግር ምርመራ መዘግየት ወይም ተገቢ ያልሆነ ህክምና ማግኘት ለሕይወት አስጊ ሊሆን ይችላል።

የአጣዳፊ የኩላሊት ጉዳት ህክምና ዋና ዋና መንገዶች የሚከተሉት ናቸው:

  1. የኩላሊት ጉዳት መንስኤዎችን ማስተካከል ወይም ማከም
  2. የመድሐኒት ሕክምና እና ድጋፍ ሰጪ ሕክምናዎች
  3. የአመጋገብ ምክር
  4. ኩላሊት እጥበት

1. የኩላሊት ጉዳት መንስኤዎችን ማከም

  • የኩላሊት ጉዳት መንስኤዎችን ለይቶ ማስተካከል ወይም ማከም ለከባድ የኩላሊት ጉዳት ህክምና በጣም አስፈላጊ ነው።
  • አንዳንድ የኩላሊት ህመም መንስኤዎችን ማከም የኩላሊትን ድክመት ለመከላከል ወሳኝ ነው። እነዚህ መንስኤዎች የደም ግፊት ኢንፌክሽን  የሽንት ቧንቧ መዘጋት እና የመሳሰሉት ሲሆኑ ምክንያቶቹን ማስተካከል ከኩላሊት ውድቀት ለመዳን አስፈላጊ ነው።
  • እንዲህ ዓይነቱ ሕክምና በኩላሊቱ ላይ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ ይከ ላከላል። በተጨማሪም እንዲድን ያደርጋል።

2. የመድሐኒት ሕክምና እና ድጋፍ ሰጪ ሕክምናዎች

  • ግቡ ኩላሊቶችን መደገፍ እና ማንኛውንም ውስብስብ ችግሮች መከላከል ወይም ማከም ነው።
  • ኢንፌክሽኖችን ማከምና መከላከል፣ ለኩላሊት መርዛማ እና አደገኛ የሆኑ መድኃኒቶችን ማስወገድ ይኖርብናል።
  • በተጨማሪም እንደ ፉሮሰማይድ ያሉ ሽንት ማሸኛ መጠቀም የሽንት መጠን እንዲጨምር እና በሰውነት ውስጥ በተለይም የሳንባ ትንፋሽ ማነስ መንስኤ የሆነውን ፈሳሽ ሳንባ ውስጥ እንዳይከማች ይረዳል።
  • ደጋፊ ህክምናዎች:-ዝቅተኛ ወይም ከፍተኛ የደም ግፊትን ማቅለሽለሽን ፣ ማስታወክን ፣ የደም ፖታስየም መጠንን ፣ ትንፋሽ ማጣትን ለመቀነስ እና ንዝረትን ለመከላከል ወይም ለመቆጣጠር የሚሰጡ መድሀኒቶችን መጠቀም።

3. የአመጋገብ ምክሮች

  • ትክክለኛ የአመጋገብ ገደቦችን ማድረግ የአስቸኳይ የኩላሊት ጉዳት ምል ክቶችን ወይም ውስብስቦችን ለመከላከል ወይም ለመቀነስ ይረዳል።
  • የፈሳሽ መጠንን መለካት:በየቀኑ የምንወስደው ፈሳሽ የሽንት መጠን እና የሰውነት ፈሳሽ ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት የታቀደ መሆን አለበት። አብዛኛውን ጊዜ እብጠትን እና ትንፋሽ ማጠርን ያሉ ውስብስብ ነገሮች ለመከላከል ፈሳሽ መገደብ አስፈላጊ ነው።
  • የፖታስየም መጠን መገደብ። በደም ውስጥ ያለው ከፍተኛ የፖታስየም መጠን (ሃይፐርካላሚያ) በጣም ከባድ እና ለሕይወት አስጊ የሆኑ ችግሮችን ሊያስከትል ስለሚችል በፖታ ስየም የበለፀጉ ምግቦችን ለምሳሌ ፍራፍሬዎችን ፣ የፍራፍሬ ጭማቂዎ ችን ደረቅ ፍራፍሬዎችን ወዘተ ማስወገድ አለብን።
  • የጨው መጠን መገደብ። የጨው መገደብ ጥማትን ፣ እብጠትን ፣ ከፍተኛ የደም ግፊት እና ትንፋሽ ማጣት ያሉ ውስብስቦችን ለመቀነስ ይረዳል።
  • በቂ ምግብ እና ካሎሪ አቅርቦት ያስፈልጋል።

4. ኩላሊት እጥበት

ኩላሊት እጥበት ኩላሊቶቹ ተግባሮቻቸውን እስኪያገግሙ ድረስ የኩላሊት ሥራን በአጭር ጊዜ ውስጥ በመተግበር(ሰው ሰራሽ ኩላሊት)ይረዳል። ለአንዳንድ ታካሚዎች ኩላሊታቸው እስኪያገግም ድረስ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።

ኩላሊት እጥበት ምንድነው?

