Read Online in Amharic
Table of Content
መግቢያ እና ይዘቶች
መሰረታዊ መረጃ
የኩላሊት መድከም
ሌሎች ዋና ዋና የኩላሊት ህመሞች
የኩላሊት ህመም ወቅት አመጋገብ

1. መግቢያ

ኩላሊት አላስፈላጊ ቆሻሻዎችን እና መርዛማ ነገሮችን ከሰውነታችን በማስወገድ ሰውነታችን ንፁህ እና ጤናማ እንዲሆን ከፍተኛ ሚና ከሚጫወቱ የሰውነታችን ክፍሎች መካከል ዋነኛዉ ነዉ። ምንም እንኳን ዋናኛ የኩላሊት ተግባር መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ከሰውነት ማስወገድ ቢሆንም ብቸኛ ተግባሩ ግን አይደለም። የደም ግፊትን በማስተካከል በሰውነት ውስጥ ያለውን ፈሳሽ እና ንጥረነገሮችን መጠን በመቆጣጠር ረገድም ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። አብዛኞቻችን ሁለት ኩላሊቶች ይዘን ብንወለድም ሁሉንም አስፈላጊ ሥራዎችን በብቃት ለመወጣት አንድ ኩላሊት ብቻ በቂ ነው።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአሳሳቢ ሁኔታ በስኳር እና በከፍተኛ የደም ግፊት ህመም የሚሰቃዩ ሕመምተኞች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ የኩላሊት ህመም የሚሰቃዩ ታካሚዎች ቁጥር በተመሳሳይ እንዲጨምር ገፊ ምክንያት ሆኗል። ይህ ደግሞ ስለ ኩላሊት ህመም ፣ መከላከያ መንገዶች እና ቅድመ ህክምና የተሻለ ግንዛቤና መረዳትን ማዳበር ላይ ቀሪ የቤት ሰራዎች እንዳሉብን አመላካች ነዉ።

በመሆኑም ፣ ይህ መጽሐፍ ታካሚዎች ከኩላሊት ህመም ጋር ተያያThነት ያላቸውን ጥያቄዎች በመመለስ እና ስለህመሙ የተሻለ ግንዛቤ በማስጨበጥ በተሻለ መልኩ ህመሙን ማከም እንዲያስችላቸው ለመርዳት ያለመውን ግብ በመጠኑም ቢሆን እንደሚያግዝ ተስፋችን ነው።

የመጽሐፉ የመጀመሪያ ክፍል፣ ኩላሊት በሰው አካል ውስጥ ስላለው ወሳኝ ሚና አንባቢያንን ያስተዋውቃል። በተጨማሪም ከኩላሊት ጋር ተያያThነት ያላቸውን ህመሙን ለመከላከል የሚያስችሉ እርምጃዎችን ይጠቁማል። መጽሐፉ የኩላሊት ሕመም ምልክቶች እና የምርመራ ውጤቶችን የሚዳስስ ከመሆኑም በላይ አንባቢዎች የተለያዩ የሕክምና አማራጮችን እንዲለዩም ጭምር የሚረዳ ይሆናል።

ከዚህም ባለፈ የመጽሐፉ ዋና ክፍል በተለይ የኩላሊት ህመምተኞችን እና ቤተሰቦቻቸውን በሚመለከት ለሚነሱ ጉዳዮች መፍትሔ ለመጠቆም የተፃፈ ነው። ከሁሉም በላይ የዚህ መጽሐፍ ስለ ኩላሊት ህመም ብዙ ክፍሉን መያዙ ለኩላሊት ታካሚዎች እና ቤተሰቦች እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ አዘጋጆቹ ያመናሉ።

መፀሀፉ ስለ ስር ሰደድ የኩላሊት ህመም፤ ስለ መጀመሪያ ደረጃ ላይ የኩላሊት እጥበት፤ የኩላሊትና የካዳቫር ንቅለ ተከላ ደረጃ የሚደርስበትን ፍጥነት መቀነስ እንዲቻል በሚደረግ ሙከራ ሂደት ዉሰጥ መወሰድ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች የሚያተኩር ልዩ ምዕራፍ በዉስጡ አካቶ ይዟል።

መጽሐፉን ለኩላሊት ህሙማን የተሟላ ማስተማሪያ ለማድረግ፣ ስለ ተለመዱ የኩላሊት ችግሮች (ከኩላሊት ስራ ማቆም ህመም በስተቀር) የተሳሳቱ አመለካከቶች፤ ስለ ኩላሊት ህመም እውነታዎች የኩላሊት ህመሞች ለመከላከል የሚረዱ ወሳኝ መረጃዎች፤ የኩላሊት ህመምተኞች ስለሚጠቀሙባቸው የተለመዱ መድኃኒቶች እና ሌሎችም ብዙ መረጃዎችን አካቷል።

ለከባድ የኩላሊት ህመምተኞች የአመጋገብ ሁኔታ አሳሳቢ በመሆኑ እና ለብዙሃኑ ግራ መጋባትን በመፍጠሩ በዚህ መፅሐፍ ውስጥ ይኸዉ ርዕሰ ጉዳይ በትኩረት የሚዳስስ ምራፍም በመጸሀፉ ዉሰጥ አናገኛለን። ህመምተኞች ማደረግ ስለሚኖርባቸዉ ጥንቃቄዎች ከትክክለኛና በቂ የአመጋገብ ምርጫዎች ጋር በዝርዝር ያሰቀምጣል በመጨረሻም የቃላት ፍቺ በሚለው የመጽሐፉ ክፍል ውስጥ ጥቅም ላይ የዋሉትን ምፅሃረ ቃላት እና የህክምና ቃላትን ያብራራል።