Read Online in Amharic
Table of Content
መግቢያ እና ይዘቶች
መሰረታዊ መረጃ
የኩላሊት መድከም
ሌሎች ዋና ዋና የኩላሊት ህመሞች
የኩላሊት ህመም ወቅት አመጋገብ

2. ኩላሊት እና ተግባሩ

ኩላሊት ለሰው አካል በጣም አስፈላጊ ከሚባሉ የአካል ክፍሎች ውስጥ አንዱ እና ዋነኛዉ ነው።

የኩላሊት ህመም ከከባድ ህመም እሰከ ሞት ሊያደረስ የሚችል አደጋ ሊያሰከትል ይችላል። ኩላሊት በጣም የተወሳሰበ መዋቅር እና ተግባር አለው።

ኩላሊቶቻችን ሁለት ወሳኝ ተግባራት በሰዉነታችን ዉስጥ ያከናዉናሉ፡-

 1. ጎጂ እና መርዛማ ምርቶችን ማስወገድ
 2. የውሃ ፣ ፈሳሾች ፣ ማዕድናት እና ኬሚካሎች ማለትም እንደ ሶዲየም ፣ ወዘተ ያሉ ኤሌክትሮላይቶችን ሚዛን ለመጠበቅ ያገለግላሉ።

የኩላሊት መዋቅር፡-

ኩላሊት መርዛማ የሆኑ የቆሻሻ ምርቶችን እና ከመጠን በላይ ውሃን ከሰውነት በማስወገድ ሽንትን ያመርታል። በእያንዳንዱ ኩላሊት ውስጥ የተሠራው ሽንት በፊኛ ኩልት ቱቦ ውስጥ ያልፋል ከዛም ወደ ፊኛ ይፈሳል በመጨረሻም በሽንት ቧንቧ አማካኝነት ከሰውነት ይወገዳል።

 • ብዙ ሰዎች ሁለት ኩላሊት አላቸው።
 • ኩላሊቶቹ በአከርካሪው በሁለቱም በኩል በሆድ የላይኛው እና የኋላ በኩል ይገኛሉ (ምስሉን ይመልከቱ)። የታችኛው የጎድን አጥንቶች ጉዳት እንዳይደርስባቸው ይከላከላሉ።
 • ኩላሊቶቹ በሆድ ውስጥ በጥልቀት ይገኛሉ፤ ስለሆነም በተለምዶ አንድ ሰው በእጁ ሊዳስሳቸው አይችልም።
 • ኩላሊት የባቄላ ቅርፅ ያላቸው የዉስጥ አካል ክፍሎች ናቸው። በአዋቂ ዎች ውስጥ አንድ ኩላሊት 10 .ሜ ቁመት ፣ 6 .ሜ ስፋት እና 4 . ውፍረት ያለዉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ኩላሊት በግምት ከ150-170 ግራም ይመዝናል።
 • በኩላሊቶች አማካኝነት የተሠራው ሽንት፤ በሽንት ቱቦዎች በኩል ወደ ሽንት ፊኛ ይወርዳል። እያንዳንዱ ሽንት በፊኛ ኩልት ቱቦ ወይም (ureter) 25 .ሜ ያህል ርዝመት ያለው ሲሆን በልዩ ጡንቻዎች የተሠራ ባዶ የሆነ ቱቦ መሰል መዋቅር አለው።
 • የሽንት ፊኛ ከጡንቻዎች የተሠራ ባዶ አካል ሲሆን በታችኛው እና የፊተ ኛው የሆድ ክፍል ውስጥ ይገኛል እንደ ሽንት ማጠራቅሚያ ያገለግላል።
 • የአዋቂ የሽንት ፊኛ ከ 400-500 ሚሊ ሊትር ሽንት ይይዛል። የመሸከም አቅሙ ለመሙላት ሲቃረብ አንድ ሰው ሽንት የመሽናት ፍላጎት ይሰማ ዋል። ሽንትን በማስወገድ ተፈጥሯዊ ሂድት ውስጥ በፊኛ ውስጥ የተጠ ራቀመው ሽንት በሽንት ቧንቧ በኩል ከሰውነት ይወገዳል። የሴቶች የሽንት ቧንቧ አጭር ሲሆን በአንጻሩ የወንዶች ረዘም ይላል።
 

ኩላሊት ለህይወት ምን ያህል አሰፈላጊ ነዉ?