  • ኩላሊት እጥበት የተጎዳውንየኩላሊት ተግባር ተክቶ ለመተግበር የሚያ ግዝ ሰው ሰራሽ ሂደት ነው።ከባድ የኩላሊት ችግር ላለባቸው ሰዎች ህይ ወትን ለማቆየት ይረዳል።
  • የኩላሊት እጥበት አስፈላጊ ተግባራት ከሰውነታችን የሚወጣውን እዳሪ ወይም ቆሻሻዎችን ለማስወገድ ፣ ከመጠን በላይ ሰውነት ውሰጥ የሚገ ኘውን ፈሳሾች ማስወገድ የአሲድ መጠንን እና የንጥረነገር ሁከት ለማ ስተካከል ነው።
  • ሁለት ዋና ዋና ኩላሊት እጥበት ዓይነቶች አሉ። እነሱም ሄሞዲያሲስ እና ፔሪቶናል ዲያሊስሲስ ተብለው ይታወቃሉ።
  • የአጣዳፊ ኩላሊት ጉዳት አብዛኛውን ጊዜ በተገቢው ህክምና ሙሉ በሙሉ ይድናሉ።

አጣዳፊ በሆነ የኩላሊት ጉዳት ውስጥ ኩላሊት እጥበት መቼ ይፈለጋል?

ኩላሊት እጥበት በቂ ጥንቃቄ የተሞላበት ህክምና ኖሮም የህመም ምልክቶች እየጨመሩ እና ውስብስብ ችግሮች በሚከሰቱባቸው ከባድ የኩላሊት ጉዳት ባጋጠማቸው ሕመምተኞች ላይ ያስፈልጋል። ከባድ ሰውነት ውስጥ የሚገኘው ፈሳሽ መጠን መጨመርን ፣ መቆጣጠር የማይቻል ሀይፐርካሊሚያ እና ከባድ የአሲድ መጠን መጨመር የኩላሊት እጥበት ወይም ዲየሊሲስ የማያስፈልጋቸው የአጣዳፊ ኩላሊት ጉዳት ምልክቶች ናቸው።

አጣዳፊ በሆነ የኩላሊት ውስጥ የኩላሊት እጥበት ሕክምና ለምን ያህል ጊዜ ያስፈልጋል?

  • የተወሰኑ የኩላሊት ጉዳት ያላቸው ህመምተኞች የኩላሊት ተግባር እስኪ ያገግሙ ድረስ ጊዜያዊ ኩላሊት እጥበት (ሄሞዲያሲስ ወይም ፔሪቶናል ዳያሊስስ) ድጋፍ ይፈልጋሉ።
  • አጣዳፊ የኩላሊት ጉዳት ያላቸው ህመምተኞች ብዙውን ጊዜ 1-4 ሳም ንታት ውስጥ ያገግማሉ። በዚህ ጊዜ ኩላሊት እጥበት ድጋፍ ሊፈለግ ይችላል።
  • በአጣዳፊ የኩላሊት ጉዳት ውስጥ የኩላሊት እጥበት ሕክምና ብዙውን ጊዜ ጊዜያዊ ነው። ይህም የሚሆነው ኩላሊታቸው ከደረሰበት ጉዳት መቀልበስ ስለሚችል ነው። ብዙውን ጊዜ ህሙማን የቋሚ የኩላሊት እጥበትን በመፍራት ኩላሊት እጥበትን በማዘግየት በከፍተኛ የኩላሊት ጉዳት ሕይወትን አደጋ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ።

አጣዳፊ የኩላሊት ህመም መከላከል

አጣዳፊ የኩላሊት ጉዳትን እንዴት መከላከል ይቻላል?

  • የኩላሊት ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ ህመሞች ቀደም ብሎ ማጣራት። በተጨማሪም ተጓዳኝ ህመሞች ባሉባቸው ታካሚዎች ውስጥ የኩላሊትን ክንውን አዘውትሮ መመርመር ያስፈልጋል።
  • ያላግባብ የደም ግፊት መቀነስ ወይም መጨመርን መከላከል እና ፈጣን እርማት ማድረግ።
  • ኩላሊት የሚጎዱ መድኃኒቶችን ማስወገድ።
  • ፈጣን የኢንፌክሽን እና የሽንት መጠን መቀነስን መቆጣጠር።