Read Online in Amharic
Table of Content
መግቢያ እና ይዘቶች
መሰረታዊ መረጃ
የኩላሊት መድከም
ሌሎች ዋና ዋና የኩላሊት ህመሞች
የኩላሊት ህመም ወቅት አመጋገብ

21. ኩላሊት እና መድኃኒቶች

የተለያዩ መድኃኒቶች በመውሰድ የሚከተሉ የኩላሊት ጉዳቶች ተለምደዋል።

ከሌሎች የሰውነት አካል ክፍሎች አንፃር ኩላሊት ለምንድን ነው በመድኃኒት መርዛማነት ይበልጥ ለጉዳት ተጋላጭ የሆነው?

በመድኃኒቶች ምክንያት ለሚከሰቱ የኩላሊት ጉዳት መንስኤዎች መካከል አብይት የሆኑት፡-

1.   መድኃኒቶች በኩላሊት በኩል መወገዳቸው፡- ኩላሊት በሰውነታችን ዉስጥ ያሉትን መድኃኒቶች እና የእነርሱን ንጥረነገሮች ሚያሰወግዱ አካላት መካከል ዋናዉን ቦታ ይይዛል። በዚህም የማስዎገድ ሂደት ላይ አንዳንዶች መድኃኒቶች እና የነሱን አገንቢነት ኩላሊትን ሊጎዱት ይችላሉ።

2.  ወደ ኩላሊት የሚሄድ ከፍተኛ የደም ሙሌት፡- በእያንዳዱ ደቂቃ ልብ ከሚረጨዉ ሙሉ የሰውነት ደም መካከል 20 በመቶ የሚሆነው (1200 ሚሊ ሊትር ደም) ለመጣራት ወደ ኩላሊት ይገባል። ሰውነታችን ዉስጥ ካሉ አካላት መካከል በክብደታቸው አንፃራዊነት ሲታይ ኩላሊት ከሁሉም ከፍ ያለ መጠን ደም ያገኛል። ከፍተኛ የደም መጠን በማግኘቱም ምክኒያት ጎጂ መድኃኒቶች እና ንጥረ ነገሮች በአጭር ጊዜ ዉስጥ ከፍተኛ መጠን ይደርሱታል። ይህም ኩላሊትን ሊጎዳው ይችላል።

ኩላሊትን የሚጎዱ አበይት መድኃኒቶች

1. ህመም ማስታገሻ ክኒን

ለሰውነት፣ ህመም፣ ራስ ምታት፣ መገጣጠሚያ፣ ህመም እና ትኩሳት የተለያዩ ቁጥጥር የሚያስፈልጋቸው መድኃኒቶች ይገኛሉ። እነዚህም መድኃኒቶች ያለ ሀኪም ማዘዣ በነፃነት ሊወሰዱ ይችላሉ። ለኩላሊት ጉዳት እነዚህ መድኃኒቶች ዋናዉን ድርሻ ይወስዳሉ።

ስቴሮይድ የሌላቸው የሰውነት ሴሎች መቆጣትን የሚቀንሱ መድኃኒቶች ህመም ትኩሳት እና የሰውነትን መቆጣትን ለመቀነስ የሚጠቅሙ የተለመዱ መድኃኒቶች ናቸው።

ከእነዚህ መድኃኒቶች መካከል፤ አስፕሪን፣ ዳይክሎፌናክ፣ አይብፕሮፊን፣ ኢንዶሜታሲን ኬቶፕሮፊን፣ ሜሎክሲካም፣ ሜፌናሚክ አሲድ፣ ኒሜሱላይድ፣ ናፕሮክሲን ይጠቀሳሉ።

ስቴሮይድ የሌላቸው የሰውነት ሴሎች መቆጣትን የሚቀንሱ መድኃኒቶች የኩላሊት ጉዳት ያስከትላሉ?

