Read Online in Amharic
Table of Content
መግቢያ እና ይዘቶች
መሰረታዊ መረጃ
የኩላሊት መድከም
ሌሎች ዋና ዋና የኩላሊት ህመሞች
የኩላሊት ህመም ወቅት አመጋገብ

13. የኩላሊት እጥበት

የኩላሊት እጥበት በኩላሊት መድከም ምክንያት ሠውነት ውስጥ የሚጠራቀሙ መወገድ ያለባቸውን ቆሻሻ ምርቶች እና ከመጠን በላይ የሆነን ውሃ ከሰውነት በሰው ሰራሽ መንገድ የሚያስወግድ ሂደት ነው። ለመጨረሻ ደረጃ የኩላሊት ህመም ወይም ለአጣዳፊ የኩላሊት በሽታ ተጠቂዎች የሚጠቅም የህይወት አድን ዘዴ ነው።

የኩላሊት እጥበት ከባድ የኩላሊት ድክመት ያለባቸውን ሰዎች እንዴት ይረዳል?

የኩላሊት እጥበት የሚከተሉትን የደከመ ኩላሊትን ስራዎች በመስራት ሰውነትን ያግዛል

 • እንደ ኬሪያቲኒን እና ዩሪያ ያሉ ቆሻሻ የሰውነት ምርቶችን በማስወገድ ደምን በማጥራት
 • ከመጠን ያለፈን ውሃ ማስወገድ እና በሰውነት ውስጥ ያለን ውሃ በትክክ ለኛው መጠን መጠበቅ
 • የንጥረነገር እና የአሲድ ቤዝ በላንስ አለመመጣጠንን ማስተካከል ተገቢ ይሆናል።

ነገር ግን የኩላሊት እጥበት ፤ሁሉንም የጤነኛ ኩላሊት ስራዎች መተካት አይችልም፤ ለአብነትም የሄሞግሎቢን መጠንን ለመጠበቅ የሚያገለግልን ኤሪትሮፖይቲን የተሰኘውን ሆርሞን የማምረት ስራ ሊተካ አይቻለዉም።

የኩላሊት እጥበት መቼ ያስፈልጋል?

የኩላሊት ስራ ከጤነኛው ኩላሊት 85-90% በሚያንስበት ጊዜ(የመጨረሻው ደረጃ የኩላሊት ህመም) ቆሻሻ ምርቶች እና ፈሳሾች በሰውነት ውስጥ ይጠራቀማሉ። እንደ ኬሪያቲኒን እና ሌሎች ናይትሮጅን ያለባቸው ቆሻሻ ምርቶችን የያዙ መርዞች በሰውነት ውስጥ በሚጠራቀሙበት ጊዜ እንደ ማቅለሽለሽ፣ማስመለስ፣ድካም፣የሰውነት ማበጥ እና ትንፋሽ ማጠር የመሳሰሉ ምልክቶችን ያስከትላሉ። እነዚህ ምልክች በአጠቃላይ ዩሬሚያ በመባል ይታወቃሉ። በዚህ ደረጃ ላይ የመድኃኒት ህክምና በቂ ስለማይሆን ሕመምተኛው የኩላሊት እጥበት መጀመር ግድ ይለዋል።

የኩላሊት እጥበት ለስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ፈውስ ይሰጣል?

አይሰጥም። ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ማለትም የማይመለስ እና አንዴ ሕመምተኛው 5 ደረጃ (የመጨረሻ ደረጃ የኩላሊት በሽታ) ደረሰዉ ዓይነት የኩላሊት ንቅለ ተከላ ሕክምና ካላገኘ በስተቀር የዕድሜ ልክ የኩላሊት እጥበት ያስፈልገዋል። በሌላ በኩል አጣዳፊ የኩላሊት በሽታ ሕመምተኛ የኩላሊት ስራው ወደ ነበረበት እስኪመለስ ድረስ ለተወሰነ ጊዜ ብቻ የኩላሊት እጥበት ሊያስፈልገው ይችላል።

የኩላሊት እጥበት አይነቶች ምንድን ናቸው

ሁለት ዋና ዋና የኩላሊት እጥበት አይነቶች ሲኖሩ፤በደም ስር የሚደረግ እና በሆድ ውስጥ የሚደረግ ኩላሊት እጥበት ናቸው።

በደም ስር የሚደረግ (ሄሞዲያሲስ)፡- በዚህ የኩላሊት እጥበት አላስፈላጊ ቆሻሻ ምርቶች እና ከመጠን ያለፉ ፈሳሾች በኩላሊት ማጣሪያ ማሽን በመታገዝ በደም በኩል አልፈው ዲያላይዘር በሚባል ልዩ ማጣሪያ ወይም ሰው ሰራሽ ኩላሊት በኩል ከሰወነት ይወገዳሉ።

የሆድ ውስጥ የሚደረግ ኩላሊት እጥበት፡- በፔሪቶኒየም የኩላሊት እጥበት ጊዜ በቆዳ በኩል በሚገባ ለስላሳ ቱቦ ወይም ካቴተር ቆሻሻ ምርቶችን እና ከመጠን ያለፈን ፈሳሽን ከሰውነት ለማስወገድ የሚረዳ የዲያለሲስ ብጥብጥ በሆድ ውስጥ ባለው ክፍት ቦታ ውስጥ ይለቀቃል።ይሄ ዘዴ በአብዛኛው የሚሰራው ያለ ማሽን ሲሆን የሚካሄደውም በመኖሪያ ቤት ውስጥ ነው።

በመጨረሻ ደረጃ የኩላሊት በሽታ ሕሙማን ዘንድ የኩላሊት እጥበት አይነትን ለመምረጥ የሚረዱ ነገሮች ምንድን ናቸው?

ደም ስር የሚደረግ እና ሆድ ውስጥ የሚደረግ ኩላሊት እጥበት ለመጨረሻ ደረጃ የኩላሊት ሕሙማን የሚሆኑ ውጤታማ መንገዶች ሲሆኑ ለሁሉም ሕሙማን የሚሆን ይሄ ነው የሚባል አንድ ተመራጭ የኩላሊት እጥበት መንገድ ግን የደም ስር የሚደረግ እና የሆድ ውስጥ የሚደረግ ኩላሊት እጥበት ጥቅም እና ጉዳት ከግንዛቤ በማስገባት አንዱን የመምረጥ ሂደት የሚደረገው በሕመምተኛው፣በቤተሰብ አባላቱ እና በኩላሊት ስፔሻሊስቱ አንድ ላይ ይሆናል።

የህክምና ወጪ፣የሕመምተኛው ዕድሜ እና ተያያTh ሁኔታዎች፣የሂሞዲያሲስ ማዕከሉ ርቀት፣የትምህርት ደረጃ፣የሀኪሙ አዝሚያማ እና የህመምተኛው ፍላጎት እና የኑሮ ዘይቤ ውሳኔውን ለማድረግ ከግምት ውስጥ የሚገቡ ነገሮች ናቸው። ባለው ዝቅተኛ ሂሳብ እና ቀላል አቅርቦት ምክንያት ህንድ ውስጥ ባሉ ብዙ ህሙማን ዘንድ ሂሞድያሲስ ተመራጭ ነው።

የኩላሊት እጥበት ተጠቃሚ ሕሙማን አመጋገባቸውን መገደብ ይኖርባቸው ይሆን?

