Read Online in Amharic
Table of Content
መግቢያ እና ይዘቶች
መሰረታዊ መረጃ
የኩላሊት መድከም
ሌሎች ዋና ዋና የኩላሊት ህመሞች
የኩላሊት ህመም ወቅት አመጋገብ

16. ፖሊሲስቲክ የኩላሊት ህመም

የጂን የበላይነት ያለው ፖሊሲስቲክ የኩላሊት ህመም (....) በጣም የተለመደ የጄኔቲክ የበላይነት ያለው በዘር የሚተላለፍ የኩላሊት ህመም ነው። የበላይነትማለት ከህመሙጋር ተያያThነት ያለውን ጂን አንድ ቅጅ ብቻ ህመሙን ለማምጣት በቂ ሲሆን ይህም የበሽታውን መከሰት እድል ከፍ ያደርገዋል። ፒ..ዲ በኩላሊቶች ውስጥ ብዙ የቋጠሩ እጢዎች በመኖራቸው ይታወቃል። ፖሊሲስቲክ የኩላሊት ህመም (..) ሥር ለሰደደ የኩላሊት ህመምአራተኛ መንስኤ ነው። በዚህ ህመም ውስጥ የቋጠሩ እጢዎች የሚታዩባቸው ሌሎች አካላት ጉበት ፣ አንጎል ፣ አንጀት ፣ ቆሽት ኦቫሪ እና የሀሞት ከረጢት ናቸው።

የፖሊሲስቲክ የኩላሊት ህመም (..) ስርጭቱ እንዴት ነው?

የፒ... መከሰት በሁሉም ዘሮች ተመሳሳይ ነው በወንዶች እና በሴቶች ላይ በእኩል የሚከሰት ሲሆን በዓለም ዙሪያ 1 ሺህ ሰዎች ውስጥ 1 ያህሉን ይነካል። የኩላሊት እጥበት ወይም የኩላሊት ንቅለ ተከላ ከሚያስፈልጋቸው ሁሉም ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመምተኞች 5% የሚሆኑት ... አላቸው።

በፒ.. ህመምተኛ ውስጥ ያለው ኩላሊት ላይ ምን ተጽዕኖ ይታይበታል?

 • በኤ.... ውስጥ በርካታ የቋጠሩ (በፈሳሽ የተሞሉ) ከረጢቶች በሁለቱም ኩላሊት ውስጥ ይታያሉ።
 • በፒ... ውስጥ የእጢዎቹ መጠኖች ተለዋዋጭ ናቸው (2.4 ሚሜ እስከ እስከ 10 . ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ስፋት ሊኖራቸው ይችላል)
 • ከጊዜ በኋላ የቋጠሩ እጢዎቹ መጠን በመጨመራቸው ምክንያት ጤናማ ኩላሊቱን በዝግታ መጭመቅ እና መጉዳት ይጀምራሉ።
 • እንዲህ ያለው ጉዳት ወደ ከፍተኛ የደም ግፊት ፣ በሽንት ውስጥ የፕሮቲን መኖር እና የኩላሊት ሥራን በመቀነስ ሥር የሰደደ የኩላሊት በሽታ መከሰ ትን ያስከትላል።
 • በረጅም ጊዜ (ከዓመታት በኋላ) ሥር የሰደደ የኩላሊት መበላሸት እየተ ባባሰ ወደ ከባድ የኩላሊት ውድቀት (መጨረሻ ደረጃ ላይ የደረሰ የኩላ ሊት በሽታ) ያስከትላል ፣ በመጨረሻም የኩላሊት እጥበት ወይም የኩላ ሊት ንቅለ ተከላ ይፈልጋል።

የፒ..ዲ ምልክቶች

.... ያላቸው ብዙ ሰዎች የህመሙ ምልክቶችን ሳያሳዩ ለብዙ አሥርተ ዓመታት ይኖራሉ። አብዛኛዎቹ የፒ..ዲ ሕመምተኞች ከ 30 እስከ 40 ዓመት ዕድሜ ካለፋቸው በኋላ የሕመም ምልክቶችን ያሳያሉ። የፒ.. የተለመዱ ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው።

