Read Online in Amharic
Table of Content
መግቢያ እና ይዘቶች
መሰረታዊ መረጃ
የኩላሊት መድከም
ሌሎች ዋና ዋና የኩላሊት ህመሞች
የኩላሊት ህመም ወቅት አመጋገብ

12. ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም ሕክምና

ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም ሕክምና

 ሦስቱ ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ሕክምናዎች የመድኃኒት ሕክምና፣የኩላሊት እጥበት ወይም ንቅለ ተከላ ናቸው።

  • ሁሉም የህመሙ ተጠቂዎች በመጀመሪያ የመድኃኒት ሕክምና ይሰጣቸ ዋል። (መድኃኒት፣አመጋገብን የተመለከቱ ምክሮች እና የቅርብ ክትትል)
  • በስር የሰደደ የኩላሊት ህመም የመጣ ከባድ የሆነ ጉዳት የኩላሊት እጥበት ወይም የንቅለ ተከላ ያስፈልገዋል።

የመድኃኒት ሕክምና

ለስር ሰደድ የኩላሊት ህመም የመድኃኒት ሕክምና በጣም ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?

ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ፈውስ የለውም።ከፍተኛ የሆነው ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ደግሞ ሕይወትን ለማስቀጠል የኩላሊት እጥበት ወይም ንቅለተከላ ያስፈልገዋል። ሕንድ ውስጥ ባለው ከፍተኛ ዋጋ እና የአገልግሎት እጥረት ምክንያት የኩላሊት እጥበት እና ንቅለ ተከላ የሚያገኙት ሕሙማን 5-10% ብቻ ሲሆኑ የተቀሩት ምንም ሕክምና ሳያገኙ ሕይወታቸው ያልፋል። ስለዚህም ቀደም ብሎ ህመሙን ማግኘት እና ጥንቁቅ የሆነ የመድኃኒት ሕክምና ማድረግ ብቸኛ አዋጪ እና ውድ ያልሆነ የበሽታው መፍትሔ ሲሆን የኩላሊት እጥበትንና ንቅለ ተከላን አስፈላጊነትም ያዘገያል።

ለምን ብዙ ሰዎች ከመድኃኒት ሕክምናው የሚገኘውን ጥቅም ሳያገኙ ቀሩ?

በመጀመሪያዎቹ የኩላሊት ህመም ደረጃዎች ላይ ትክክለኛውን ሕክምና መጀመር በጣም ጠቃሚ ነው። አብዛኞቹ ሕሙማን ትክክለኛውን ሕክምና በመጀመሪያው ደረጃዎች ላይ ካገኙ ከምልክቶች ነጻ ይሆናሉ ወይም የጤነኝነት ስሜት ይሰማቸዋል። በዚህም ምክንያት ብዙ ሕሙማን እና ቤተሰቦቻቸው የበሽታውን አሳሳቢነትን በመዘንጋት መድኃኒት መቋረጥ እና የአመጋገብ ገደብን መተው ያሳያሉ። ሕክምና ማቋረጥ የኩላሊትን በሽታ በፍጥነት አባብሶ ውድ የሆነ የኩላሊት እጥበት እና የንቀለተከላ ህክምና እንዲደረግ የግድ ይላል።

በስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ውስጥ የመድኃኒት ሕክምና ግቦች ምንድን ናቸው?

ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ፈውስ የሌለው በጊዜ ሂደት እየተባበሰ የሚሔድ ሁኔታ ነው።የመድኃኒት ሕክምና ግቦች የሚከተሉት ናቸው፡-

  1. የህመሙን የመባባስ ሒደት መቀነስ
  2. የህመሙን አምጪ ምክንያቶችንና አባባሽ ሁኔታዎች ማስወገድ
  3. ምልክቶቹን ማስታገስ እና ውስብስብ ውጤቶቹን ማከም
  4. ለልብ እና ለደም ቧንቧ ህመም ተገላጭነትን መቀነስ
  5. የኩላሊት እጥበትን እና ንቅለ ተከላን ማዘግየት

ለተለያዩ ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ደረጃዎች የሚጠቅሙ የሕክምና ስልቶች ምንድን ናቸው?