አዎ።የሶድየም፣ፖታሽየም ፣ፎስፈረስ እና ፈሳሽ ገደቦች ለኩላሊት እጥበት ህሙማን የሚመከሩ የተለመዱ የአመጋገብ ገደቦች ናቸው። የኩላሊት እጥበት ተጠቃሚ ህሙማን እነዚህን ገደቦች መከተል ይኖርባቸዋል ነገር ግን ለስር ሰደደ የኩላሊት ህመም ሕሙማን የኩላሊት እጥበት ከተጀመረ በኋላ ገደቦቹ ይቀንሳሉ። አብዛኞቹ ህሙማን ከቅድመ ኩላሊት እጥበት ህክምናቸው አንፃር በኩላሊት እጥበት ወቅት ተጨማሪ ፕሮቲን ከበቂ ካሎሪ ጋር፣ውሃ ሟሚ ቪታሚኖች እና ሚናራሎች እንዲወስዱ ይመከራል። የኩላሊት እጥበት ተጠቃሚ ህሙማን አመጋገባቸውን በተገቢው ሁኔታ ለማቀድ ከአመጋገብ ባለሙያ ጋር ምክክር እንዲያረጉም በብዙ ይመከራል።

ደረቅ ክብደት (ድራይ ዌት) ምንድን ነው?

ደረቅ ክብደት የኩላሊት እጥበት ተጠቃሚዎች በሰውነታቸው ውስጥ የነበረው ከመጠን በላይ የሆነ ፈሳሽ ከተወገደ በኋላ የሚኖራቸው የሰውነት ክብደት ነው። የህሙማን ትክክለኛው ክብደት ሊቀየር ስለሚችል ደረቅ ክብደቱም ከጊዜ ወደ ጊዜ ማስተካከያ ሊያስፈልገው ይችላል። ህመምተኛው የሳንባ መታፈን ስለማያጋጥው እንዲሁም የሄሞዳይናሚክ ሁኔታውም (የህመምተኛው የደም ግፊት ዝቅተኛ አይደለም ብሎም ምልክትም አይታይበትም) ከአደጋ ነፃ በመሆኑ ደረቅ ክብደት ከእብጠት ነፃ ክብደት በመባል ይታወቃል።

ሄሞዲያሲስ

በሄሞዲያሲስ ጊዜ ደም በኩላሊት ማጣቢያ ማሽን እና ማጠቢያ አማካኝነት ይጣራል።

ሄሞዲያሲስ የሚሰራው እንዴት ነው?

አብዛኛውን ጊዜ ሄሞዲያለሲስ የሚሰራው በሆስፒታል ወይም በኩላሊት እጥበት ማዕከላት ውስጥ በሀኪሞች፣ነርሶች እና የኩላሊት እጥበት ባለሙያዎች ነው።

 • የኩላሊት ማጠቢያ ማሽኑ ደምን ከሰውነት በተጣጣፊ ቱቦዎች አማካኝ ነት በመውሰድ ወደ ማጠቢያው ይረጫል።የደም መርጋትን ለመከላከል ወይም የማያቋርጥ የሳላይን ርጭት ይደረጋል።
 • ማጠቢያው (ሰው ሰራሽ ኩላሊት) ደም በውስጡ አልፎ ውስጡ ያሉት ቆሻሻ ምርቶች እና ከመጠን ያለፉ ፈሳሾች የሚወገዱበት ልዩ ማጣሪያ ነው።ይኸውም በኩላሊት ማጠቢያ ማሽን በሚዘጋጅ እና ዲያሊያዝር የሚባል ልዩ ብጥብጥ በመጠቀም ደምን ያጣራል።
 • የማጠቢያ ማሽኑ ደም ከተጣራ በኋላ ወደ ሰውነት መልሶ ይልከዋል።
 • ሄሞዲያሲስ በአብዛኛው በሳምንት ሶስት ጊዜ የሚሰራ ሲሆን እያንዳንዱ እጥበት አራት ሰዓታትን አካባቢ ይፈጃል።

በሄሞዲያሲስ ጊዜ ደም ለመታጠብ ከሰውነት የሚወሰደው እንዴት ነው እና ከተጠራ በኋላስ እንዴት ይመለሳል?

ማዕከላዊ የደም መላሽ ቧንቧ ካቴተር,የተፈጥሮ የደም ቧንቧ እና ደም ሥር ግንኙነት እና ሰው ሰራሽ ትቦ የተለመዱ ሦስት ለሄሞዲያሲስ የሚያስፈልጉ የደም ቧንቧ መድረሻዎች ናቸው።


1. ማዕከላዊ የደም መላሽ ቧንቧ ካቴተር

 • ሄሞዲያሲስ ለመጀመር ውሳኔ እንደተደረገ የደም ቧንቧ መድረሻ ወይም ማዕከላዊ የደም መላሽ ቧንቧ ካቴተር መተከል አለበት። የደም ቧንቧ መድረሻው ደም ለመጽዳት እና ለመጣራት ከሕመምተኛው ሰውነት በመ ውጣት ወደ ሰው ሰራሽ ኩላሊት ወይም ማጣቢያ እንዲገባ ይረዳል።
 • ይሄ የደም ቧንቧ መድረሻ አይነት የሚያገለግለው ፊስቱላ ወይም ግራፍት እስኪዘጋጅ ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ነው።
 • ይሄ ካቴተር አንገት፣ደረት፣ ወይም ብሽሽት አካባቢ የሚገኙ ትልልቅ የደም መላሽ ቧንቧዎች ላይ ይሰካል።በካቴተር በኩል ደም ከ300ሚሊ/ደቂቃ በላይ ለእጥበት መውጣት ይችላል።
 • ካቴተሮች ሁለት ቀዳዳ ያላቸው ባዶ ተጣጣፊ ቱቦዎች ሲሆኑ፤ ደም ከህ መምተኛው ሰውነት በአንዱ ቀዳዳ በመውጣት ወደ ኩላሊት ማጣሪያው መሳሪያ ገብቶ በሌላኛው ቀዳዳ ተመልሶ ወደ ሰውነት ይገባል።
 • የደም መላሽ ቧንቧ ካቴተሮች በድንገተኛ ጊዜ ለሄሞዲያሲስ የሚያገለ ግሉ ፈጣን ነገር ግን ደግሞ ጊዜያዊ መድረሻዎች ናቸው።
 • ሁለት ዓይነት የደም መላሽ ቧንቧ ካቴተሮች ሲኖሩ ባለመሿለኩያ (ለወራት የሚጠቅም) እና መሻለኩያ የሌለው (ለሳምንታት የሚጠቅም) ናቸው።

2. የደም ወሳጅ እና መላሽ ቧንቧዎች መገናኛ

 • የደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛ ለረጅም ጊዜ ሂሞዲያሲስ የሚያገለ ግል የተለመደ እና ምርጥ የደም ቧንቧ መዳረሻ ሲሆን በረጋ ደም ወይም ኢንፌክሽን የመዘጋት ዕድሉ።
 • የደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛ የሚሰራው በክንድ ላይ የእጅ አንጓ አካባቢ በቀላል ቀዶ ጥገና ራድያል ደም ወሳጅ ቧንቧ በማገናኘት ነው።
 • የደም ፍሰት እና ሃይል ከደም መላሽ ቧንቧዎች ይልቅ ደም ወሳጅ ቧንቧዎች ላይ ስለሚበ ልጥ ደም ከደም ወሳጅ ቧንቧ ይጓዛል።
 • ከተወሰኑ ሳምንታት ወይም ወራት በኋላ ደም መላሽ ቧንቧው መስፋት እና ግድግ ዳው መወፈር ይጀምራል። ይሄ የደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛ መጠንከር ጊዜ ሰለሚወስድ ወዲያው እንደ ተሰራ ለሄሞዲያሲስ መጠቀም አይቻልም።
 • ለሄሞዲያሲስ አንድ ደም ወደ ማጣቢያ የሚወስድ እና ሌላ የተጣራውን ደም ወደ ሰውነት የሚመልስ ሁለት ባለ ትልቅ ቀዳዳ መርፌዎች ፊስቱ ላው ላይ ይሰካሉ።
 • የደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛ በደንብ ከተጠበቀ ለዓመታት መቆየት ሲችል ሁሉም የተለመዱ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች የደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛ እጅ ላይ እንዳለ መከናወን ይችላሉ።

የደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛ የተለየ እንክብካቤ የሚያስፈልገው ለምንድን ነው?