ስቴሮይድ የሌላቸው የሰውነት ሴሎች መቆጣትን የሚቀንሱ መድኃኒቶች በሐኪም ክትትል ስር በትክክለኛው መጠን ከተወሰዱ በአጠቃላይ አይጎዱም። ነገር ግን ማስተዋል ያለብን ነገር ቢኖር ስቴሮይድ የሌላቸው የሰውነት ሴሎች መቆጣትን የሚቀንሱ መድኃኒቶች መድኃኒት በመውሰድ ከሚከሰት የኩላሊት ጉዳት አምጪ መድኃኒቶች ዝርዝር ዉስጥ ከአሚኖግላይኮሳይዶች በመከተል በሁለተኝነት ደረጃ ተቀምጦል።

ስቴሮይድ የሌላቸው የሰውነት ሴሎች መቆጣትን የሚቀንሱ መድኃኒቶች ኩላሊት መቼ ነው የሚገዱት

ስቴሮይድ የሌላቸው የሰውነት ሴሎች መቆጣትን የሚቀንሱ መድኃኒቶች በመውሰድ ለሚከሰት የኩላሊት ጉዳት አስጊ ምክንያቶች፡-

 • ያለ ዶክተር ክትትል በከፍተኛ መጠን ረዘም ላለ ጊዜ መውሰድ።
 • የብዙ መድኃኒቶች ቅልቅል የያዘ አንድ ኪኒን ረዘም ላለ ጊዜ መውሰድ (ለምሰሌ APC በውስጡ አስፕሪን፣ፌናሴቲን እና ካፊን ይዟል።)
 • አረጋውያን የኩላሊት አቅም ማነስ ስኳር ወይንም ውኃአነስነት ያላቸ ሰው ሰዎች ሲወስዱ።

የኩላሊት አቅም ማነስ ላለባቸው ሰዎች የትኛው የህመም ማስታገሻ መድኃኒት ቢወስዱ ጉዳት አይኖረውም?

ፓራስታሞል ከስቴሮይድ የሌላቸው የሰውነት ሴሎች መቆጣትን የሚቀንሱ መድኃኒቶች አንፃር ተመራጭ ነው።

ብዙ የልብ ታማሚወች የእድሜ ልክ አስፕሪን ይታዘዝላቸዋል። ይሄ መድኃኒት ኩላሊትን ሊጎዳው ይችላል?

ለልብ ታማሚወች አነስተኛ መጠን እስፕሪን ስለሚመከር አይጎዳም።

በስቴሮይድ የሌላቸው የሰውነት ሴሎች መቆጣትን የሚቀንሱ መድኃኒቶች የሚከሰት የኩላሊት ጉዳት ሊሻሻል ይችላል?

አዎ እና አይ

አዎ፡- አጣዳፊ የኩላሊት ጉዳት የመጣው አጠር ላለ ጊዜ ስቴሮይድ የሌላቸው የሰውነት ሴሎች መቆጣትን የሚቀንሱ መድኃኒቶች በመጠቀም ከሆነ አብዛኛውን ጊዜ ስቴሮይድ የሌላቸው የሰውነት ሴሎች መቆጣትን የሚቀንሱ መድኃኒቶች በማቆም እና አስፈላጊውን የህክምና ክትትል በማግኘት ይሻሻላል።

አይ፡- አብዛኛዎቹ የመገጣጠሚያ ህመም ያለባችው አረጋውያን ታካሚዎች ረዘም ላለ ጊዜ ስቴሮይድ የሌላቸው የሰውነት ሴሎች መቆጣትን የሚቀንሱ መድኃኒቶች ያስፈልጋቸዋል። በተከታታይ ከፍ ባለ መጠን ረዘም ላለ ጊዜ (ዓመታት) ስቴሮይድ የሌላቸው የሰውነት ሴሎች መቆጣትን የሚቀንሱ መድኃኒቶች መወሰድ ዝግ ያለ ቀስበቀስ የሚጭምር የኩላሊት ጉዳት ያስከትላል። ይህን አይነት የኩላሊት ጉዳት ኢተመላሺ (ኢተሻሻይ) ነው። አርጋዊያን ታካሚዎች ከፍ ያለ መጠን ያለው ስቴሮይድ የሌላቸው የሰውነት ሴሎች መቆጣትን የሚቀንሱ መድኃኒቶች ለረThም ጊዜ መውሰድ ካስፈለጋችው፤ በሃኪም እዉቅናና ክትትል ሊሆን ይገባዋል።

አንድ ስው በስቴሮይድ የሌላቸው የሰውነት ሴሎች መቆጣትን የሚቀንሱ መድኃኒቶች ምክንያት የመጣ ዝግ ያለ፤ ነገርግን ቀስበቀስ የሚጭምር የኩላሊት ጉዳት እንዳለበት እንዴት በጊዜ ሊያውቅ ይችላል?