ለተለያዩ የህመሙ ደረጃዎች የሚጠቅሙ የሕክምና ስልቶች እና የሚመከሩ እርምጃዎች

የህመሙ ደረጃዎች

የሚመከሩ እርምጃዎች

ሁሉም ደረጃዎች

  • መደበኛ ክትትል እና ቁጥጥር
  • የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ እና አጠቃላይ የጥንቃቄ እርም ጃዎች

1

  • ያህመሙን መባባስ ለመቀነስ ሕክምና ማድረግ
  • ሕሙማንን ስለ ህመሙ አያያዝ ማስተማር
  • አብረው የሚመጡ ሁኔታዎችን ማከም፣የልብን እና የደም ቧንቧ ህመም ተጋላጭነትን መቀነስ

2

  • ሒደቱን መገመት፤አብረው የሚመጡን ሁኔታዎችን ማከም

3

  • ውስብስብ ችግሮችን መገምገም እና ማከም፣ወደ ኩላሊት ስፔሻሊስት ሐኪም መላክ

4

  • ሕሙማንን ስለ ኩላሊት መተኪያ አማራጮች ማስተማር እና ለኩላሊት መተካት ሕክምና መዘጋጀት

5

  • በኩላሊት እጥበት ወይም በንቀለ ተከላ የኩላሊትን ስራ መተካት

 

ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም የመድኃኒት ሕክምና 9 የእርምጃ ዕቅድ ደረጃዎች

1. መሠረታዊ መነሻውን መቆጣጠር

ከስር ያሉትን መሠረታዊ መነሻዎችን ማወቅ እና ማከም ስር የሰደደን የኩላሊት ህመምን መባባስ ለመከላከል፣ለማዘግየት ወይም ለመመለስ ሊጠቅም ይችላል።

  • ስኳር ህመም እና ደም ግፊት
  • የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ወይም መዘጋት
  • ግሎሚሩሎኔፍራይተስ ፣የኩላሊት ደም ቧንቧ ህመም ፣የሕመም ማስታ ገሻ ሲበዛ የሚያመጣው የኩላሊት ህመም።

2. ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም መባባስ ለመቀነስ የሚጠቅሙ ስልቶች

ሐኪማችሁከታች እንደተጠቀሰው የበሽታውን መባባስ ለመቀነስ አስፈላጊ እና ውጤታማ እርምጃዎችን ሊወስድ ይችላል።

  • ጥብቅ የሆነ ከፍተኛ የደም ግፊት ቁጥጥር እና
  • የፕሮቲን ገደብ
  • ሊፒድ የሚቀንስ ሕክምና
  • የደም ማነስ ማስተካከያ

3. ደጋፊ እና በምልክቶች ላይ የተመሠረተ ሕክምና

  • የሽንት መጠንን ለመጨመር እና እብጠትን ለመቀነስ የሚሰጥ ዋተረ ፒል
  • ማቅለሽለሽን፣ ወደ ላይ ማለትን እና የጨጓራ አለመመቸት ስሜትን ለመ ቆጣጠር የሚረዱ መድኃኒቶች
  • ካልሽየም ፣ፖስፔት ባይንደርስ ፣አክቲቭ ቪታሚን እና ከስር የሰደደ የኩ ላሊት ህመም ጋር ተያያዞ የሚመጣ የአጥንት ህመምን ለማስተካከል የሚሆኑ ሌሎች መድኃኒቶች
  • ዝቅተኛ ሄሞግሎቢንን (ደም ማነስ) በአይረን፣ቪታሚኖች እና የኤሪትሮፖ ይቲን ኢንጀክሽን ማስተካከል
  • የልብ እና የደም ቧንቧ ክስተቶችን መከላከል። የሚቃረነው ነገር ከሌለ በቀር በየቀኑ የሚወስድ አስፕሪንን መጀመር

4. የሚቀየሩ ምክንያቶችን መቆጣጠር

የኩላሊትን ህመም መጠንን የሚያባብሱ እና መመለስ የሚችሉ ምክንያቶችን መፈለግ እና ማከም። እነዚህ ተመላላሽ ምክንያቶችን ማስተካከል የኩላሊት ድክመትን ሊያስተካክል እና የኩላሊትን ስራ ወደ ቋሚ እርከን ሊመለስ ይችላል። እነዚህ ተመላላሽ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው።

  • የፈሳሽ መጠን መቀነስ
  • በመድኃኒቶች የመጣ የኩላሊት ድክመት
  • ኢንፌክሽንና እና የልብ ድካም

5. ውስብስብ ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ውጤቶችን መለየት እና ማከም

የበሽታው ውስብስብ ውጤቶች በጊዜ መመርመር እና መታከም አለባቸው። ከባድ የፈሳሽ ጥርቅም፤ከፍተኛ የደም ፖታሽየም መጠን(ፖታሽየም 6 mEQ/l በላይ) ከፍተኛ የሆነ የኩላሊት ድክመት በልብ፣በአንጎል እና ሳንባ ላይ የሚያስከትለው ከባድ የሕመም ውጤቶች ትኩረት የሚፈልጉ የተለመዱ ውስብስብ ውጤቶች ናቸው።