 • የስር የሰደደ ኩላሊት እና የመጨረሻ ደረጃ የኩላሊት ህመም ሕመምተኛ ህይወት በበቂ እና መደበኛ የኩላሊት እጥበት ላይ ይወሰናል። የደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛ ለረጅም ጊዜ ሂሞዲያሲስ የሚሆን ቋሚ የደም ቧንቧ መድረሻ ሲሆን ሄሞዲያሲስ ለሚያደርገው ሕመምተኛም የህይወት መስመር ተብሎ ይጠራል። ለ av fistula ልዩ እንክብካቤ ማድረግ በቂ የሆነ ደም ለረጅም ጊዜ እንዲጓጓዝ ይረዳል።
 • በ የደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛ ደም መላሽ ቧንቧ ውስጥ ብዙ መጠን ያለው ደም በከፍተኛ ኃይል ይፈሳል። እንደዚህ የሰፉ ደም መላሽ ቧንቧዎች ላይ የሚደርስ ድንገተኛ አደጋ ከፍተኛ መጠን ያለው የደም መፍሰስ ያስከትላል እንደዚህ ድንገተኛ የሆነ እና መጠኑ የበዛ የደም መፍሰስ ደግሞ ለሕይወት አስጊ ይሆናል። ስለዚህ ለ av fistula ደም መላሽ ቧንቧዎች የሚደረግ ልዩ እንክብካቤ ግዴታ ነው።

ለ የደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛ የሚደረግ እንክብካቤ

የደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛ የሚደረግ ተገቢ መደበኛ የሆነ እንክብካቤ እና ጥንቃቄ ለብዙ ዓመታት በቂ የሆነ ደም እንዲጓጓዝ ይረዳል።ፊስቱላ በጤንነት ተጠብቆ ረጅም ጊዜ እንዲሰራ መወሰድ የሚገባቸው አስፈላጊ ጥንቃቄዎች የሚከተሉት ናቸው፡-

1. ኢንፌክሽንን መከላከል

የደም ቧንቧ መድረሻ ያለበትን ክንድ በየቀኑ እና ከእያንዳንዱ የኩላሊት እጥበት በፊት በማጠብ የፊስቱላውን ቦታ ንፅህና ሁልጊዜም መጠበቅ ያስፈልጋል። ካቴተሮችም በሚሰኩበት እንዲሁም ሙሉ የኩላሉት እጥበት በሚደረግበት ጊዜ የንፅህና መንገድ መጠቀም ያስፈልጋል።

2. የደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛን በጥንቃቄ መጠበቅ

 • የደም ቧንቧ መድረሻውን ለኩላሊት እጥበት ብቻ መጠቀም ይገባል።ለ ማንም የደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛ ያለበትን ክንድ በደም ስርየሚ ሰጡ መድኃኒት ለመስጠት፣ደም ለመቅዳት ወይም ደም ግፊት ለመለካት እንዲጠቀም መፈቀድ የለበትም።
 • የደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛ ን ከአደጋ መጠበቅ። ጌጣጌጥ ፣ጠባቅ ልብሶች ወይም የእጅ ሰዓት የደም ቧንቧ መድረሻ ባለበት ክንድ ላይ አለ ማድረግ። ድንገተኛ የሆነ የ የደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛ አደጋ ህይ ወትን አደጋ ለሚጥል የበዛ ደም መፍሰስ ይዳርጋል።
 • የደም መፍሰስን ለመቆጣጠር ወዲያውኑ በተቃራኒ እጅ ወይም በንጹህ ጠባቅ የጨርቅ ማሰሪያ የሚደማውን ቦታ ጠበቅ አድርጎ መያዝ ያስፈል ጋል። የደም መፍሰሱ ከቆመ በኋላ ወደ ሀኪም መሄድ ያስፈልጋል ነገር ግን የሚፈሰውን ደም ለመቆጣጠር ከመሞከር ይልቅ እርዳታ ለማግኘት ወደ ሆስፒታል ለመሄድ መቻኮል ብልህ ያልሆነ እና መዘዝ ያለዉ እርምጃ ነው።
 • የደም መድረሻ ቧንቧ ባለበት ክንድ ከባባድ ነገሮችን አለማንሳት እና ቦታውን አለመጫን፤ እንዲሁም የደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛ ያለበት ክንድ ላይ ባለመተኛት ጥንቃቄ መደረግ አለበት።

3. የደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛ በተገቢ ሁኔታ መስራቱን ማረጋገጥ

 • የደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛ በኩል የሚያልፈውን የደም ፍሰት የሚሰጠውን የንዝረት ስሜት በቀን ሦስቴ(ከቁርስ፣ምሳ እና እራት በፊት) በመከታተል ንዝረቱ የማይኖር ከሆነ ለሀኪም ወይም ለኩላሊት እጥበት ማዕከል ሰራተኞች በፍጥነት ማሳወቅ ያስፈልጋል። በ ለሄሞዲያሲስ አንድ ደም ወደ ማጣቢያ የሚወስድ እና ሌላ የተጣራውን ደም ወደ ሰውነት የሚ መልስ ሁለት ባለ ትልቅ ቀዳዳ መርፌዎች ፊስቱላው ላይ ይሰካሉ።
 • ውስጥ የደም መርጋት ተፈጥሮ ሊሆን ስለሚችል በጊዜ አግኝቶ መበተን ወይም ማስወገድ የደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛ ሊያድን ይችላል።
 • ዝቅተኛ የደም ግፊት ለየደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛ አለመስራት ሊያጋልጥ ስለሚችል እሱን መከላከል ያስፈልጋል።

4. መደበኛ እንቅስቃሴ

መደበኛ እንቅስቃሴ ማድረግ የደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛ እንዲጠነክር ያረዳል። ሄሞዲያሲስ ከተጀመረም በኋላ የደም ቧንቧ መድረሻ ያለበትን ክንድ መደበኛ እንቅስቃሴ ማሰራት የደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛ ን እንዲጠነክር ይረዳዋል።

3. ግራፍት

 • የደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛ ግራፍት ሌላ አይነት ለረጅም ጊዜ የሚያገለግል የደም ቧንቧመድረሻ ሲሆን ሰዎች ለየደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛ የሚሆን ደህና የሆነ የደም መላሽ ቧንቧ ከሌላቸው ወይም የደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛው በማይሰራ ጊዜ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።
 • የደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛ ግራፍት ለመስራት የደም ወሳጅ ቧንቧ ቆዳ ውስጥ በሚቀበር አጭር እና ለስላሳ ሰው ሰራሽ ቱቦ አማካኝነት ከደም መላሽ ቧንቧ ጋር በቀላል ቀዶ ጥገና ይገናኛል። በኩላሊት እጥበት ጊዜ የሚያገለግሉ መርፌዎች እዚህ ግራፍት ላይ ይሰካሉ።
 • የደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛ ጋር ሲነፃፀር የደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛ ግራፍት የደም መርጋት እና ኢንፌክሽን የማምጣት እድሉ ከፍተኛ ሲሆን እንደ የደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛም ረጅም ጊዜ አይ ቆይም።

የሄሞዲያሲስ ማሽን ጥቅሞች ምን ምንድን ናቸው?