 • በስቴሮይድ የሌላቸው የሰውነት ሴሎች መቆጣትን የሚቀንሱ መድኃኒ ቶች የተከስተ የኩላሊት ጉዳት እንዳለ የሚታወቅበት ቀዳሚ እና ብቸኛ ፍንጭ፤ በሽንት ውስጥ ፕሮቲን ሲገኝ ነው። የኩላሊት የመስራት አቅም ይበልጥ ሲዳከም በደም ውስጥ ያለው የክሪያቲኒን መጠን ከፍ ይላል።

ህመም ማስታገሻ መድሀኒቶች በመውሰድ ከሚከሰት የኩላሊት እክል አንድ ስው እንዴት እራሱን ሊጠብቅ እና ሊከላከል ይችላል?

የህመም ማስታገሻ በመውሰድ ከሚመጣ የኩላሊት ጉዳት ለመከላከል፤ መውሰድ ከሚገባችው ቀላል እርምጃዎች መካከል የተወሰኑትን እንመልከት፡-

 • አስጊ ታካሚዎች ላይ ስቴሮይድ የሌላቸው የሰውነት ሴሎች መቆጣትን የሚቀንሱ መድኃኒቶች አለመጠቀም።
 • የህመም ማስታገሻ መድኃኒቶችን ሳያረጋግጡ አለመጠቀም።
 • ስቴሮይድ የሌላቸው የሰውነት ሴሎች መቆጣትን የሚቀንሱ መድኃኒቶች ለረጅም ጊዜ መውሰድ ካስፈለገ በሀኪም ክትትል ስር መሆን አለበት።
 • በህክምና ጊዜ የ ስቴሮይድ የሌላቸው የሰውነት ሴሎች መቆጣትን የሚቀ ንሱ መድኃኒቶች መጠን እና የሚሰጥበትን ጊዜ መመጠን።
 • የተለያዩ የህመም ማስታገሻ መዳኃኒቶችን አቀላቅሎ ለረጅም ጊዜ አለመ ውሰድ ይመከራል።
 • በየቀኑ በርከት ያለ ውሃ መጠጣት፣ ስውነትን በቂ ውሃ መስጠት፣ ወደ ኩላሊት የሚሄደውን የደም ዝውውር ለመጠበቅ እና የኩላሊት እክል እን ዳያጋጥም ይረዳል።

2. አሚኖግላይኮሳይድ

 • አሚኖግላይኮሳይድ የተባሉት መዳኃኒቶች የአንቲባዩቲክ ቡደን ሲሆኑ በህ ክምና ላይ የሚዘወትሩ ነገር ግን የኩላሊት ጉዳት በማስከተል አቅማቸው የሚታወቁ መዳኃኒቶች ናቸው። የኩላሊት እክሉ የሚገጥመው መድኃኒት መውሰድ ከተጀመረ 7-10 ቀን ባለው ነው። ይህን ችግር ለይቶ ለማውቅ ያስቸግራል ምክንያቱም በምርመራ ወቅት የሽንት ይዘት እምብዛም አይቀ የርም።
 • በአሚኖግላይኮሳይድ የሚመጣ የኩላሊት ጉዳት ከፍ ያለ የመጠቃት እድል ካላችው መካካል፤ አርጋዊያን፣ ዝቅ ያለ የስውነት የውሃ መጠን ቀድሞ የነበር የኩላሊት እክል፣ ፓታሲየም እና ማግኒዚየም እጥረት፣ ረዘም ላለ ጊዜ ከፍተኛ የአሚኖግላይኮሳይድ መጠን መውሰድ፣ ሌሎች ኩላሊትን ከሚጎዱ መድኃኒቶች ጋር አብሮ መውሰድ፣ ሴፕሲስ፣ የጉበት ህመም እና ኮንጄስቲቭ የልብ ድካም ይካለላሉ።

አሚኖግላይኮሳይድን በመውሰድ ከሚከስት የኩላሊት እክል አንድ ስው እንዴት እራሱን ሊጠብቅ እና ሊከላከል ይችላል?