6. የአኗኗር ዘይቤ ማሻሻያዎች እና አጠቃላይ የጥንቃቄ እርምጃዎች

እነዚህ እርምጃዎች አጠቃላይ ተጋላጭነትን ለመቀነስ በጣም ጠቃሚ ናቸው

  • ትምባሆ ማጨስ ፈጽሞ ማቆም
  • ጤናማ የሆነ የሰውነት ክብደትን ተቆጣጥሮ መጠበቅ፣መደበኛ የሠውነት እንቅሳቃሴ ማድረግ እና በመደበኛነት ንቁ አቋም መያዝ
  • የአልኮል መጠጥን መቀነስ
  • ጤናማ የሆነ የአመጋገብ ሥርዓትን መከተል እና የምግብ ጨውን መቀነስ
  • መድኃኒቶች መወሰድ ያለባቸው በሐኪም ሲታዘዙ ብቻ መሆን አለበት።እ ንደ ኩላሊቱ በሽታው ከባድነት ሊስታካከሉ ይችላሉ።
  • በኩላሊት ስፔሻሊስት እንደታዘዙ መደበኛ ክትትሎች እና ሕክምናዎችን ማድረግ

7. የአመጋገብ ገደቦች

በኩላሊት ህመም አይነት እና እንደ ክብደቱ መጠን የአመጋገብ ገደቦች ያስፈልጋሉ።

ጨው(ሶድየም)፡- ከፍተኛ የደም ግፊትን እና የሠውነት እብጠትን ለመከላከል የጨው አወሳሰድ ገደቦች ይመከራሉ። የጨው ገደቦች እነዚህን ያጠቃልላሉ፤በምግብ ገበታ ላይ ጨው አለመጨመር እና ጨው የሚበዛባቸውን እንደ ፈጣን ምግቦች ፣ፓፓድ እና ፒክልስ ያሉ ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ በተጨማሪም የታሸጉ ምግቦች አጠቃቀምን በእጅጉ መቀነስ ያስፈልጋል።

የፈሳሽ አወሳሰድ፡- በስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ተጠቂዎች ዘንድ መጠኑ የቀነሰ ሽንት የሠውነት ማበጥን እና በከባድ ጊዜዎች ላይ ደግሞ ትንፋሽ ማጣትን ሊያስከትል ይችላል፤በመሆኑም ለሁሉም የሠውነት እብጠት ላለባቸው ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ተጠቂዎች የፈሳሽ አወሳሰድን መገደብ ይመከራል።

ፖታስየም፡- ብዙ ጊዜ በስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ሕመምተኞች ላይ የደም ፖታስየም መጠን መጨመር ይታያል። ይኸም በልብ ላይ ለሕይወት አስጊ የሆኑ ሁኔታዎችን ያመጣል። ይህን ለመከላከል በሐኪም በሚታዘዘው መሠረት ፖታስየም የበዛባቸውን ምግቦች(ደረቅ ፍራፍሬዎች፣የካካዋ ውሃ፣ድንች፣ብርቱካን፣ሙዝ፣ቲማቲም የመሳሰሉት)መገደብ ያሰፈልጋል።

ፕሮቲን፡- ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ያለባቸው ሕሙማን የኩላሊት ጉዳትን ሊያባብሱ የሚችሉ ከፍተኛ ፕሮቲን ያላቸውን ምግቦች መመገብ ማስወገድ አለባቸው