 • የሄሞዲያሲስ ማሽን ደምን ለማጣራት ወደ ማጣቢያው የሚላክ ዲያሊ ያዝ የሚባል ልዩ ዉህድ ያዘጋጃል።
 • ለህመምተኛው እንደሚያስፈልጉት መጠን ወደ ማጣቢያው የሚላከው ብጥብጥ ውስጥ ያለ የኤልክትሮላይቶች መጠን፣ሙቀት፣መጠን እና ግፊትን በጥንቃቄ ያስተካክላል ይቆጣጠራልም። የኩላሊት እጥበት ብጥብጡ ሰውነት ውስጥ የሚገኙ ቆሻሻ ምርቶችን እና ከመጠን ያለፈን ውሃ በማጣቢያው በኩል ያስወግዳል።
 • ለሕመምተኛው ደኅንነት ሲባል ማሽኑ ደም ሳይታወቅ ከማጠቢያው መውጣት እና መፍሰስን ወይም አየር በደም መስመር ውስጥ መገኘ ትን ለመጠቆም የሚያገለግሉ የተለያዩ የደኅንነት ዕቃዎች እና የማንቂያ ደወሎች አሉት።
 • የተለያዩ መለኪዮችን በማያ ገጽ የሚያሳዩ የሄሞዲያሲስ ኮምፒተር ሞዴሎች እና የተለያዩ የማንቂያ ደወሎች የኩላሊት እጥበት ህክምናውን ለማካሄድ እና ለመቆጣጠር ምቹ፣ትክክለኛ እና ደህንነቱ የተረጋገጠ ሁኔ ታይፈጥራሉ።

የማጣቢያው መዋቅር ምንድን ነው ደም የሚያጣራውስ እንዴት ነው?

የማጠቢያው መዋቅር

 

 • ማጣቢያ ወይም በ ሄ ሞ ዲ ያ ሲ ስ ሂደት ጊዜ የደም በት ማጣሪያ ነው።
 • ማጠቢያው በከፊል ፈሳሽ በሚያስልፍ ሰው ሰራሸ ሽፋን የተሠራ ብዙ ሺህ የሚሆኑ ቱቦ መሳይ ባዶ ፋይበሮች የያዘ እና ወደ 20. ርዝመት እና 5. ያለ ሰፊ የፕላስቲክ ስሊንደር ነው።
 • እነዚህ ባዶ ፋይ በሮች በላይ እና ታች የሲለንደሩ ጫፍ ላይ እርስ በርሳቸው በመገናኘት የደም ክፍል ይሰራሉ።ደም በባዶ ፋይበሮዎቹ መክፈቻ በኩል ወይም በአንዱ ጫፍ ወደ ደም ክፍል ገብቶ ከተጣራ በኋላ በሌላው ጫፍ በኩል ይወጣል።
 • የኩላሊት እጥበት ብጥብጥ በአንደኛው የማጠቢያ ጫፍ ገብቶ ከፋይበ ሮች ውጪ ዙሪያ (ዲያሊያዝ ክፍል)ከተዘዋወረ በኋላ በሌላኛው ጫፍ ይወጣል።

በማጠቢያው የሚካሄደው ደም የማጽዳት ሂደት

 

 • በሄሞዲያሲስ ጊዜ ደም ወደ ብዙ ሺህ ደም ስር መሳይ ባዶ ፋይበሮች ውስጥ ገብቶ ለመሰራጨት በህመምተኛው የደም ቧንቧ መድረሻ እና የደም ቱቦዎች በኩል በመውጣት ወደ አንዱ የማጠቢያ ጫፍ ይገባል። የኩላሊት እጥበት ብጥብጡ ደግሞ በሌላ ጫፍ ገብቶ በማጠቢያው ዲያሊያዝ ክፍል ውስጥ ይዘዋወራል።
 • በእያንዳንዱ ደቂቃ ወደ 300.ሊ የሚሆን ደም እና ወደ 600. የሚሆን የኩላሊት እጥበት ብጥብጥ በተቃረኒ አቅጣጫ በማጣሪያው ውስጥ ያለማቋረጥ ይዘዋወራሉ። ደምን ከዲያሊያዝ የሚለየው የባዶ ፋይበሮች ከፊል ፈሳሽ አሳላፊ ሽፋን ቆሻሻ ምርቶችን እና ከመጠን ያለፉ ፈሳሾችን ከደም ወደ ዲያሊያዝ ክፍል እንዲገቡ ይረዳል።
 • እጥበት የጨረሰ ደም በአንዱ የማጣሪያ ጫፍ በኩል የሚወጣ ሲሆን ከደም የሚወገዱ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን እና ከመጠን ያለፉ ፈሳሾችን የያዘ የኩላሊት እጥበት ዉህድ ደግሞ ደም በሚገባበት የማጣሪያ ጫፍ በኩል ይወጣል።
 • በሄሞዲያሲስ ጊዜ የህመምተኛው ደም በማጠቢያው ውስጥ 12 ጊዜ ያክል ያልፋል። ከሰዓታት ህክምና በኋላ የደም ዩሪያ እና ኬሪያቲኒን መጠኖች በደንብ ይቀንሳሉ እንዲሁም ከመጠን ያለፉ ፈሳሾች ሲወገዱ የኤልክትሮላይት መጠኖችም ይስተካከላሉ።

ዲያሊያዝ ምንድን ነው በሄሞዲያሲስ ሂደት ውስጥስ ጥቅሙ ምንድን ነዉ?

 • ዲያሊያዝ(የኩላሊት እጥበት ብጥብጥ) ቆሻሻ ምርቶችን እና ከመጠን ያለፉ ፈሳሾችን ከደም ለማስወገድ የሚጠቅም የተለየ ፈሳሽ ነው።
 • የስታንዳርድ ዲያሊያዝ ጥንቅር ኖርማል የውጨህዋስ ፈሳሽን የሚመስል ሲሆን ጥንቅሩ ለህመምተኛው እንደሚያስፈልጉት ንጥረ ነገሮች ዓይነት ሊሻሻል ይችላል።
 • ዲያሊያዝ ከከፍተኛ የተጠራ ውሃ 30 ክፍሎች እና ከአንድ የዲያሊያዝ ጥንቅር በአምራቾች ይዘጋጃል።
 • የዲያሊያዝ ብጥብጥ ኤልክትሮላይቶችን፣ሚናራሎችን እና ባይካርቦኔ ትን የያዘ እና ገበያ ላይ የሚገኝ የተለየ ፈሳሽ ነው።
 • ዲያሊያዝን ለመስራት የሚያገለግለው ውሃ በአሸዋ ማጣሪያ፣በከሰል ማጣሪያ፣በውሃ ማለስለሻ፣በተገላቢጦሽ ኦስሞሲስ፣በዲአዮናይዜሽን እና በአልትራቫዮሌት ማጣሪያ ይጣራል። የእነዚህ ሂደቶች ውጤት የሚሆ ነውከ አፈር፣ከሰስፔንድድ ብርዞች ፣ኬሚካል ብርዞች፣ሚናሎች፣ባክቴሪ ያዎች እና ኢንዶቶክሲን ነፃ የሆነ ውሃ ይሆናል።
 • ይሄ በጥንቃቄ የተደረገ ውሃ የማጥራት እና ቀጣይ ጥራቱን የመቆጣ ጠር ሂደቶች ህመምተኛውን ውሃ ውስጥ ለሚገኙ በካዮች እንዳይጋለጥ ይረዳል። በእያንዳንዱ ሄሞዲያሲስ ጊዜ እያንዳንዱ ህመምተኛ 150 ሊትር ለሚሆን ውሃ ተጋላጭ ይሆናል።

ሄሞዲያለሲስ የሚሰራው የት ነው?

