Read Online in Amharic
Table of Content
መግቢያ እና ይዘቶች
መሰረታዊ መረጃ
የኩላሊት መድከም
ሌሎች ዋና ዋና የኩላሊት ህመሞች
የኩላሊት ህመም ወቅት አመጋገብ

መግቢያ እና ይዘቶች

 

ለኩላሊት ህመምተኞች የተሟላ ማስተማርያ

ኩላሊትዎን ይታደጉ

አጠቃላይ መረጃ ስለ የኩላሊት ህመሞች መከላከያ እና ህክምና

 

በመጀመሪያ የተፃፈው / ሳንጃይ ፓንዲያ ኤም.. .ኤን.. (ኔፊሮሎጂ)

ራጅኮት ህንድ

የአማርኛ ትርጉም ደራሲ / እሴተ ጌታቸው ኤም.. ኢትዮጵያን ኪድኒ ኬር ዋና ሥራ አስኪያጅ እና መስራች

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

 

መጽሐፉን በዋኛነት በመተርጎም የረዱ

 • ህሊና ከበረ ተክለሀይማኖት- የህክምና ተማሪ
 • ምህረት ሰለሞን ተስፋዬ-የህክምና ተማሪ
 • ሆሳዕና ገብሩ በርሄ- የህክምና ተማሪ
 • አቤል ዮሐንስ በለጠ-የህክምና ተማሪ
 • እፀገነት መኩሪያ አዲስ- የህክምና ተማሪ
 • ልደት ኤፍሬም ገብረእግዚአብሔር- የህክምና ተማሪ
 • ቅድስት ነጋ አራጋው- የህክምና ተማሪ
 • ቤቴልሔም ታምራት አቦዬ- የህክምና ተማሪ
 • ሔርሜላ ስንታየው ይርዳው-ማኔጀር

 

ዋና ኤዲተር

ሀይለሚካኤል አበበ መስፍን-ጋዜጠኛ

በኤዲቲንግ የረዱ

ሲስተር ሀና ሳምሶን ለገሰ-የምግብ ባለሙያ አምደስላሴ አማረ ፈለቀ-የትምህርት ባለሙያ አማኑኤል አድማሱ ደሳለኝ-ኢንጅነር

/ እየሩሳሌም አበራ ኣራጋው-የሕክምና ባለሙያ ቤተልሄም ቦጋለ የሺጥላ-የህክምና ተማሪ


 

 

ኩላሊትዎን ይታደጉ

አሳታሚ

ሳማርፓን ኪድኒ ፋውንዴሽን የሳማርፓን ሆስፒታል ቡቱካና ቾክ ራጅኮት 360002 (ጉጅራት ህንድ)

-ሜል: [email protected]

 

© ሳማርፓን ኪድኒ ፋውንዴሽን

ሁሉም መብቶች ተጠብቀዋል። የትኛውም የዚህ መጽሐፍ ክፍል በማንኛውም መልክ ወይም በኤሌክትሮኒክ ሊባዛ አይችልም። የመረጃ ማከማቻ እና መልሶ ማግኘትን ጨምሮ ማንኛውም ኤሌክትሮኒክ ወይም ሜካኒካዊ መንገዶች ጨምሮ ያለአሳታሚ የጽሑፍ ፈቃድ ሳይኖር ማሳተም አይቻልም። ይህ መጽሐፍ በህንድ ውስጥ የሚታተም እና ያለ አሳታሚው ቅድመ ጽሑፍ ፍቃድ መላክ አይቻልም። አለመስማማት በሚኖርበት ጊዜ ሁሉም ህጋዊ ጉዳዮች በራጅኮት ስልጣን ስር ብቻ እልባት ሊያገኙ ይችላሉ።

 

ጸሀፊዎች:

/ እሴተ ጌታቸው ኤም..

ኢትዮጵያን ኪድኒ ኬር ዋና ሥራ አስኪያጅ እና መስራች አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

 

/ ሳንጃይ ፓንዲያ - ኤም.. ዲኤንቢ (ኒፎሮሎጂ)

የሳምፓን ሆስፒታል ቡቱካና ቾክ ራጅኮት 360002 (ጉጅራት, ህንድ)


   

  

 

ይህ መጽሐፍ ለሁሉም የኩላሊት ህመምተኞች እና ለቤተሰቦቻቸው የተዘጋጀ ነው።


 

  

 

የርዕስ ማውጫ

ክፍል 1 ስለ ኩላሊት መሰረታዊ መረጃ

 1. መግቢያ
 2. ኩላሊት እና ተግባሩ
 3. የኩላሊት ህመም ምልክቶች
 4. የኩላሊት ህመሞች ምርመራዎች
 5. ዋና ዋና የኩላሊት ህመሞች
 6. ስለ ኩላሊት ህመሞች ትክክል ያልሆኑ አመለካከቶች እና እውነታዎች
 7. የኩላሊት ህመም መከላከያዎች