8. ለኩላሊት መተካት ሕክምና መዘጋጀት

  • ህመሙ በምርምራ እንደተገኘ ዋና ያልሆነ ክንድ ላይ የሚገኙትን የደም መላሽ ቧንቧዎች መጠበቅ
  • እዚሁ ክንድ ላይ ያሉትን የደም መላሽ ቧንቧዎች ደም ለመውሰድ አለመ ጠቀም
  • የኩላሊት የመሥራት አቅም እየከፋ ሲሄድ እና የመጨረሻ ደረጃ የኩላ ሊት ህመም ሲቃረብ የኩላሊት እጥበት ወይም የንቅለ ተከላ ሕክምና ይታዘዛል። እንደ በሽታው የመድኃኒት አስፈላጊነት እና እንደ ሕመምተኛው ፍለጎት ተጨማሪ የሕክምና አማራጮችን የኩላሊት ስፔሻሊስቱ ከሕመም ተኞቹ እና ቤተሰቦቻቸው ጋር ይወያያል። የኩላሊት እጥበት ዘዴ በድም ሥር እና በሆድ በኩል ኩላሊት እጥበትን ያጠቃልላል።
  • የኩላሊት እጥበት ለህክምና ከተመረጠ፤ ሕመምተኞች እና ቤተሰቦቻ ቸው ስለ ደም ወሳጅ እና መላሽ ቧንቧ አገናኝ ፊስቱላ መማር እና ቢቻል ከኩላሊት እጥበቱ መጀመር ከ6-12 ወራት በፊት እንዲያሰሩ መመከር አለ ባቸው።
  • ስር የሰደደ የኩላሊት ታማሚ ከኩላሊት እጥበት መጀመር በፊት የኩላ ሊት ንቅለ ተከላ ለማግኘት ብቁ ሊሆን ይችላል። እዚህ ጋር ታማሚው የኩ ላሊት ልገሳ የሚያገኘው በህይወት ካለ ሰው መሆኑን ማወቅ ተገቢ ነዉ።
  • በመጀመሪያዎቹ ስር ሰደድ፤ የኩላሊት ህመም ደረጃዎች ላይ የሄፓታቲስ ክትባት መስጠት በኩላሊት እጥበት ጊዜ ወይም ንቅለ ተከላ ጊዜ የሚ ኖረውን የሄፐታቲስ ቢ ኢንፌክሽን ተጋላጭነት ይቀንሳል። 4 ደብል መጠን የሪኮምቢናንት ሄፐታይተስ ክትባት በትክሻ ጡንቻ አካባቢ ክንድ ላይ 01 እና 6 ወራት ውስጥ መሰጠት አለበት።

9. ወደ ኩላሊት ስፔሻሊስት መላክ

ስር የሰደደ የኩላሊት ህመምተኛን ከጽኑ ሕመም እና ሞት ለመጠበቅ በጊዜ ወደ ኩላሊት ስፔሻሊስት መላክ እና ቅድመ የኩላሊት እጥበት ትምህርት መስጠት ያስፈልጋል። ህመምተኛውን በጊዜ ወደ ስፔሻሊት መላክ የህመሙን መባባስ ብሎም ወደ መጨረሻ ደረጃ የኩላሊት ህመም የመቀየሩን ዕድል ቀንሶ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ሕክምና አስፈላጊነትን እንዲዘገይ ሊያደርግ ይችላል።

ስር የሰደደ የኩላሊት ህመምን ለመከላከል ወይም መባባሱን ለማዘግየት የትኛው የሕክምና አይነት ተመራጭ ነው?

ስር የሰደደ የኩላሊት ህመምን ያስከተለዉ ምክንያት የትኛዉም ቢሆን፤ ጥብቅ የሆነ የከፍተኛ ደም ግፊት ቁጥጥር ዋነኛው ህመሙን ለመከላከል እና መባባሱን ለመቀነስ የሚጠቅም የሕክምና ዘዴ ነው። በቁጥጥር ስር ሰደድ ያልሆነ ከፍተኛ የደም ግፊት ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም በፍጥነት እንዲባባስ እና እንደ ልብ ድካም እና ስትሮክ የመሳሰሉ ውስብሰብ ችግሮች እንዲመጡ ያደርጋል።

የትኞቹ መድኃኒቶች ናቸው ከፍተኛን የደም ግፊት ለመግታት የሚጠቅሙት?

የኩላሊት ስፔሻሊስቱ ወይም አጠቃላይ ሀኪሙ ከፍተኛ የደም ግፊትን ለመግታት የሚጠቅሙትን ተገቢ መድኃኒቶች ይመርጣል።

አንጅዮቴንሲን ኮንቨርቲንግ እንዝያም ኢንሂቢተርስ አንጅዮቴንሲን ሪሰፕተር ብሎከርስ ካልሽየም ቻናል ብሎከርስ እና ሽንት ማሸኛ የተለመዱ የከፍተኛ ደም ግፊት መድኃኒቶች ናቸው።

አንጅዮቴንሲን ኮንቨርቲንግ እንዝያም ኢንሂቢተርስ እና አንጅዮቴንሲን ሪሰፕተር ብሎከርስ በቅድሚያ የሚመረጡ ደም ግፊትን ለመቀነስ የሚረዱ እንዲሁም የኩላሊትን የጉዳት ሂደትን በመቀነስ ኩላሊትን የሚጠብቁ መድኃኒቶች ናቸው።

በስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ውስጥ የደም ግፊት ቁጥጥር ዓላማ ምንድን ነው?