አብዛኛውን ጊዜ ሄሞዲያሲስ በሆስፒታሎች ወይም በኩላሊት እጥበት ማዕከላት ውስጥ በሀኪሞች ተቆጣጣሪነት በሰለጠኑ ባለሙያዎች ይሰጣል። ጥሩ ሁኔታላይ ለሚገኙ ጥቂት ህሙማን ግን መኖሪያ ቤት ውስጥ ሊሰጥ ይችላል። መኖሪያ ቤት ውስጥ የሚሰጥ ሄሞዲያሲስ ለማድረግ ለህመምተኛው እና ለቤተሰብ አባላቱ ተገቢ የሆነ ስልጠና መስጠት፣በቂ የሆነ ቦታ እና ጥሩ የገንዘብ አቅም ይጠይቃል።

ሄሞዲያሲስ የህመም ስሜት ያመጣል በኩላሊት እጥበት ጊዜስ ህመምተኛው ምን ማከናወን ይችላል?

የሄሞዲያሲስ ሂደት የህመም ስሜት አያመጣም። ሆኖም ግን ሂደቱ ሲጀምር በደም ስር የሚገቡ መርፌዎች ተሰክተው የደም ቱቦዎች ከህመምተኛው ሰውነት ጋር በሚገናኙበት ጊዜ አነስተኛ የህመም ስሜት ሊሰማ ይችላል።ተመላላሽ ታካሚዎችም ለዚሁ ህክምና በሳምንት ሶስት ጊዜ ወደ ሆስፒታል ወይም የኩላሊት እጥበት ማዕከል መመላለስ ይጠብቅባቸዋል።

በህክምናው ጊዜ ህሙማኑ ማረፍ፣መተኛት፣ማንበብ፣ሙዚቃ ማዳመጥ ወይም ቴሌቪThን ማየት ይችላሉ። ቀለል ያሉ መቆያ ምግቦች እና ትኩስ እና ቀዝቃዛ መጠጦችንም ሊወስዱ ይችላሉ።

በሄሞዲያሲስ ጊዜ የተለመዱ ችግሮች ምንድን ናቸው?

በሄሞዲያሲስ ጊዜ የተለመዱ ችግሮች የሚባሉት ዝቅተኛ የደም ግፊት ፣ማቅለሽለሽ፣ወደላይ ማለት፣የጡንቻ መሸማቀቅ ፣ድካም እና ራስ ህመም ሲሆኑ የታካሚውን ሄሞዳይናሚክስ እና የደም መጠን በተገቢው ሁኔታ ከኩላሊት እጥበት በፊት በመለካት እነዚህን አሉታዊ ክስተቶች መከላከል ይቻላል። በየእጥበቱ መሀልም የክብደት መጠንን ብሎም የደም ኤሌክትሮላይቶችን እና የሄሞግሎቢን መጠንን መቆጣጠር ያስፈልጋል።

የሄሞዲያሲስ ጥቅም እና ጉዳቶች ምንድን ናቸው?

የሄሞዲያለሲስ ጥቅሞች፡-

 • ህክምናው የሚደረገው በሰለጠኑ ነርሶች እና ባለሙያዮች ስለሆነ ለታካ ሚዎች ራስን የመንከባከብ ጫናን ይቀንሳል። አንዳንድ ታካሚዎች ደግሞ በተለየ ሄሞዲያሲስን ከፔሪቶንየም የኩላሊት እጥበት ይልቅ ምቹ እና ውጥረት የሌለበት ሆኖ ያገኙታል።
 • ሄሞዲያሲስ ከፔሪቶንየም የኩላሊት እጥበት በተሻለ ፈጣን እና ውጤታማ ነው።
 • የሄሞዲያሲስ ማዕከል ታካሚዎች ከሌሎች ተመሳሳይ በሽታ ካለባቸው ታካሚዎች ጋር የሚገናኙበት እና ትስስር የሚፈጥሩበት መድረክ ይፈጥ ራል። እንደዚህ አይነት ትስስር ውጥረትን ቀንሶ ታካሚዎች ከሌሎች ታካ ሚዎች ጋር የሚያሳልፉትን ጊዜ እንዲወዱት በማድረግ ይረዳል።
 • በአብዛኛው ጊዜ ሄሞዲያሲስ በሳምንት ሦስት ጊዜ ለ4 ሰዓታት ያህል የሚሠራ ስለሆነ ታካሚዎች በመሃል ነፃ ጊዜ ይኖራቸዋል።
 • ታካሚዎች የፐሪቶናይቲስን እና የቱቦ መውጫ ኢንፌክሽኖችን ተጋላጭነት ማስወገድ ይችላሉ።
 • በአንዳንድ ሀገራት የሄሞዲያሲስ ወጪ ከፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ይቀንሳል።

የሄሞዲያሲስ ጉዳቶች

 • በተለይ የኩላሊት እጥበት ማዕከል ከመኖሪያ ቤት በጣም የራቀ ከሆነ ወደ ማዕከሉ ለመሔድ የሚጠፋ ጊዜ እና አለመመቸትን ሊፈጥር ይችላል።
 • የኩላሊት እጥበት ቀጠሮ የተወሰነ ስለሆነ ታካሚው የሚያከናውናቸውን ሌሎች ድርጊቶች ከቀጠሮ ውጪ አድርጎ ማቀድ ይኖርበታል።
 • በህክምናው ጊዜ በተደጋጋሚ መርፌ የሚገባበት ቦታ ላይ የህመም ስሜት ሊፈጠር ይችላል። ነገር ግን ህመሙን ለመቀንስ ቆዳ ላይ የሚቀቡ ማደን ዘዣዎች ማድረግ እና የመሳሰሉ እርምጃዎችን መውሰድ ይቻላል።
 • ከፈሳሽ፣ጨው፣ፖታሽየም ፣እና ፎስፈረስ የተገደበ አመጋገብ መከተል ስለ ሚያስፈልግ ታካሚዎች እነዚህን ገደቦች መልመድ ይኖርባቸዋል።
 • እንደ ሄፐታይተስ ቢ እና ሲ ለመሳሰሉ በደም በኩል ለሚተላለፉ ኢንፌክሽ ኖች ተጋላጭነትን ከፍ ያደርጋል።

በሄሞዲያሲስ ጊዜ መደረግ ያለባቸው እና የሌለባቸው ነገሮች

 • የኩላሊት እጥበት ተጠቃሚ የመጨረሻ ደረጃ የኩላሊት ህመም ህመ ምተኞች በሳምንት ሦስቴ ህክምና ያስፈልጋቸዋል። የህክምናውን ቀጠሮ መዝለል ወይም ከነ አካቴዉ መቅረት ጤናን አደጋ ላይ ይጥላል።
 • የሄሞዲያሲስ ታካሚዎች ተገቢ የሆነ የአመጋገብ ገደቦችን ማድረግ አለ ባቸው። የፈሳሽ፣ጨው፣ፖታሽየም እና ፎስፈረስ ገደቦችን መጠበቅ ይኖር ባቸዋል። የፕሮቲን አወሳሰድንም በሀኪም ወይም በአመጋገብ ባለሙያ ምክር በመታገዝ መቆጣጠር ይገባል። በሀሳብ ደረጃ በኩላሊት እጥበት መሀል የሚኖር የሰውነት ክብደት መጨመር ከ2-3.(4.4-6.6 lbs) ብቻ መሆን እንዳለበትም ተቀምጧል።
 • በሄሞድያሲስ ታካሚ ዘንድ የአመጋገብ ጉድለት የተለመደ በመሆኑና ወደ አልተፈለገ ውጤት ስለሚያመራ በሰውነት ውስጥ ያለን ካሎሪ እና ፕሮቲን በበቂ ሁኔታ ለመጠበቅ ታካሚውን በሀኪሙ ተቆጣጣሪነት ወደ አመጋገብ ስርአት ባለሙያ መላክ ተገቢ ነው።
 • ለሄሞዲያሲስ ታካሚዎች እንደ ቪታሚን ቢ እና ሲ የመሰሳሉ በውሃ ሟሚ ቪታሚኖች መስጠት ያስፈልጋል። ለሰውነት የሚያስፈልጉ ቪታሚ ኖች በበቂ ሁኔታ ላይኖራቸው እና ስር የሰደደ የኩላሊት በሽታ ህሙማንን ሊጎዱ የሚችሉ እንደ ቪታሚን ኤ፣ኢ እና ሊይዙ ስለሚችሉ ካለ ሀኪም ትዕዛዝ የሚሸጡ የቫይታሚን እንክብሎችን ከመጠቀም መቆጠብ ያስፈ ልጋል።
 • ደም ውስጥ እንዳለው የካልሽየም፣ ፎስፈረስ እና ፓራታይሮድ ሆርሞን መጠን ታይቶ ለታካሚው ካልሽየም እና ቪታሚን ሊሰጡት ይችላሉ።
 • የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ ማድረግ ግዴታ ሲሆን ማጨስ ማቆም፣ተገቢ የሆነ የሰውነት ክብደትን መጠበቅ፣መደበኛ እንቅስቃሴ ማድረግ እና የአ ልኮል አወሳሰድን መገደብ የመሳሰሉ እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው።