 • ከፍተኛ የደም ግፊት።
 • በጀርባ ላይ ህመም በአንዱ ወይም በሁለቱም በኩል የጎን ህመም እና / የሆድ እብጠት መኖር።
 • በሆድ ውስጥ ትልቅ እብጠት መኖር ስሜት።
 • በሽንት ውስጥ ደም ወይም አረፋ (ፕሮቲን)መታየት።
 • ተደጋጋሚ የሽንት ኢንፌክሽን እና የኩላሊት ጠጠር መኖር።
 • ከጊዜ ወደ ጊዜ የኩላሊት ሥራን በማጣት ምክንያት ሥር የሰደደ የኩላ ሊት ህመም ምልክቶች መታየት።
 • ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ውስጥ እንደ አንጎል ፣ ጉበት ፣ አንጀት ባሉ የቋጠሩ እጢዎች ምልክቶች መታየት።
 • የፒ..ዲ ህመምተኛ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮች የአንጎል ደም ስር መወጠር ፣ የሆድ ግድግዳ መላላት ፣ የጉበት የቋጠሩ እጢዎች መበከል እና ኢንፌክሽን መፈጠር የትልቅ አንጀት እና በልብ ቫልቭ ችግሮች ናቸው። ወደ 10% የሚሆኑት የፒ..ዲ ህመምተኞች የአንጎል ደም ስር መወጠር ያዳብራሉ። የአንጎል ደም ስር መወጠር አንጎል ውስጥ እብጠትን ያስከት ላል። ይሄም ራስ ምታትን እናም ደም ስሩን በመበጠስ ለስትሮክ ደም ምት አልፎ ተርፎም ለሞት ሊዳርግ ይችላል።

.. ያለበት እያንዳንዱ ሰው የኩላሊት ውድቀት ያጋጥመዋል?

የለም፤ የፒ..ዲ ህመም ባለባቸው ታካሚዎች ሁሉ የኩላሊት ሽንፈት አይከሰትም። 50% የሚሆኑት የፒ..ዲ ሕመምተኞች እስከ 60 ዓመት ዕድሜ ድረስ የኩላሊት ሽንፈት አለባቸው ፣ 60 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ እስከ 70 ዓመት ዕድሜ ድረስ የኩላሊት ድክመት ይኖርባቸዋል። የፒ..ዲ ህመም ባለባቸው ህመምተኞች የህመሙ እድገት የመከሰቱ ዕድል በሚከተሉት ሁኔታዎች ይወሰናል።

ትልቅ የኩላሊት መጠን ፣ በምርመራ ወቅት ወጣት ዕድሜ ፣ የደም ግፊት (በተለይም ዕድሜው ከ 35 ዓመት በፊት በሆነ ሰው) ፣ በሽንት ውስጥ ፕሮቲን መኖር (> 300 . / በቀን) በሽንት ውስጥ ብዙ ደም መኖር የወንዶች ፆታ > 3 እርግዝና የተወሰኑ የጄኔቲክ ችግሮች እንዲሁም የትምባሆ ፍጆታ።