ክፍል 2 ዋና ዋና የኩላሊት ህመሞች እና ህክምናቸው
የኩላሊት መድከም

 1. የኩላሊት መድከም ምንድነው?
 2. አጣዳፊ የኩላሊት መድከም
 3. ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም መንስኤዎች
 4. ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም ምልክቶች እና ምርመራ
 5. ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም: ሕክምና
 6. የኩላሊት እጥበት
 7. የኩላሊት ንቅለ ተከላ

ሌሎች ዋና ዋና የኩላሊት ህመሞች

 1. ከስኳር ህመም ጋር የተዛመደ የኩላሊት ህመም
 2. ፖሊሲስቲክ የኩላሊት ህመም
 3. ከአንድ ኩላሊት ጋር መኖር
 4. የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን
 5. የኩላሊት ጠጠር ህመም
 6. የፕሮስቴት እጢ ህመም
 7. ኩላሊት እና መድኃኒቶች
 8. ኔፍሮቲክ ሲንድሮም
 9. የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ልጆች ላይ
 10. በልጆች ላይ የሚከሰት በማታ ሽንት አለመቆጣጠር ችግር

የኩላሊት ህመም ወቅት አመጋገብ

 1. ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም ወቅት አመጋገብ
 2. የቃላት መፍቻ
 3. ለኩላሊት ህመምተኞች የተለመዱ የደም ምርመራዎች

 

 

 

ወደ አማርኛው እትም መግቢያ

የመጀመሪያውን “ኩላሊትዎን ይታደጉ” እትም ዶ/ር ሳንጃይ ፓንዲያ መሠረታዊ የተለመዱ የኩላሊት ህመሞችን ለመከላከል መመሪያዎች እና ግንዛቤን የሚሰጥ መጽሐፍ ለመጻፍ አልመው የተጻፈ ሲሆን በተቃራኒ ከተለመደው የኔፍሮሎጂ ጽሑፎች ይህ መጽሐፍ በዋነኝነት የተጻፈው ለጤና ባለሙያ ላልሆነው ሰው ነው።

ይህ የአማርኛው እትም የበጎ ፈቃደኞች ትብብር ሥራ ውጤት ሲሆን ህብረተሰቡ የበለጠ የኩላሊት ህመሞችን የሚመለከቱ የተለያዩ ጉዳዮችን ላይ ያላቸውን እውቀት ለማጎልበት አላማ አለው። በኢትዩጵያ ላይ እየጨመረ ያለውን የኩላሊት ህመም ለመቀነስ ታስቦ የተተረጎመ መጽሐፍ ነው።

በሁለት ክፍሎች የተከፈለ ነው። የመጀመሪያው ክፍል ‹መሰረታዊ የኩላሊት መረጃ› ላይ በማጠንጠን አንባቢው የኩላሊት መደበኛ አወቃቀር እና ተግባር ላይ ግንዛቤ ያስጨብጣል እንዲሁም በርካታ ቴክኒካል ቃላቶች አጠቃቀም ጋር ያስተዋውቃል። ሁለተኛው ክፍል የበለጠ ከኩላሊት ጋር ተያያThነት ያላቸው ዝርዝር ጉዳዮችን ይመለከታል ለምሳሌ.፣ አጣዳፊ የኩላሊት ጉዳት ፣ ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም ፣ የስኳር ህመም ፣ ኩላሊት እጥበት፣ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ወዘተ. ያካትታል።

የመጨረሻው ምዕራፍ የዶክተር ፓንዲያ የራሱ ስራ የሆነው ስለ ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም ወቅት አመጋገብን ይዳስሳል።

መታወቅ ያለበት የአመጋገብ ሃሳቦቹ በተለያዩ ባህል ልዩነቶች ምክንያት የግድ ለሁሉም ህብረተሰብ በአጠቃላይ ተተግባሪ ላይሆኑ እናደሚችሉ መገንዘብ ያስፈልጋል። በመጽሐፉ ውስጥ አንባቢያን ሲያነቡ በጣም ጠቃሚ ሆኖ ሊያገኞቸው የሚችሉአቸው አሕጽሮተ ቃል እና የቃላት መፍቻም ተካትቷል።

በዚህ መጸሀፍ ላይ በመተርጎም እና በኤዲቲኝግ ለተሳተፉት ሁሉ ማመስገን እወዳለሁ።

"እንደ ጠቢብ ሰው ያስቡ ግን በሰዎች ቋንቋ ይግባቡ።"
- ዊሊያም በትለር ይትስ

ዶ/ር እሴተ ጌታቸዉ
ጠቅላላ ሐኪም
የኢትዮጵያን ኪድኒ ኬር መሥራች እና ዋና ሥራ አስኪያጅ አዲስ አበባ

 

 

ወደ መጀመሪያ እትም መግቢያ
የኩላሊት ህመሞችን እንከላከል...