የሄሞዲያሲስ ታካሚ ሀኪም ወይም ነርስን ማማከር ያለበት መቼ ነው?

ታካሚው በፍጥነት የኩላሊት እጥበት ነርስን ወይም ሀኪምን ማማከር ያለበት ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው።

 • ከየደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛ ወይም ካቴተር ከተሰካበት ቦታ የደም መፍሰስ ሲኖር
 • የደም ቧንቧ እና ደም ሥር መገናኛ ላይ ንዝረት፣የተለየ ድምፅ (bruit) ፣መርገብገብ ሳይኖር ሲቀር
 • ያልተጠበቀ የክብደት መጨመር፣አሳሳቢ የሰውነት ማበጥ እና የትንፋሽ ማጠር ሲኖር
 • የደረት ህመም እና በጣም ያዘገመ ወይም የፈጠነ የልብ ምት
 • ግራ መጋባት፣እንቅልፍ እንቅልፍ ማለት፣ራስን መሳት ወይም ማንቀጥቀጥ
 • ትኩሳት፣ብርድ ብርድ ማለት፣ከባድ የሆነ ወደላይ ማለት፣ደም መትፋት ወይም ከባድ ድካም

የሆድ ውስጥ ኩላሊት እጥበት (የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት)

የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት የኩላሊት ድክመት ላጋጠማቸው ህሙማን የሚሰራ ሌላኛው የኩላሊት ማጠቢያ መንገድ ሲሆን ውጤታማነትን እና በሰፊው ተቀባይነትን አግኝቷል። ይኸውም በመኖሪያ ቤት ውስጥ የሚደረግ የተለመደ የኩላሊት እጥበት አይነት ነው።

የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ምንድን ነው?

 • ፔሪቶንየም የውስጠኛውን የሆድ ክፍል የሚሸፍን ስስ ሽፋን ነው።
 • የፔሪቶንየም ሽፋን በተፈጥሮ በከፊል የሚያሳልፍ ሲሆን በደም ውስጥ የሚገኙ አላስፈላጊ የሰውነት ቆሻሻዎችንና መርዞችን ማሳለፍ ይችላል።
 • የፔሪቶንም ኩላሊት እጥበት በፔሪቶንየም ሰስ ሽፋን አማካኝነት የሚካ ሄድ ደም የማጥራት መንገድ ነው።

የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት አይነቶች ምንድን ናቸው?

የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት አይነቶች፡-

 1. አልፎ አልፎ የሚደረግ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት
 2. የማይቋረጥ ተንቀሳቃሽ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት
 3. የማይቋረጥ ዑደታዊ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት

1. አልፎ አልፎ የሚደረግ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት

አልፎ አልፎ የሚደረግ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት፤ በሆስፒታል ውስጥ ለተኙ የአጣዳፊ ኩላሊት ህመም ታማሚዎች፣ለሕፃናት፣ለድንገተኛ ሁኔታዎች እንዲሁም ለመጨረሻ ደረጃ የኩላሊት ህመም ተጠቂዎች እንደ መጀመሪያ ደረጃ ህክምና የሚሰጥ እና ለአጭር ጊዜ የሚደረግ ውጤታማ የኩላሊት እጥበት ዓይነት ነው። በዚህ የኩላሊት እጥበት ሂደት ዲያሊያዝ የሚባል የተለየ ዉህድ፤ በህመምተኛው ሆድ ላይ በሚቀመጥ፤ ብዙ ቀዳዳዎች ባሉት ካቴተር ወደ ህመምተኛው ክፍት የሆድ ቦታ ወይም ፔሪቶንያል ስፔስ ይላካል። ዲያሊያዙ ቆሻሻ ምርቶችን እና ከመጠን ያለፉ ፈሳሾችን ከህመምተኛው ደም በመሳብ ያወጣቸዋል። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ፈሳሹ ከሰውነት ይወገዳል ሂደቱ በዚህ መሰረት በቀን ውስጥ ብዙ ጊዜ ይደጋገማል፡

 • አልፎ አልፎ የሚደረግ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ከ24-36 ሰዓታት የሚቆይ ሲሆን በህክምናው ሂደት ውስጥ 30-40 ሊትር የሚሆን ዲያሊ ያዝ ብጥብጥ ጥቅም ላይ ይውላል።
 • አልፎ አልፎ የሚደረግ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ለህመምተኛው እን ደሚያስፈልገው መጠን ከ1-3 ቀን ባለ ልዩነት ውስጥ ተደጋግሞ ሊሰራ ይችላል።

የማያቋርጥ የሆድ ውስጥ የኩላሊት እጥበት

2. የማይቋረጥ ተንቀሳቃሽ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት

የማይቋረጥ ተንቀሳቃሽ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት (CAPD) ምንድን ነው?

የማይቋረጥ ተንቀሳቃሽ የፔሪቶንየም ዲያለሲስ ማለት፡ የማይቋረጥ- ሂደቱ አይቋረጥም(ህክምናው ሳይቋረጥ በቀን ለ24 ሰዓታት በሳምንት ለ7 ቀናት ይደረጋል)

ተንቀሳቃሽ- ታካሚው ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ እና የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴውን ማድረግ ይችላል።

ፔሪቶንየም- በሆድ ውስጥ የሚገኘው የፔሪቶንየም ስስ ሽፋን እንደ ማጣሪያ ሆኖ ያገለግላል።

ዲያለሲስ- ደምን የማጥራት መንገድ

የማይቋረጥ ተንቀሳቃሽ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት የተለየ ፈሳሽን በመጠቀም በመኖሪያ ቤት ውስጥ በታካሚዎች ሊሰራ የሚችል የኩላሊትእጥበት አይነት ሲሆን ምቾት እና ነፃነትን ስለሚሰጥ በበርካታ የዓለም ሀገራት የታወቀ የኩላሊት እጥበት አይነት ነው።

የማይቋረጥ ተንቀሳቃሽ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ሂደት የማይቋረጥ ተንቀሳቃሽ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ካቴተር፡-

ቋሚ ለሆነ የፔሪቶንየም የኩላሊት እጥበት የሚጠቀመው መዳረሻ ብዙ ቀዳዳዎች ያሉት ለስላሳ ቀጭን እና ተጣጣፊ የሆነ ሲልከን የላስቲክ ቱቦ ነው። ቱቦው በቀላል ቀዶ ጥገና ከእምብርት አንድ ኢንች በአንድ በኩል ወረድ ብሎ በሆድ ግድግዳ በኩል የህመምተኛው ሆድ ውስጥ ይከተታል። የማይቋረጥ ተንቀሳቃሽ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ካቴተር የሚደረገው ኩላሊት እጥበቱ ከመጀመሩ ከ10-14 ቀናት በፊት ነው። ይህ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ካቴተር ለታካሚው የደም ሥር እና የደም ቧንቧ መገናኛ ለሄሞዲያሲስ ታካሚ እንደሆነው የህይወት መስመር ተብሎ ይጠራል።