አሚኖግላይኮሳይድ በመውሰድ ከሚመጣ የኩላሊት ጉዳት ለመከላከል መውሰድ ከሚገባቸው ቀላል እርምጃዎች መካከል፡-

 • የጉዳቱ ስጋት ያለባቸው ታካሚዎች ላይ ጥንቃቄ በተሞላ መልኩ መጠቀም። በተቻለ መጠን ለስጋት የሚዳርገዉን ሕመም ማስወገድ አልያም በተቻለ መጠን መቀነስ ተገቢ ይሆናል።
 • በቀን ውሰጥ ብዙ ጊዜ መድኃኒቱን ከመስጠት መቆጠብ እና በቀን አንድ ጊዜ ብቻ መስጠት።
 • አሚኖግላይኮሳይድ ቴራፒ ሲሰጡ ስኬታማ መጠን፣ አመቺ እና የጊዜ ርዝመት መስጠት።
 • በቅድሚያ የነበረ የኩላሊት እክል ካለ የመድኃኒቱን መጠን ማስተካከል።
 • የኩላሊት ጉዳት ካለ በጊዜ ለመያዝ አንድ ቀን እየዘለሉ በተከታታይ የሴረም ክሪያቲኒንን መቆጣጠር።

3. ሬድዮ ሜትራዊ መለያ መርፌ

ሬድዩግራፊክ ኮንትራስት ሚዲያ (x-ሬድ ማቅለሚያ) ምክንያት የሚከሰት አጣዳፊ የኩላሊት ድክመት በሀኪም ቤት ታካሚወች ላይ የተለመደ ነው። አብዛኛውን ጊዜም ይሻሻላል። ስኳር ፣ ዝቅተኝ የሰውነት የውሀ መጠን፣ የልብ ድካም፣ ቀድሞ የነበረ የኩላሊት ህመም፣ የእድሜ መግፋት እና ሌሎች ኩላሊትን የሚጎዱ መድኃኒቶች አብሮ መጠቀም በኩላሊት ጉዳት የመያዝ ስጋትን ይጨምራል።

በዚህ መንገድ የሚመጣውን የኩላሊት ጉዳት ለመከላከል የተለያዩ እርምጃዎችን መውሰድ ይቻላል።

ከነዚህም መካከል፡- ዝቅተኛ መጠን ማቅለሚያ መጠቀም አዮኒክ ያልሆኑ ማቅለሚያዎችን መጠቀም ፣ የሰውነትን የውሀ እና ንጥረ ነገሮችን መጠን መጠበቅ እና ሶድየም ባይካርቦኔት እና አሴታይልሲስቲን ለሰውነት መስጠት ይገኙበታል።

4. ሌሎች መድኃኒቶች

 • ኩላሊትን ሊጎዱ ከሚችሉ መድኃኒቶች መካከል የተለመዱት አንዳድ አን ቲባዮቲክስ የካንሰር መድኃኒቶች እና የቲቢ መድኃኒቶች ይገኙበታል።

5. ሌሎች መድኃኒቶች

 • በተለምዶ ሁሉም የተፈጥሮ መድኃኒቶች (የቻይና እፅዋት የመሳሰሉት) እና የምግብ ተጨማሪ ግብአቶች ጉዳት የላቸውም የሚለው እሳቤ ትክክል አይደለም።
 • ከእነዚህ መካከል አንዳዶቹ የተፈጥሮ መድኃኒቶች ከባድ ብረታብረት እና ጎጂ ንጥረነገር በዉስጣቸው አካተው ይዘዋል እናም ይህ ኩላሊትን ሊጎዳ ይችላል።
 • ከእነዚህ መካከል አንዳዶቹን የተፈጥሮ መድኃኒቶች መጠቀም የኩላሊት ድክመት ላለባቸው ታካሚዎች አደገኛ ሊሆን ይችላል።
 • ከፍተኛ የፖታሲም መጠን ያላቸው የመድኃኒት ዝርያዎች የኩላሊት ድክመት ታካሚዎች ላይ ገዳይ ሊሆን ይችላል።