 • በየቀኑ የተለያዩ አይነት ምግቦችን እንመገባለን፣ መጠጦችንም እንጠጣ ለን
 • በሰውነታችን ውስጥ ያለው የውሃ የጨው እና የአሲድ ብዛት እንዲሁ በየቀኑ ይለያያል
 • ምግብን ወደ ኃይል የመቀየር ሂደት ውስጥ ሰውነታችን አደገኛ እና መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ያመርታል
 • እነዚህ ሂደቶች በሰውነት ውስጥ ባለው ፈሳሽ በኤሌክትሮላይቶች እና በአሲዶች መጠን ላይ ለውጥ ያስከትላሉ
 • የማይፈለጉ መርዛማ ቁሳቁሶች መከማቸት ለሕይወት አስጊ ሊሆን ይችላል
 • እያንዳንዱ ኩላሊት ጎጂ እና መርዛማ የሆኑ ተረፈ ምርቶችን የማውጣት ስራን ያከናውናሉ
 • በተመሳሳይ ጊዜ የውሃ የአሲድ እና የንጥረነገሮች ትክክለኛ ሚዛን እና ደረጃዎች ይቆጣጠራሉ እንዲሁም ይጠብቃሉ

የኩላሊት ዋነኛ ተግባራት ምንድን ናቸው?

የኩላሊት ዋና ተግባር ሽንት መስራት እና ደምን ማጥራት ነው። እያንዳንዱ ኩላሊት ቆሻሻ ንጥረ ነገራትን እንዲሁም ሌሎች የማይፈለጉ ኬሚካሎችን ያስወግዳል።

የኩላሊት አስፈላጊ ተግባራት ከዚህ በታች ተብራርተዋል -

1. የቆሻሻ ምርቶችን ማስወገድ

የቆሸሹ ምርቶችን በማስወገድ የደም ንፅህናን መጠበቅ በጣም አስፈላጊው የኩላሊት ተግባር ነው። የምንመገበው ምግብ በውስጡ ፕሮቲን ይይዛል፤ ይህ ፕሮቲን ለሰውነት እድገት እና ጥገና በጣም ወሳኝ ነው፤ ነገር ግን ፕሮቲን በሰውነት ውስጥ ጥቅም ላይ ከዋለ በኋላ ቆሻሻ ምርቶችን ያመርታል። የእነዚህ ቆሻሻ ምርቶች መከማቸት እና መቆየት በሰውነት ውስጥ መርዝን ማቆየት አንደማለት ነው። እያንዳንዱ ኩላሊት ደም እና የቆሻሻ ምርቶችን አጣርቶ በሽንት በኩል ከሰውነታችን ያስወግዳል።

ክሬቲኒን እና ዩሪያ በደም ውስጥ በቀላሉ ሊለኩ የሚችሉ ሁለት አስፈላጊ የቆሻሻ ምርቶች ናቸው። ሁለቱም ኩላሊቶች ሲደክሙ በደም ምርመራ የሚለካው የክሬቲኒን እና የዩሪያ መጠን ከፍተኛ ይሆናል።

2. ከመጠን በላይ ፈሳሽ ማስወገድ

ሁለተኛው እና በጣም አስፈላጊዉ የኩላሊት ተግባር፤ የሰውነታችንን የፈሳሽ ሚዛን መጠበቅ ነው። በሰውነት ውስጥ አስፈላጊ የሆነውን የውሃ መጠን በመቆጣጠር እናም ከመጠን በላይ የውሃ መጠን በሽንት መልክ በማስወገድ ይሄንን ተግባር ያከናውናሉ። ኩላሊቶቹ ሲደክሙ ይህንን ከመጠን በላይ ውሃ የማስወገድ ችሎታ እያጠራቸዉ ይመጣል፤ ይህንን ተከትሎ በሰውነት ውስጥ ከመጠን በላይ የፈሳሽ ክምችት በመፈጠር ለሰውነት እብጠት ይዳርጋል።