ይህ “ኩላሊትዎን ይታደጉ” የሚለው መጽሐፍ የተለመዱ የኩላሊት ህመሞች ላይ መሠረታዊ ግንዛቤን ለማስጨበጥ እና መከላከያ መመሪያዎች ለመስጠት የሚደረግ ጥረት ነው።

በአለፉት ጥቂት አስርት ዓመታት ውስጥ በአስገራሚ እና አስደንጋጭ ሁኔታ የኩላሊት ህመሞች በሚከሰቱበት አጋጣሚዎች ጭማሪ አሳይቷል። ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም የተለመደ እና የማይድን ነው። በመንስኤዎቹ ፣ ምልክቶቹ እና እርምጃዎቹ ላይ ግንዛቤ ማዳበር ይህንን አስከፊ ህመም ለመከላከል በጣም ጥሩው መንገድ ነው። ይህን መጽሐፍ በቀላሉ የጤና ባለሙያ ሰው በቀላሉ እንዲረዳ በቀላል ቃላት ያዘጋጀነው የትህትና ሙከራችን ነው።

የዚህ ህመም ቅድመ ምርመራ እና በጊዜ ሕክምና ማግኘት የረጅም ጊዜ ጥቅሞች በዝቅተኛ ዋጋ ለማግኘት ጠቃሚ ነው። በግንዛቤ እጥረት ምክንያት በጣም ጥቂቶች ናቸው የኩላሊት ህመም የመያዝ እድልን የሚያመለክቱ ምልክቶችን በቅድሚያ የሚገነዘቡት ይህም በቅድመ ምርመራ ላይ አደገኛ መዘግየት ያስከትላል። እንደ ኩላሊት እጥበት እና ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም ሕክምና እጅግ ውድ እና እንደ ህንድ ባለ ሀገር ውስጥ አቅም ያላቸው ታካሚዎች ከ 10% በታች ናቸው ስለሆነም በሀገራችን ቀደም ብሎ ምርመራ እና ሕክምናው ማግኘት ብቸኛው እና የችግሩ መቀነሻ አማራጭ ነው።

በምርመራ አንድ ሰው በኩላሊት ህመም እየተሰቃየ መሆኑን ሲያሳይ ህመምተኛው እና ቤተሰቡ በጣም ከባድ ጭንቀት ውስጥ ይወድቃሉ። ህመምተኞች እና የቤተሰብ አባሎቻቸው ስለ ኩላሊት ህመም ማወቅ ይፈልጋሉ ግን ለታካሚው ሐኪሙ ብዙ ማብራሪያ በግልጽ ማቅረብ አይችልም። ይህ መጽሐፍ በታካሚው እና በዶክተሩ መካከል የጎደለው ማብሪሪያ እንደሚያቀርብ ተስፋ እናደርጋለን።

የሆነ ሆኖ ይልቁንስ በተገቢው ጊዜ ለማንበብ እና እንደ አስፈላጊነቱ ደጋግመው ይመልከቱት ዘንድ መረጃ ሰጭ መጽሐፍ መኖሩ ጠቃሚ ነው። ስለ የተለያዩ የኩላሊት ምልክቶች ፣ ምርመራዎች ፣ መከላከል እና ህክምና ሁሉ መሠረታዊ መረጃዎች በቀላል እና በቀላል ቋንቋ ስለ ህመሞዎች ይሰጣል።

ለተለያዩ የኩላሊት ህመሞች የአመጋገብ ምክሮችንም እንዲሁ ያካትታል። እዚህ በግልጽ ሁኔታ መግለፅ ያለብን ነገር በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተሰጠው መረጃ የህክምና ምክር እንዳልሆነና ለማስተማሪያ ዓላማ ነው። በራስ መድሃኒት መውሰድ ወይም የአመጋገብ ማሻሻያ ያለ ባለሙያ ምክር መጽሐፉን ብቻ በማንበብ አደገኛ ሲሆን አይመከርም።

ይህ የኩላሊት ማስተማሪያ ለኩላሊት ህመምተኞች እና ለቤተሰቦቻቸው ብቻ ሳይሆን ጥቅሙ የኩላሊት ህመም የመያዝ እድል ላላቸው ሰዎች ጭምር ነው። በተጨማሪም የትምህርት ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለው ግንዛቤን ከፍ ማድረግ ለሚሹ ግለሰቦች እና የሕክምና ተማሪዎች ፣ ሐኪሞች ፣ የህክምና ባለሙያዎች ይህንን መጽሐፍ ምቹ የማጣቀሻ መመሪያ መጽሀፍ ሆኖ እንደሚያገኙት እርግጠኛ ነን።

አንባቢዎች ይህንን መጽሐፍ ጠቃሚ እና መረጃ ሰጭ ሆኖ እንደሚያገኙት ተስፋ አደርጋለሁ።

ይህንን መጽሐፍ የበለጠ ለማሻሻል አስተያየቶችን ሁል ጊዜም በደስታ እንቀበላለን። ለሁላችሁም ጤንነት እመኛለሁ።

ዶክተር ሳንጃይ ፓንዲያ
ራጅኮት ፣ ህንድ