የፒ.. ምርመራ

የሚከተሉት ለኤ.... ህመምተኛ የሚደረጉ ዋና ምርመራዎች ናቸው።

 • የኩላሊት አልትራሳውንድ:- ይህ ለፒ..ዲ በጣም በተለምዶ ጥቅም ላይ የሚውለው የምርመራ ነው ምክንያቱም አስተማማኝ ፣ ቀላል ፣ ደህ ንነቱ የተጠበቀ ህመም የሌለው አነስተኛ ዋጋ ያለው እና በኩላሊቶች ውስጥ የቋጠሩትን እጢዎች በቀላሉ የሚለይ ምርመራ ስለሆነ ነው።
 • ሲቲ ወይም ኤም.አር.አይ ምርመራ:- እነዚህ ሙከራዎች ይበልጥ ትክ ክለኛ ውጤት ቢሰጡም ውድ ናቸው። እነዚህ ምርመራዎች በአልትራሳው ንድ ሊመረመሩ የማይችሉ ትናንሽ የቋጠሩ እጢዎችን ሊያገኙ ይችላሉ።
 • የቤተሰብ ምርመራ:- ..ዲ በዘር የሚተላለፍ ህመም ሲሆን እያንዳ ንዱ ልጅ በህመሙ የመያዝ እድሉ 50 በመቶ ነው። ስለዚህ የፒ.. ህመምተኛ የቤተሰብ አባላት ምርመራ ቀድሞ ቢደረግ ይረዳል።
 • ..ዲ በኩላሊት ላይ ያለውን ተፅዕኖ ለመገምገም የሚደረጉ ምርምራዎች:- በሽንት ውስጥ የደም ወይም የፕሮቲን እንዳለ ለማወቅ የሚደረግ የሽንት ምርመራ አንዱ ነው። የኩላሊቱን ተግባር ለመገምገም እና ለመቆጣጠር ለክሪእትኒን የደም ምርመራ ይደረጋል።
 • የአጋጣሚ ምርመራ:- ..ዲ በተለመደ የጤና ምርመራ ወይም በሌላ ምክንያት በተደረገው የአልትራሳውንድ ምርመራ ወቅት ሊታወቅ ይችላል።
 • የጂን ትስስር ምርመራ:- ይህ በጣም ልዩ የሆነ የደም ምርመራ ነው የትኛው የቤተሰብ አባል የፒ..ዲን ጂን እንደሚሸከም ለመለየት ይጠቅ ማል። ይህ ምርመራ መደረግ ያለበት ሲቲ እና ኤም.አር.አይ ምርመራዎች ምንም ካላሳዩ ብቻ ነው። ይህ ሙከራ በጣም በጥቂቱ ማዕከላት የሚገኝ እና በጣም ውድ ስለሆነ የሚከናወነው አልፎ አልፎ ብቻ ነው።

የፒ..ዲ ህመምተኞች የትኞቹ የቤተሰብ አባላት የፒኬዲ ምርመራ ማደረግ አለባቸው?

የፒ..ዲ ሕመምተኞች ወንድሞች ፣ እህቶች እና ልጆች ለፒ..ዲ ምርመራ ማድረግ አለባቸው። በተጨማሪም በሽታውን ለታካሚው ያወረሱት ወላጆች ፣ የወላጆች የቅርብ ሰጋ ዘመዶች ምርመራ ሊደረግላቸው ይገባል።

ሁሉም የፒ.. ህመምተኞች ልጆች ተመሳሳይ ህመም የመያዝ አደጋ አላቸው?

እይ ፒ..ድ በዘር የሚተላለፍ ህመም ሲሆን እናት ወይም አባት የጂን የበላይነት ያለው ፒ..ድ ካለባቸው ልጆቹ ህመሙን የመያዝ እድላቸው 50% ነው።

የፖሊሲስቲክ የኩላሊት ህመም መከላከል

..ዲን ለመከላከል ምን ማድረግ ይቻላል?

በአሁኑ ጊዜ በፒ.. ውስጥ የቋጠሩ እጢዎችን ከመከሰት ወይንም ከማደግ የሚከላከል ህክምና የለም።

የቤተሰብ አባላትን አጣርቶ ህመሙ ከመጀመሩ በፊት ቅድመ ምርመራ ማድረግ ብዙ ጥቅሞች አሉት። ቅድመ ምርመራ ፒ..ዲን በተሻለ መንገድ ለማከም እድል ይሰጣል። የከፍተኛ የደም ግፊት ቅድመ ምርመራ እና ሕክምና በፒ..ዲ ውስጥ ከባድ የኩላሊት ህመም መከሰትን ወይም መባባስን ይከላከላል።

በፒ.. ህመምተኞች የአኗኗር ዘይቤ እና የአመጋገብ ማስተካከል ኩላሊታቸውን እንዲሁም ልብን ይጠብቃል። የማጣራት ዋነኛው ኪሳራ ሊሆን የሚችለው ግለሰቡ ምልክቶቹ ሳይኖርበት ወይም ምንም ዓይነት ህክምና በማይፈልግበት ደረጃ ላይ ስለበሽታው በጣም አብዝቶ ይጨነቅ ይሆናል።

የፒ..ዲን ክስተት ለመቀነስ ለምን አልተቻለም?