የማይቋረጥ ተንቀሳቃሽ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ቴክኒክ፡-

በማይቋረጥ ተንቀሳቃሽ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ሂደት ጊዜ ዲያሊያዝ(ልዩ ፈሳሽ) በሆድ ክፍት ቦታ ውስጥ በመለቀቅ ለተወሰነ ጊዜ እዛው ከተቀመጠ በኋላ ይወገዳል። የመሙላት፣የማኖር እና የማስወገድ ሂደቱ ደግሞ ልውውጦሽ ተብሎ ይጠራል።

 

መሙላት፡ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ፈሳሽ ከንፁህ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ከረጢት በስበት ኃይል በመውጣት ከካቴተር ጋር በተገናኙ ንፁህ ቱቦዎች አልፎ በሆድ ክፍት ቦታ ውስጥ ይለቀቃል። ብዙ ጊዜ የሚለቀቀው ፈሳሽ 2ሊትር ሲሆን፤ ባዶ የሆነው የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ከረጢትም ተጠቅልሎ እስከሚቀጥለው ልውውጥ ድረስ በህመምተኛው የውስጥ ልብስ ውስጥ ይከተታል።

መቆየት፡ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ፈሳሽ በሆድ ክፍት ቦታ ውስጥ የሚቆይበት ጊዜ የማኖር ጊዜ ተብሎ ይጠራል። ይሄም በእያንዳንዱ ልውውጥ ጊዜ በቀኑ ክፍለ ጊዜ ከ4-6 ሰዓታት ያህል በማታው ክፍለ ጊዜ ደግሞ ከ6-8 ሰዓታት ያህል ይወስዳል። ደምን የማጥራት ሂደቱ የሚካሄደው በዚሁ የማኖር ጊዜ ይሆናል። የፔሪቶንየም ስስ ሽፋን ቆሻሻ ምርቶችን ፣የማያስፈልጉ ንጥረ ነገሮች እና ከመጠን ያለፉ ፈሳሾችን ከደም ወደ ፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ፈሳሹ እንዲገቡ በማድረግ እንደማጣሪያ ያገለግላል። በዚህ ጊዜ ታካሚው ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ስለሚችል ተንቀሳቃሽ ይባላል።

ማስወገድ የማኖር ጊዜው ሲገባደድ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ፈሳሹ የታካሚው ልብሶች ውስጥ ተጠቅልሎ ወደ ተቀመጠው ባዶ ፈሳሽ ማጠራቀሚያ ከረጢት ውስጥ ይወገዳል። የሚወገደውን ፈሳሽ የያዘው ከረጢት የሚጣለው ክብደቱ ከተለካ በኋላ ሲሆን የሚወገደው ፈሳሽም ጥርት ያለ መሆን አለበት። ፈሳሹን አስወግዶ በአዲስ ብጥብጥ የመተካት ሂደትም ከ30-40 ደቂቃ ይወስዳል። ልውውጡ በቀኑ ክፍለ ጊዜ ከ3-5 ደቂቃ እና በማታው ክፍለ ጊዜ አንዴ ሊሰራ ይችላል። በማታው ክፍለጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው ፈሳሽ ሆድ ውስጥ በማደር የሚወገደው ጠዋት ላይ ነው። የማይቋረጥ ተንቀሳቃሽ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት በሚሰራበት ጊዜ ጥብቅ የሆኑ የንፅህና ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይገባል።

3. የማይቋረጥ ዑደታዊ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ወይም አውቶማቲክ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት

የማይቋረጥ ዑደታዊ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ወይም አውቶማቲክ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት በመኖሪያ ቤት ውስጥ አውቶማቲክ አሽከርካሪ ማሽንን በመጠቀም የሚሰራ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት አይነት ነው። ማሽኑ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ፈሳሹን በአውቶማቲክ መንገድ ይሞላል ከዛም ከሆድ ያስወግዳል። እያንዳንዱ ዑደት ከ1-2 ሰዓታት የሚቆይ ሲሆን ልውውጡ በእያንዳንዱ እጥበት ውስጥ ከ4-5 ጊዜ ይደረጋል። ህክምናው ታካሚው በሚተኛበት ጊዜ ማታ ላይ የሚሰራ ሲሆን ከ8-10 ሰዓታት ይቆያል። ጠዋት ላይ ማሽኑ የሚነቅል ሲሆን ከ2-3 ሊትር የሚሆን የፔሪቶንየም ፈሳሽ የሆድ ክፍት ቦታ ውስጥ ይቀራል። ይሄ ፈሳሽ በሚቀጥለው ምሽት ህክምና ከመጀመሩ በፊት ይወገዳል። ታካሚዎቹ በቀኑ ክፍለ ጊዜ የእለት ተእለት እንቅስቃሴዎቻችውን ማድረግ ማስቻሉ አንዱ የአውቶማቲክ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ጥቅም ሲሆን የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ከረጢት ከካቴተሩ ጋር የሚቀጠለው እና የሚላቀቀው በቀን አንዴ ብቻ በመሆኑ ሂደቱን ምቹ እና ለፔሪቶናይቲስ የቀነሰ ተጋላጭነት ያለው ያደርገዋል። ሆኖም ግን አውቶማቲክ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት አንዳንድ ሀገሮች ውስጥ ውድ ሊሆን ከመቻሉም አልፎ ለአንዳንድ ህሙማን አጠቃቀሙ የተወሳሰበ ሊሆን ይችላል።

የማይቋረጥ ዑደታዊ የፔሪቶንያል ኩላሊት እጥበት ሂደት ውስጥ የፔሪቶንየም እጥበት ፈሳሽ ጥቅም ምንድን ነው?

የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ፈሳሽ ወይም ዲያሊያዝ ንጥረነገሮች እና ግሉኮስን የያዘ ንጹህ ብጥብጥ ነው። በዲያሊያዝ ውስጥ የሚገኘው ግሉኮስ ፈሳሽ ከሰውነት እንዲወገድ ይረዳል። በውስጣቸው በሚገኘው የግሉኮስ መጠን ላይ ተመስርቶ በህንድ ውስጥ ወይም በሌሎች የዓለም ክፍላት ሊገኙ የሚችሉ ሦስት የዲያሊያዝ አይነቶች ሲኖሩ (1.52.54.5) ለእያንዳንዱ ታካሚ የሚሆነው የዲያሊያዝ አይነት የሚወሰነው መወገድ እንዳለበት ሰውነት ውስጥ እንዳሚገኝ ፈሳሽ መጠን ይሆናል። አንዳንድ ሀገራት ውስጥ በግሉኮስ ፋንታ icodextrin የያዙ አዳዲስ የፔሪቶንየም ዲያሊያዝ ፈሳሾችን ማግኘት ይቻላል። icodextrin የያዙ ብጥብጦች ፈሳሽ ከሰውነት ውስጥ የሚያስወግዱት በዝግታ ሲሆን ከፍተኛ የሰውነት ክብደት ላላቸው እና ለስኳር ህመምተኞች ተመራጭ ናቸው።

የማይቋረጥ ዑደታዊ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ብጥብጥ መያዣ ከረጢቶች 1000-2500 . ያህል በተለያዩ መጠኖች ተዘጋጅተው ሊገኙ ይችላሉ።

የማይቋረጥ ዑደታዊ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ጊዜ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የተለመዱ ችግሮች ምንድን ናቸው?