3. የማዕድን እና ኬሚካሎች ሚዛን መጠበቅ

ኩላሊት እንደ ሶዲየም ፖታሲየም ሃይድሮጂን ካልሲየም ፎስፈረስ ማግኒThየም እና ባይካርቦኔት ያሉ ማዕድናትን እና ኬሚካሎችን የመቆጣጠር ጠቃሚ ሚናም የሚጫወት የሰዉነታችን አካል ነዉ። በሶዲየም መጠን ላይ የሚታዩ ለውጦች በሰው ልጅ የዓእምሮ ሁኔታ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳርፉ ይችላሉ። በፖታስየም መጠን ላይ የሚከሰቱ ለውጦች በልብ ምት ላይም ሆነ በጡንቻዎች ላይ ከባድ ጉዳት ያደርሳሉ። የካልሲየም እና ፎስፈረስ መደበኛ መጠናቸው መጠበቅ ለጤናማ አጥንት እና ጥርስ አስፈላጊ ነው።

4. የደም ግፊትን መቆጣጠር

ኩላሊቶች የተለያዩ ሆርሞኖችን ያመነጫሉ (ሬኒን አንጂዮቴንሲን አልዶስቴሮን ፕሮስታጋላንዲን ወዘተ) እንዚህ ሆርሞኖች ጥሩ የደም ግፊት ቁጥጥር ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። ከዚህም በተጨማሪ በሰውነት ውስጥ የውሃ እና ጨው ቁጥጥር ለመጠበቅ እና ለማመጣጠን ይረዳሉ።

5. የቀይ የደም ሴሎች ማምረት

ኤሪትሮፖይቲን በኩላሊቶች ውስጥ የሚመረተው ሌላ ሆርሞን ነው። ቀይ የደም ሴሎችን በማምረት ረገድ ጠቃሚ ሚና ይጫወታል። በኩላሊት ድካም ወቅት የኤሪትሮፖይቲን ምርት ይቀንሳል። ይህ ደግሞ የቀይ የደም ሴሎችን ምርት እንዲቀንስ ያደርገዋል። ይህም ለደም ማነስ ይዳርጋል። ለኩላሊት ችግር የተዳረጉ ታማሚዎች ላይ የደም ማንስ ችግር ሲፈጠር፤ በአይረን እና በቫይታሚን አማካኝነት ማይሻሻልበት ምክንያትም ይኸዉ ነው።

6. ጤናማ አጥንቶችን ለመጠበቅ

ኩላሊቶቹ ቫይታሚን ዲን ወደ ገባሪነቱ ይለውጣሉ።ይህም ከምግብ ውስጥ ካልሲየምን ነጥሎ ለማው ጣት ይጠቅማል ፣ አጥንቶች እና ጥርስ እዲያድጉ እንዲሁም አጥንቶች ጠንካራ እና ጤናማ እንዲሆኑም ያደርጋሉ። በኩላሊት ድክመት ወቅት ገባሪ የሆነ የቫይታሚን ዲ መጠን መቀነስ፣ የአጥንቶች እድገት እንዲያቆም እንዲሁም አጥንቶች ደካማ እንዲሆኑ ያደርጋል። ልጆች ላይ የሚታይ የእድገት መዘግየት የኩላሊት መድከም ምልክት ሊሆን ይችላል።

ደም እንዴት ይጣራል፤ ሽንትስ እንዴት ይፈጠራል?