..ዲ ብዙውን ጊዜ የሚገኘው ዕድሜው 40 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ በሆነ ሰው ላይ ነው። ብዙ ሰዎች ከዚህ እድሜ በፊት ልጆች ስለሚኖራቸው ወደ ቀጣዩ ትውልድ እንዳይተላለፍ መከላከል አይቻልም።

የፒ.. ሕክምና

.. የማይድን ህመም ሆኖም ለምን ህክምና ይፈልጋል?

 • የኩላሊት ህመሙን ለመከላከል እና ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም እድ ገትን ለማዘግየት ማለትም የኩላሊት ህመሙ እንዲይባባስ እና በዚህም ህመምተኛ እንዲተርፍ ያደርጋል።
 • ምልክቶቹን ለመቆጣጠር እና ውስብስብ ችግሮችን ለመከላከል።

በፒ.. ሕክምና ውስጥ አስፈላጊ እርምጃዎች:-

 • ከመጀመሪያው ምርመራ በኋላ ታካሚው ለብዙ ዓመታት የህመሙ ምልክት አያሳይም እናም ምንም ዓይነት ህክምና አያስፈልገውም። ነገር ግን እንደነዚህ ያሉት ታካሚዎች ወቅታዊ ምርመራ እና ክትትል ያስፈልጋ ቸዋል።
 • ከፍተኛ የደም ግፊት ላይ የሚደረግ ጥብቅ ቁጥጥር፤ የመጨረሻ ደረጃ የኩላሊት ህመም እድገትን ያዘገየዋል።
 • ኩላሊቱን በማይጎዱ መድኃኒቶች ህመምን መቆጣጠር (እንደ አስፕሪን ወይም ፓራሲታሞል ያሉ)። የፒ..ዲ ታካሚው በተደጋጋሚ የሚመላለስ ወይንም ሀይለኛ የሆነ ህመም በእጢዎቹ መስፋፋት ምክንያት ይከሰትበ ታል።
 • የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽኖችን በፍጥነት እና በተመጣጣኝ አንቲባዮቲክ መድህኒት ማከም።
 • የኩላሊት ጠጠርን ቀደሞ ማከም።
 • ግለሰቡ እብጠት ከሌለው ፈሳሽ በብዛት መውሰድ የሽንት ህመሞችን እና የኩላሊት ጠጠርን ለመከላከል ይረዳል።
 • በምዕራፍ 10 እስከ 14 እንደተብራራው ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመምን በጥንቃቄ መታከም።
 • በጣም ጥቂት በሆኑ ታካሚዎች ውስጥ በቀዶ ጥገና ወይም በሬዲዮሎጂ ፈሳሽ የቋጠሩትን እጢዎች በህመም ፣ በደም መፍሰስ ፣ በኢንፌክሽን ወይም በመዘጋት ምክንያት ማስወገድ ሊያስፈልግ ይችላል።

.. ያለበት ህመምተኛ ሐኪም ማማከር ያለበት መቼ ነው?

የፒ..ዲ ሕመምተኞች የሚከተሉት ነገሮች ካለባቸው ወዲያውኑ ዶክተር ማማከር አለባቸው።

 • ትኩሳት ድንገተኛ የሆድ ህመም ወይም ቀይ ሽንት።
 • ከባድ ወይም ተደጋጋሚ የመጣ ራስ ምታት።
 • በተለቀ ኩላሊት ላይ ድንገተኛ ጉዳት መከሰት።
 • የደረት ህመም ፣ የምግብ ፍላጎት ማጣት ፣ ከባድ ማስታወክ ፣ ከባድ የጡንቻ ድክመት ፣ ግራ መጋባት ፣ ድብታ ፣ ራስን መሳት ወይም መንቀጥ ቀጥ መከሰት።