የደም ግፊት መጠንን 130/80 ሚሜ ሜርኩሪ በታች ማድረግ ይመከራል።

በስር ሰደደ የኩላሊት ህመም ውስጥ የደም ግፊትን ለመከታተል እና መቆጣጠር የበለጠ የሚጠቅመው የትኛው መንገድ ነው?

አልፎ አልፎ የሚደረግ የሀኪም ክትትል የደም ግፊትን ሁኔታ ለማወቅ ያስችላል። ነገር ግን፤ በስር የሰደደ የኩላሊት በሽታ ውስጥ የደም ግፊት መለኪያን ገዝቶ በመደበኛነት ቤት ውስጥ መለካት የደም ግፊትን ለመከታተል እና ለመቆጣጠር የበለጠ ይረዳል። የደም ግፊት መመዝገቢያ ሪከርድ ተጠቅሞ የደም ግፊት ልኬትን መመዝገብ ደግሞ ሀኪሙ የመድኃኒት መጠንን እና የሚወሰድበትን ጊዜ እንዲያስተካክል ይረዳዋል።

ስር የሰደደ የኩላሊት ህመምተኞች እንዴት ሽንት በሚያሽኑ መድኃኒቶች ሊጠቀሙ ይችላሉ?

ሀኪሞች የሽንት መጠንን ለመጨመር እና የሰውነት እብጠትን ቀንሶ የትንፋሽ ማጠርን ለማስተካከል እነዚህን መድኃኒቶች ሊያዙ ይችላሉ። ነገር ግን እነዚህ መድኃኒቶች የሽንት መጠንን ከመጨመር ባለፈ የኩላሊት ስራን እንደማያሻሽሉ መታወስ አለበት።

በስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ውስጥ ለምን ደም ማነስ ይከሰታል እና ህክምናውስ እንዴት ነው?

ኩላሊቶች በተገቢው ሁኔታ በሚሰሩ ጊዜ የአጥንት መቅኔ ቀይ የደም ሴሎች እንዲያመርት የሚረዳ ኢሪትሮፖይቲን የሚባል ሆርሞን ያመነጫሉ። በስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ጊዜ የኩላሊት የመስራት አቅም ሲቀነስ የኢሪትሮፖይቲንም ምርት ይቀንሳል ይኼም ለደም ማነስ ይዳርጋል።

የአይረን ኪንኖቸ፣ቫይታሚኖች አንዳንዴም በደም ስር የሚሰጥ አይረን በመጀመሪያ ደረጃ በስር የሰደደ የኩላሊት ሕመም ምክንያት ለሚመጣ ደም ማነስ ይሰጣሉ። ከባድ ለሆነ ወይም በመድኃኒት ለማይመለስ ደም ማነስ የአጥንት መቅኔ ኦክስይጅን የሚሸከሙ ቀይ ደም ሴሎች እንዲሰራ የሚረዳ ሰው ሰራሽ ኢሪትሮፖይቲን በኢንጀክሽን መልክ መሰጠት ያስፈልጋል። የኢሪትሮፖይቲን ኢንጀክሽን አስተማማኝ፣ውጤታማ እና በስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ምክንያት የመጣ ደም ማነስን ለማከም ተመራጭ መንገድ ነው። በድንገተኛ ጊዜ ለህመምተኛው ደም መስጠት ደም ማነስን ለማስተካከል ፈጣን እና ውጤታማ ቢሆንም ለኢንፌክሽን እና ለአለርጂ ሪያክሽን ሰለሚያጋልጥ ተመራጭ መንገድ አደለም።

በስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ውስጥ የሚመጣ ደም ማነስ ሕክምና ለምን ያስፈልገዋል?

ቀይ የደም ሴሎች ኦክስይጅን ከሳንባ በመውሰድ ለሁሉም የአካል ክፍሎች ያሰራጫሉ። በስር የሰደደ የኩላሊት ህመም የሚመጣ ደም ማነስ ለድካም፣ለተዳከመ የእንቅስቃሴ አቅም፣ለትንፋሽ ማጠር፣ለፈጣን የልብ ምት፣ለትኩረት ማጣት ብርድን ላለመቋቋም እና ለደረት ህመም ይዳርጋል ስለዚህ ይሄ በጊዜ እና በተገቢው መልኩ መታከም ይኖርበታል።