ኢንፎክሽኖች ዋነኛ የማይቋረጥ ዑደታዊ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት የሚያመጣቸው ውስብስብ ችግሮች ናቸው። በጣም የተለመደው ፔሪቶናይቲስ ወይም የፔሪቶኒየም ኢንፌክሽን ሲሆን የሆድ ህመም፣ትኩሳት፣ብርድ ብርድ ማለት እና የተረበሸ የፔሪቶንየም ፈሳሽ ፍሰት የተለመዱ ምልክቶቹ ናቸው። ፔሪቶናይቲስን ለመከላከል የማይቋረጥ ዑደታዊ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት በሚደረግበት ጊዜ ጥብቅ የሆነ የንፅህና ጥንቃቄ መደረግ ይኖርበታል እንዲሁም የሆድ ድርቀትንም መከላለከል ይገባል። የፔሪቶናይቲስ ህክምና የሚባሉት ሰፊ ስፔክትረም አንቲባያቲክስን መስጠት፣የፈሳሹን መስራት(ተገቢውን አንቲባያቲክስ ለመምረጥ)፣እና ለጥቂት ታካሚዎች ደግሞ ካቴተሩን ጨርሶ ማንሳት ይሆናሉ። የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ካቴተር መውጫ ላይም የሚፈጠር ኢንፌክሽን ሊኖር ይችላል።

ኢንፌክሽንን ለመከላከል የሚወሰዱ ጥንቃቄዎች የማይቋረጥ ዑደታዊ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ለሚጠቀሙ ታካሚዎች በጣም አስፈላጊ ናቸው።

ሌላ ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮች የሆድ መነፋት፣በሆድ ግድግዳ መሳሳት ምክንያት ሊመጣ የሚችል እበጥ፣የፈሳሽ መጠራቀም፣የቆለጥ ከረጢት ማበጥ፣የሆድ ድርቀት፣የጀርባ ህመም፣አነስተኛ ፍሰት ያለው ውጋጅ፣የፈሳሽ ሳይታወቅ መውጣት እና የክብደት መጨመር ናቸው።

የማይቋረጥ ዑደታዊ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ጥቅም

 • ከሄሞድያሲስ ህክምና ጋር ሲነፃፀር መወሰድ ያለባቸው የምግብ እና የፈሳሽ ገደቦች አነስተኛ ናቸው።
 • የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት በመኖሪያ ቤት፣በሥራ ቦታ ወይም በጉዞ ላይ ሊሰራ ስለሚችል የበለጠ ነፃነትን ያጎናጽፋል። የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ለማድረግ የሄሞዲያሲስ ማሽን፣የሄሞዲያሲስ ነርስ፣ባለሙያ ወይም የቤተሰብ አባል ስለማያስፈልግ ታካሚው እራሱ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበቱን ማከናወን ይችላል።
 • ከሄሞዲያሲስ ጋር ተያይዘው የሚመጡ በሆስፒታል ወይም በኩላሊት እጥበት ማዕከላት የሚሰጡት ቋሚ ቀጠሮዎችን፣የመጓጓዣ ጊዜን እና የመርፌ ህመሞችን ያሰቀራል።
 • የደም ግፊትን እና ማነስን በተሻለ መልኩ መቆጣጠር ሊያስችል ይችላል።
 • ለዘብ ያለ እና የማያቋርጥ የደም ማጥራት ስለሆነ እንግልት እና አለመመ ቸት አይኖረውም።

የማይቋረጥ ዑደታዊ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ጉዳቶች

 • የፔሪቶንየም ኢንፌክሽኖች (ፔሪቶናይቲስ) እና የካቴተር መውጫ ቦታ ላይ የሚፈጠሩ ኢንፌክሽኖች የተለመዱ ናቸው።
 • ታካሚዎች በየዕለቱ ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ መመሪያዎችን እና ጥብቅ ንፅህናን በመከተል ህክምናውን ያለማቋረጥ ማድረግ ስለሚኖርባቸው ህክምናው ውጥረት የተሞላበት ሊሆን ይችላል።
 • በቋሚ እና ውጫዊው ካቴተር ብሎም በሆድ ውስጥ በሚጠራቀመው ፈሳሽ ምክንያት አንዳንድ ህመምተኞች ላይ አለመመቸት ሊኖር ይችላል።
 • የክብደት መጨመር፣ደም ውስጥ ያለ ስኳር ከፍ ማለት እና ትራይገላ ሰሪዲ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ብጥብጥ ውስጥ ካለው ስኳር (ግሉኮስ) ሊመጣ ይችላል።
 • የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ብጥብጥ ከረጢት ቤት ውስጥ ለማስቀ መጥ ሆነ ለመያዝ ምቹ ላይሆን ይችላል።

ለማይቋረጥ ዑደታዊ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ታካሚዎች ምን አይነት የአመጋገብ ለውጦች ያስፈልጋሉ?

 • የማይቋረጥ ዑደታዊ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ታካሚ በቂ የሆነ የተ መጣጠነ ምግብ የሚያስፈልገው ሲሆን አመጋገቡም ከሄሞዲያሲስ ታካ ሚዎች በመጠኑ ሊለይ ይችላል።
 • ሀኪሙ ወይም የአመጋገብ ባለሙያው በፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ጊዜ ሊመጣ የሚችል የፕሮቲን ማነስን ለመተካት በምግብ ላይ ከፍ ያለን ፕሮቲን እንዲወሰድ ሊመክሩ ይችላሉ።
 • ከመጠን ያለፈን የክብደት መጨመርን አስቀርቶ የተመጣጠነ ምግብ እጥ ረትን ለማስወገድ በቂ የሆነ ካሎሪ መወሰድ አለበት። ሆኖም ግን የፔሪ ቶንየም ብጥብጥ ውስጥ ያለው ግሉኮስ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ተጠቃሚ ላይ ከመጠን ያለፈ ካርቦሃይድሬትንያለማቋረጥ ሊጨምር ይችላል።
 • በፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ጊዜ ፈሳሽ እና ጨው መገደብ ቢኖርባቸ ውም ፤ገደባቸው ግን በሄሞዲያሲስ ጊዜ ከሚደረገው ይቀንሳል።
 • ምግብ ውስጥ ያሉ ፖታሽየም እና ፎስፌት መገደብ አለባቸው።
 • የሆድ ድርቀተን ለመከላከል በምግብ ውስጥ የሚወሰድ ፋይበር መጨመር አለበት።

የማይቋረጥ ዑደታዊ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ታካሚ መቼ ነው የኩላሊት እጥበት ሀኪም ወይም ነርስ ማግኘት ወይም ማማከር ያለበት?

የማይቋረጥ ዑደታዊ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ታካሚ የሚከተሉት ችግሮች ካጋጠሙት በፍጥነት የኩላሊት እጥበት ሀኪም ወይም ረዳት ነርስ ማግኘት አልያም ማማከር አለበት።

 • የሆድ ህመም፣ትኩሳት ወይም ብርድ ብርድ ማለት፤
 • የደፈረሰ ወይም ደም የቀላቀለ የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ፈሳሽ፤
 • በፔሪቶንየም ካቴተር መውጫ ዙሪያ የህመም፣መግል፣መቅላት፣ማበጥ ወይም ሙቀት መኖር፤
 • የፔሪቶንየም ኩላሊት እጥበት ፈሳሽን ለማስገባት እና ማስወጣት መቸገር፤
 • የሆድ ድርቀት፤
 • ያልተጠበቀ የክብደት መጨመር፣ጉልህ የሆነ የሰውነት እብጠት፣የትንፋሽ ማጠር እና ከባድ የሆነ የደም ግፊት(የፈሳሽ ከመጠን በላይ መብዛትን የሚያሳይ) መኖር፤
 • ዝቅተኛ የደም ግፊት፣የክብደት መቀነስ፣ቁርጥማት እና ማዞር(የፈሳሽ ማነስን የሚያመላክት)