በደም ማጣሪያ ሂደት ውስጥ ኩላሊቶቹ ሁሉንም አስፈላጊ ንጥረ ነገሮችን ይዘው ከመጠን በላይ ፈሳሾችን ንጥረ ነገሮችን እና የቆሻሻ ተረፈ ምርቶችን በማጣራት ያስወግዳሉ።

ይህን ድንቅ እና የተወሳሰበ ሂደት እንመልከት።

 • በየደቂቃው 1200 ሚሊ ሊትር ደም ወደ ኩላሊት ውስጥ ለመጽዳት ይገባል። ይህም ከልብ ከሚወጣው አጠቃላይ ደም 20% ያህሉን ይይዛል። ስለዚህ በአንድ ቀን ውስጥ 1700 ሊትር ደም ይጠራል።
 • ይህ የመንጻት ሂደት ኔፍሮንተብለው በሚታወቁት አነስተኛ የማጣሪያ ክፍሎች ውስጥ የሚከናወን ነዉ።
 • እያንዳንዱ ኩላሊት አንድ ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑ ኔፍሮኖችንበውስጡ ይይዛል። እያንዳንዱ ኔፍሮን በግሎሜሩልስእና ትዩብዩልስየተሰራ ነው።
 • ግሎሜሩለስ በጣም ጥቃቅን ቀዳዳዎች ያሉት ማጣሪያ ነዉ። ውሃ እና አነ ስተኛ መጠን ያላቸው ንጥረ ነገሮች በቀላሉ በቀዳዳዎቹ ማለፍ ይችላሉ። ነገር ግን ትልቅ መጠን ያላቸው ቀይ የደም ሴሎች ነጭ የደም ሴሎች ፣ ፕሌትሌቶች ፣ ፕሮቲን ወዘተ በእነዚህ ቀዳዳዎች ውስጥ ማለፍ አይች ሉም። ስለዚህ እንደዚህ ያሉ ህዋሶች በመደበኛነት በጤናማ ሰዎች ሽንት ውስጥ አይታዩም።
 • የሽንት መፍጠሪያ የመጀመሪያው ደረጃ በ በግሎሜሩልስውስጥ ይከሰ ታል። ቆሻሻ ምርቶችን ኤሌክትሮላይቶችን እና መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ብቻ ሳይሆን ግሉኮስ እና ሌሎች ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን ይይዛል።
 • ወደ ቱቦዎች ውስጥ ከገባ 180 ሊትር ፈሳሽ ውስጥ 99% ፈሳሽ በተመ ረጠ ሁኔታ ወደሰውነት የሚመለስ ሲሆን ቀሪው 1% ፈሳሽ በሽንት መልክ ይወገዳል።
 • በዚህ ብልህ ሂደት ሁሉም አስፈላጊ ንጥረ ነገሮች እና 178 ሊትር ፈሳሽ በትዩብዩሎች ውስጥ ወደሰውነት ይመለሳሉ። 1-2 ሊትር ፈሳሽ ፣ የቆሻሻ ውጤቶች እና ሌሎች ጎጂ ንጥረ ነገሮች ደግሞ ይወገዳሉ።

 ጤነኛ ኩላሊት ያለው ሰው በተለያዩ ጊዜያት የተለያየ የሽንት መጠን ሊኖረው ይችላል?

 • አንድ ሰው የሚጠጣው የውሃ መጥን ሲቀንስ ወይም በሞቃታማ ወቅት ላይ፤ ኩላሊት በሰውነት ውስጥ ያለውን የውሃ መጠን ለመጠበቅ የሚመ ረተውን የሽንት መጠን ይቀንሳል።
 • በተቃራኒ ደግሞ አንድ ሰው የሚጠጣውን የውሃ መጠን ሲጨምር ወይም በቅዝቃዜ ወቅት የሚመረተው የሽንት መጠን ይጨምራል።
 • በጤነኛ ሰው ላይ ሽንት ከ500ኤም.ኤል በታች ወይም ከ3000 ኤም.ኤል በላይ ሲሆን የኩላሊት ችግር እንዳይሆን ክትትል ያስፈልገዋል።